ትላንት ፤ ዛሬ፤ ነገ // yesterday; today tomorrow // ክፍል 5// Section 5

 



ክፍል 5

ትላንት ፤ ዛሬ፤ ነገ

    ሰው በለውጥ ውስጥ ከሚያልፉት ፍጥረታት መካከል አንዱ ነው፡፡ በለውጥ ውስጥ ማለፍ የማይችሉ ደግሞ አሉ፡፡ ለምሳሌ መላዕክት ሲፈጠሩ የያዙትን ተፈጥሮና ማንነት ይዘው እሰከዛሬ አሉ፡፡ ምንዓልባትም ወደፊትም በዚህ ሁኔታ ይቀጥሉ ይሆናል፡፡ እነእርሱ ተራክቦ አይፈፅሙም፡፡ በዚህ ምክንያት አይራቡም፡፡ በትንሽነት ተፈጥረው እያደጉ የሚሄዱም አይደሉም፡፡ በዚህ ምክንያት በለውጥ/ በመቀየር ውስጥ የሚያልፉ ሆነው አልተፈጠሩም፡፡ ሰማይና ምድርም ባሉበት ያሉ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ከፍም ዝቅም አይሉም፡፡ 

 ልክ እንደ ሰው ሁሉ ብዙ ፍጥረታት በመለወጥ ውስጥ የሚያልፉ አሉ፡፡ ለምሳሌ እፅዋት፣ አዕዋፋት፣ እንስሳት፣ እና የመሳሰሉትን ብንመለከት እየተለወጡ የሚሄዱ ናቸው፡፡ በእኛ በሰዎች እይታ መለወጣቸውን የምንመለከተው ከሚታየው አካላቸው ማለትም ከቁመትና ከክብደት አንጻር ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አሁንም ምርምር የሚሻ ጉዳይ ቢሆንም በሚታይ ብቻ ሳይሆን በማይታየው (በባህሪ፣ በአመለካከት፣ በአስተሳሰብ) የለውጥ ሂደት ውስጥም እንደሚያልፉ የሚያሳይ ነገር አላቸው፡፡ 

 የሰው ልጅ ግን ከሁሉም በተሻለና በበለጠ በለውጥ ውስጥ እንዲኖርና እንዲያልፍ ሆኖ የተፈጠረ ነው፡፡ ሰው ከመሆኑ በፊት ጀምረን ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሰው ሆኖ አድጎና ሰው ሆኖ እስከሚሞት ድረስ ያለውን ሂደት ብንመለከትና ብናጤን የምንረዳው ይህንን ነው፡፡ እድገቱ ወይም ለውጡ አጠቃላይ ሰውነቱን የሚነካ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡  በአካል ከትንሽነት እስከ ትልቅነት ይሄዳል፡፡ በእውቀት ምንም ከአለማወቅ እስከ ሁሉን አዋቂና ጠቢብ እስከመሆን ይደርሳል፡፡ በአስተሳሰብ ውስን ከሆነው ተነስቶ ውስብስብና እረቂቅ የሆነውን እስከማሰላሰል ድረስ አቅም አለው፡፡ በኢኮኖሚም ካየነው ከአንድ ብር ባለቤትነት ተነስቶ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ትሪሊየነር መሆን ይችላል፡፡ በፖለቲካው መስክ ከቃኘነው  ደግሞ ከእድር መሪ ተነስቶ እስከ ሀገር አስተዳዳሪነት መድረስ ይችላል፡፡ ይሄ ሁሉ መሆን የቻለው የሰው ልጅ በለውጥ ውስጥ ያለማንም ከልካይ ማለፍ እንደሚችል ሆኖ የተፈጠረ በመሆኑ ነው፡፡

