“አትጠራጠሩ እናሸንፋለን:: //"Don't doubt, we will win." ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ// P M Dr. Abiy Ahmed

 
ክፍል 2



“አትጠራጠሩ እናሸንፋለን፡፡”
                            ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ
 
 ስለ “ቃል” ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አሁን ወደ አሉበት የሀላፊነት እርከን ሳይመጡ በፊት በአንድ መድረክ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ቃል ይተክላል፤ ቃል ይነቅላል” ነበር ያሉት፡፡ እውነት ነው ቃል ያደርቃል፡፡ ቃል ያለመልማል፡፡ይህንን ሀሳብ ቅዱሳት መፅሃፍትም እንደገናም የመሳሳብን ህግ (the law of attraction) መሰረት በማድረግ የተፃፈው “ሚስጥሩ” የሚለው መፅሀፍ አብራርቶታል፡፡
ወደ እነዚህ ሁለት ቃላት ተመልሰን ታላቅነታቸውን እንመልከት፡፡ ዓለም ከጨለማ ወደ ብርሃን ዘመን የመጣው ባለመጠራጠር መንፈስ በእናሸንፋለን ስለ ልቦና የሚደክሙ ሰዎች ስለነበሩ ነው፡፡ እሳትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለመፍጠር ሲሞክሩ በውስጣቸው መጠራጠር ቢኖር ኖሮ መልካም ውጤቱን አያዩም ነበር፡፡ እሳትን ለመፍጠር እጃቸው እስኪላጥ ድረስ ማሸት ነበረባቸው፡፡ ይሄ ደግሞ እጅግ አድካሚ ነበር፡፡ ግን እንችላለን ብለው በአሸናፊነት መንፈስ ስለጣሩ ውጤት አመጡ፡፡ ሌላውም ነገር ልክ እንዲሁ ነው፡፡  አለመጠራጠር ቦታ አግኝቶ፤ እሸናፊነት ከፊት ስለቀደመ ብቻ ነው ስኬት የመጣው፡፡ ስለዚህ ዓለም ከዚህ ደረጃ ለመድረስ እነዚህ ሁለት ሆነው በአንድ የሚጠሩ ቃላት ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ መካድ አይቻልም፡፡ የሚሰሩት ስራ ውጤት እንደሚያመጣ ያማናሉ፤ እንዲሁም እንዳይሸነፉና ስራቸው በጅምር እንዳይቀር እናሸንፋለን የሚለውን ቃል ከልባቸው ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህም ነው ዳገቱን ደርምሰው ሜዳ ለማድረግ አቅም ያገኙት፡፡ ጨለማውን ገፈው የብርሃን ወጋገን ያሳዩን፡፡
ከልጅነት ጀምረን እየሰማን ያደግናቸው ቃላት ስብዕናችንን የመቅረፅ አቅም አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን እየሰማ ያደገ ልጅ በህይወት ዘመኑ መልካም የሚያደርግ ይሆናል፡፡ መጥፎ የሆኑ ቃላትን እየሰማ ያደገ ልጅ እንዲሁ በህይወቱ ክፋትን በማድረግ የሚስተካከለው ያጣል፡፡ በቤት ውስጥ አትችልም፣ አትረባም፣ ሰነፍ ነህ፣ አታሸንፍም፣….ወዘተ እየተባለ ያደገ ልጅ በስተመጨረሻ ስኬታማ ሳይሆን ቢቀር ብዙ አይገርምም፡፡ ምክንያቱም ቀድሞ ቤተሰቦቹ እንዳይሳካለት እንቅፋት እየሆኑ ስላሳደጉት ማለት ነው፡፡
 በተቃራኒው ደግሞ ትችላለህ፣ ጎበዝ ነህ፣ ታሸንፋለህ፣ ጀግና አንተ ነህ፣ ….ወዘተ እየተባለ ያደገ ልጅ በህይወት ስኬታማ ይሆናል፡፡ ዘወትር በአልሸነፍ ባይነት ስለሚሰራ እምቅ የአዕምሮውን ብቃት መጠቀም ይችላልና፡፡
 ይህንን “አትጠራጠሩ እናሸንፋለን፡፡” የሚለውን የጠቅላያችንን ንግግር ስሰማ አባቴ የነገረኝ ታሪክ ትዝ ይለኛል፡፡ ታሪኩ በገብረ ጉንዳን ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን እንዲህ ነበር ያለኝ፡፡
  “ከዘመናት በፊት ጉንዳኖች እንዲህ እንደአሁኑ በህብረት አይኖሩም ነበር፡፡ ከተወለዱ በኋላ መንቀሳቀስ እንደጀመሩ የሄዱበትን መንገድ ተከትለው በዚያ ይጠፋሉ፡፡ ከዚያም በዚያ እንደገና የራሳቸውን ኑሮ እንደአዲስ ይመሰርታሉ፡፡ ሁሉም የየራሳቸው የኑሮ ፍልስፍና መስርተው፣ የግላቸውን ባህልና እምነት ፈጥረው ነበር የሚኖሩት፡፡ ከአንድነት ይልቅ የነጠላ ኑሮ ነበር የሚመርጡት፡፡ በዚህም የተነሳ ብዙ እንግልት ይደርስባቸው ነበር፡፡ በብዙ ችግሮች ስለሚቸገሩ እድሜያቸው በጣም አጭር ነበረ፡፡ ቶሎ ቶሎ ስለሚሞቱ ቁጥራቸውም እንደአሁኖቹ ጉንዳኖች አይበዙም ነበር፡፡ የችግርን መፍትሄ ማግኘት ስለሚሳናቸው በዙ ይሰቃዩ ነበር፡፡ ምግብ ለማግኘት፣ መኖሪያ ለማዘጋጀት ሁሉ በጣም ይቸገሩ ነበር፡፡
 በዕድሜ ገፋ ያሉ አዛውንቶች ሲናገሩ “ጉንዳኖች አንድ የሚያደርጋቸው ብዙ ነገር እያለ የሚለያያቸው ነገርን ብቻ በማሰብ በህብረት ሳይኖሩ ብዙ እንግልት ደርሶባቸዋል፡፡ ባለማስተዋልና ባለማወቅ አንድ ባለመሆናቸው ፈተናዎች እየተደራረቡባቸው ሲሰቃዩ እንደነበር እያስታወሱ ይናገራሉ፡፡ጉንዳኖች በድሮ ዘመን መሪ አልነበራቸውም፡፡ በዚህ ውጡ በዚህ ግቡ እያለ እቅጣጫ የሚያሳይ ስላለነበራቸው ብዙ መካራ ሲያሳልፉ ነበር፡፡
 በኋላ ግን እንደዚህ መኖራቸው የሚያሳዝናቸው አንድ አንድ ጉንዳኖች በየቦታው መነሳት ጀመሩ፡፡ እነዚህ በየቦታው የተነሱት የተሻለማሰብ የሚችሉ ስለነበር ለችግራችን መፍትሄ ማግኘት አለብን በማለት ዘወትር ይጥሩ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀንም ለመሰባሰብ ወሰኑ፡፡ አዋጅ ተነገረ ነጋሪትም ተጎሰመና ሁሉም እንዲሰባሰብ ተደረገ፡፡ በሸለቆው፣ በዋሻው፣ በወንዙ፣ በየመንገዱ፣ በሰው ቤት ውስጥ ያሉት ሁሉ ተሰብሰበው ሀሳባቸውን እንዲሰጡ ታሰበ፡፡ በስብሰባው ላይ ብዙ ዓይነት ሀሳብ ተነስቶ ተወያዩበት፡፡ ደግ ደግ ሃሳብ ያነሱ አስተዋይ እንዳሉ ሁሉ በህብረት ከመኖር ይልቅ ተለያይቶ መኖር ይሻላል ያሉም ነበሩ፡፡ በስተመጨረሻ በህብረት ለመኖር ተስማምተው ሁሉም ደስ ብሏቸው አንድ ላይ መኖር ጀመሩ፡፡ አንድ ላይ ለመኖር ሲጀምሩ ግን ብዙ ነገር ፈትኗቸው ነበር፡፡ የሚግባቡበት ቋንቋአጡ፡፡ ባህላቸውና እምነታቸው ሊስማማ አልቻለም፡፡ አመለካከታቸውም የተለያዬ ስለነበር ወደ አንድ ለማምጣት ብዙ ጊዜ ወሰደባቸው፡፡ ነገር ግን ይሄንን ቀስ ቀስ እያሉ እያስተካከሉት ሄዱ፡፡ የሚለያያቸውን እየተው አንድ በሚያደርጋቸው ነገር ላይ ብቻ ትኩረት እያደረጉ አብሮነታቸውን አጠናከሩ፡፡
 አብረው መኖር ሲጀምሩ በእየዕለቱ ብዙ መልካም ነገሮች ማስተናገድ ጀመሩ፡፡ የበለጠ ደስተኛ እየሆኑ መጡ፡፡ ከዚህ በፊት የሚያስቸግራቸው ችግር አሁን ላይ ምንም አልመስል አላቸው፡፡ ማንኛውም ዓይነት ችግር ሲገጥማቸው ቆም ብለው ሰብሰብ ይሉና መመካከር ይጀምራሉ፡፡ ሀሳብ ያዋጡና ለችግሩ መፍትሔ ያስቀምጣሉ፡፡ ነገር ግን መፍትሄውን ተግባራዊ ለማድረግ ይፈሩ ነበር፡፡ ምክንያቱም በብቸኝነት ዘመናቸው ብዙ ሰቆቃ ስለደረሰባቸውና ከአዕምሯቸው ስላልጠፋ ነው፡፡ ይችላሉ፡፡ ይሰራሉ፡፡ አቅምም አላቸው፡፡ ግን ፍርሃትና የማሸነፍ ስነ ልቦና ማጣት አስቸገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ትላልቆቹና በሰል ያሉት ጉንዳኖች እንደገና ስብሰባ ጠርተው ለማወያየት አሰቡ፡፡