  አዎ የሰው ልጅ ከትላንት ዛሬ ከዛሬ ደግሞ ነገ አዲስ ነገር እያሰበ አዲስ ነገር እየሰራ መሄድ ያለበት ፍጥረት ነው፡፡ ሁልጊዜ ተመሳሳይ አኗኗር የሚኖር ከሆነ ትክክል አይደለም፡፡ እንደደረቀ እንጨት ትላንት ከቆመበት ላይ ዛሬም በሰውነትም በአስተሳሰብም በኢኮኖሚም ቆሞ ነገን የሚጠብቅ ከሆነ ሰው አይደለም ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ በሰውነቱ እየጠነከረ እየረዘመ እየገዘፈ የሚሄድ ነው፡፡ በአስተሳሰቡም ልጅ ከሆነው አስተሳሰቡ ተነስቶ ትልቅ የሆነውን አስተሳሰብ በውስጡ የሚቀበል ነው፡፡ ልጅ እያለ የሚያስበው ከሚያዝናናው ከሚበላውና ከሚጠጣው እንዲሁም ከሚለብሰው የዘለለ አይሆንም፡፡ ከፍ ሲል ደግሞ ስለክብሩ ማሰብ ይጀምራል፡፡ ስለቤተሰቡና ስለማህበረሰቡ ማሰብ እንዳለበት ያስባል፡፡ ዘብ ለመቆምም እራሱን ማዘጋጀት ይጀምራል፡፡ አሁንም ከዚህ ከፍ ሲል የህይወት አጋሩን መፈለግ እንዳለበት ያምናል፡፡ ሃላፊነት ለመቀበል ዝግጁ ይሆናል፡፡ ልጅ ይወልድና ከልጅነት አስተሳሰቡ ሙሉ በሙሉ እየተላቀቀ ይመጣና የበለጠ ትልቅ የሆነ አስተሳሰብ በውስጡ ማስረፅ ይጀምራል፡፡ ስለእራሱ ብቻ አብዝቶ ሲያስብ የነበረው ሰው ከራሱም ከቤተሰቡም እርቆ የእየለዕት ሀሳቡ የሀገሩና የወገኑ እንዲሁም ከእምነቱ ጋር ያለው ጉዳይ ይሆናል፡፡ እናም የሰው ልጅ ትላንት የያዘውን አስተሳሰብ ዛሬ አይዝም፡፡ ቀደም ብሎ ስለእራሱ ብቻ ያስብ ከነበረ ዛሬ ግን የግድ የቤተሰቡ ጉዳይ ያሳስበዋል፡፡ ትላንት የሀገሩ የድንበሩ ጉዳይ ሲያሳስበው ካልነበረ ዛሬ ግን የግድ ያሳስበዋል፡፡ ምክንያቱም የሚለወጥ ማንነት አለውና፡፡ 

 የሚለወጥ ማንነት ያለውን የሰውን ልጅ ትላንት በነበረው አስተሳሳብ ምክንያት ዛሬ ልንገፋው አይገባም፡፡ እርግጥ ነው ትላንትና በነበረው ሀሳብና አስተሳሰብ ምክንያት ብዙ በድሎ ብዙ አጉድሎ ይሆናል፡፡ እውነት ነው ትላንት ያለተገራ ሀሳብ ይዞ ስህተት ሰርቶ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተሰብ አፍሮበት ማህበረሰብ አዝኖበት አካባቢውም ተንቆበት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዛሬ ትልቅ ሀሳብ አንግቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ትልቅ ዕራይ ሰንቆልን ሊሆን ይችላል፡፡ ማን ያውቃል ትላንት እንደዚያ ሲያዋክበን የነበረው ሰው ዛሬ ለችግራችን መፍትሔ፣ ለህመማችን መድሐኒት ይዞልን መጥቶ ይሆናል፡፡ ቆም ብሎ ማሰብ አለብን፡፡ እንጅ በትላንት ማንነቱ ምክንያት ገፍተን ጥለነው ዛሬ ይዞልን የመጣውን በረከት እንዳናጣው መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ በእረኛዬ ድራማ በዚህ ክፍል ውስጥ የምናገኘው ቁምነገር  ይህ ነው፡፡

 በነገራችን ላይ ከችግራችን መላቀቅ፣ ከህመማችን መፈወስ ያቃተን ሌላ ብዙ ምክንያት ቢኖረንም አንደኛው ግን ትላንት የሆነውን ሁሉ ዛሬም ማሰብና መተከዝ ልምዳችን ስላደረግን ነው፡፡ ምልከታችን ሁሉ ለውጥ የሌለበት በመሆኑ ነው፡፡ አንድን ሰው ትላንት ሌባ ከነበረ ዛሬም ሌባ ነው ብሎ ከእርሱ ጋር በጋራ ላለመስራት የመወሰን ችግር ነው፡፡ ትላንት እነግዳለው ብሎ ከከሰረ ዛሬም ይከስራል ብሎ ማሰብ ከድህነት እንዳይወጣ መከልከል ነው፡፡ 

  ወጣት እያለን የጠላንን ያጣላንን ሰው ዛሬም ያንን አመለካከቱን ሊተው አይችልም ብሎ ሀሳቡን ላለመቀበል ገሸሽ ማለት የሰው ልጅ የሚለወጥ ማንነት አንዳለው መርሳት ነው፡፡ መመዘኛችን ዛሬ እንጅ ትላንት መሆን የለበትም፡፡ ትላንት አይችሉም የተባሉ ሁሉ ዛሬ ችለው አሳይተውናል፡፡ ሰነፍ ያልናቸው ሁሉ በርትተው የስኬት ጫፍ ላይ ሆነው ተመልክተናል፡፡ 

እኛ ኢትዮጲያውያኖች ከድህነት እንውጣ ካልን ይህንን መጥፎ ልማድ ማስወገድ አለብን፡፡ የትኛውም ሰው ትላንት የነበረውን ማንነቱን ለውጦ ዛሬን እየኖረ ነው፡፡ ዛሬ ያዘው ማንነቱ ደግሞ ነገ እርሱም እየተለወጠ ስለሚሄድ አብሮ መለወጡ አይቀሬ ነው፡፡ እደግመዋለው በትላንት ሚዛን ማንም አይመዘን፡፡ 

 ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ከአባጅፋር መንደር

..................................................................................................................................................
....................................................................................

Section 5
yesterday; today tomorrow


     Man is one of the creatures that go through change. There are those who cannot go through change. For example, angels have the same nature and essence that they possessed when they were created. Perhaps you will continue this way in the future. They are not hungry. As a result, they do not starve. They are not small and growing. Because of this, they were not created to undergo transformation. They are beings that exist in heaven and earth. They do not say high or low.
  Like humans, many creatures go through transformations. For example, if we look at plants, birds, animals, etc., they are changing. From our human perspective, we can see them change only in terms of their visible body, i.e. height and weight. However, although it is still a subject that requires research, they have evidence that they go through a process of change not only in the visible but also in the invisible (behavior, attitude, thinking).
  But the human being is created to live and go through change better and more. This is what we can understand if we look at and consider the process that started before becoming a human being, until nature grew up as a human being and died as a human being. We find that the growth or change affects the whole body. Physically it goes from small to large. In terms of knowledge, it ranges from knowing nothing to being omniscient and wise. From the limited in thought to the complex and abstract, he has the capacity to contemplate. From what we have seen in the economy, it is possible to become a famous and influential trillionaire from owning one birr. If we look at it in the political field, it can reach from the leader of the web to the administration of the country. All this was possible because the human being was created in such a way that no one can pass through the barrier.
   Yes, the human being is a creature who has to think new things from yesterday, today and tomorrow, and do new things. It is not right to live the same lifestyle all the time. He is not a man if he is standing like a dry tree from the same place he stood yesterday with his body, mind, and economy and waiting for tomorrow. Human beings are getting stronger and taller. In his thinking, he rises from his childish thinking and accepts the big thinking in him. As a child, what he thinks about is nothing more than what he eats, drinks, and wears. And when he gets high, he starts thinking about his glory. He thinks he should think about his family and community. He begins to prepare himself to stand guard. He still believes that he needs to find his life partner when he gets high. Will be ready to accept responsibility. He gives birth to a child and is completely freed from his childish thinking and begins to instill a bigger thinking in him. The person who was thinking about himself too much, away from himself and his family, his future thoughts will be about his country, his family and his faith. And the human being does not hold the same thinking that he had yesterday. If earlier he only thought about himself, today he is definitely concerned about his family. If yesterday he was not concerned about the country's border issue, today he is definitely concerned about it. Because he has a changing identity.
  We should not push the human being who has a changing identity today because of yesterday's thinking. Of course, because of yesterday's thoughts and thinking, he may have suffered a lot. It is true that he may have made a mistake yesterday with an unbridled thought. As a result, the family will be ashamed, the community will be sad and the area will be shunned. But today he may have a big idea. It could be a big deal. Who knows, the person who was harassing us like that yesterday may have come with a solution to our problem, a medicine for our pain. We have to stop and think. But it is appropriate to be careful that we do not lose the blessing that has come to us today because we pushed him away because of his personality yesterday. This is the essence of this episode of the Shepherd's drama.
  By the way, although there are many other reasons why we have not been able to get rid of our problems and heal from our pain, one of them is because we have made the habit of thinking about everything that happened yesterday. Because all our observations are changeless. If someone was a thief yesterday, he is still a thief today, it is a problem to decide not to work together with him. Thinking that if he was bankrupt yesterday, he will be bankrupt today is to prevent him from getting out of poverty.
   To refuse to accept the idea that the person who hated us when we were young and lost can't give up that attitude today is to forget that human beings do not have a changeable identity. Our standard should not be yesterday but today. Everyone who said they couldn't do it yesterday has shown us how to do it today. We have seen all those we called lazy become strong and on the verge of success.
If we Ethiopians want to get out of poverty, we must get rid of this bad habit. Anyone can change who they were yesterday and live today. The person he is today will inevitably change as he changes tomorrow. I repeat, let no one be weighed by yesterday's scale.

Bamlaku Abebaw, jimma

key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post