የስብስባቸውም አጀንዳ “እንዴት የሚገጥሙንን ችግሮች እየፈታን ስኬታማ ኑሮ መኖር እንችላለን?” የሚል ነበር፡፡ ውይይቱን ከፊት ሆኖ እየመራ ያለው አንድ ጉንዳን በአጀንዳው ዙሪያ ሰፊ ማብራርያ ሰጠ፡፡ እንዲህ በማለት “እኛ ባለማስተዋልና ባለማወቅ እጅግ ፈተና የበዛበት ኑሮ ኖርን፡፡ ስንት መፍትሄ ያለው ነገር ሲፈትነንና አለፍ ሲልም ሲገድለን ኖረ፡፡ አሁን ወደ አንድነት መጥተናል፡፡ ይሄ ትክክለኛና መልካም ተግባራችን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ምንም ይሁን ምን ሊያስቸግረን አይገባም፡፡ ለዚህ ደግሞ መሰባሰባችን ትልቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ሀሳብ እንስጥና ድጋሚ መሰብሰብ ሳያስፈልገን የዛሬውን መውሳኔ ተግባራዊ እያደረግን እንኖራለን፡፡” ብሎ ሌሎቹን መመልከት ጀመረ፡፡ ብዙ ሀሳብ ተነሳ፡፡ ደስ በሚል ሁኔታ ሀሳብ ተለዋወጡ፡፡ የስብሰባው አጀንዳ ለመቋጨት ሰብሳቢው ሲሰነዳዳ አንድ አዛውንት ጉንዳን እጃቸውን አነሱ፡፡
 እንዲህም አሉ “ ሁላችንም አሁን በተነጋገርነው መልኩ ለችግሮቻችን መፍትሄ እየሰጠን መኖር እንችላለን፡፡ እኔ ግን መፍትሄዎችን ብቻ ማወቅ የሚበቃን አይመስለኝም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከውስጣችን ያለውን እምቅ አቅም እንድንጠቀም መጠራጠርን ከውስጣችን ማስወገድ አለብን፡፡ የተሸናፊነትን ክፉ መንፈስ አስወግደን ሁሉንም እንደምናሸንፍ አምነን ነው ወደ ተግባር መግባት ያለብን፡፡ አለበለዚያ ነገም መፍራታችን አይቀርም፡፡ የሚፈራ ደግሞ መፍትሄ አያመጣም፡፡ አንጠራጠርም እናሸንፋለን የሚለውን ጉልበተኛ ቃል የህይወታችን መመሪያ ማድረግ አለብን፡፡” ብለው በስሜት ተናገሩ፡፡ ሁሉም አጨበጨበላቸው፡፡ ሁሉም ተቀበሉትና ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምተው ስብሰባቸውን ጨረሱ፡፡
 ጉንዳኖች ከዚህ ቀን ጀምረው በህብረት አንድ ሆነው ተዓምር መስራት ጀመሩ፡፡ የሚታለፉ የማይመስሉ መንገዶችን በህብረት ያልፋሉ፡፡ በህብረት ወንዝን ያህል ለመሻገር የሚከብድ ነገር እነእርሱ ግን ይሻገሩታል፡፡ በጣም ገደል በሆነ ቦታ ቢገቡ ተያይዘው ማንም ሳይቀር ይወጣሉ፡፡ ባሉበት ላይ አፈር ቢደፋባቸው በብልሃትና በጥበብ ይወጣሉ፡፡ አንበሳን ያህል ጉልበተኛ እንሰሳ በህብረት አቅሙን ያሳጡታል፡፡“አትጠራጠሩ እናሸንፋለን” የሚል ዜማ ሰርተው ሁሉም በአንድ ላይ በአንድ የአሸናፊነት መንፈስ ብዙ ችግርን አልፈዋል፡፡ ገናም ያልፋሉ፡፡
 እናም ልጄ እኛም እንደ ጉንዳኖች ህብረት ካለን ምንም ነገር ማድረግ እንችላለን፡፡ አለበለዚያ ግን ድካም ብቻ ነው የሚሆንብን” ብሎኝ ነበር፡፡
      እኔም በመጸሐፈ ምሳሌ 6፤6 ላይ “አንተ ታካች ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፡፡ መንገዷንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን፡፡” ያለውን የሰሎሞንን ቃል እያሰብኩ ጠቢብ ለመሆን አስብ ነበር፡፡

ይህ አባቴ የነገረኝ የጉንዳን ታሪክ እጅግ አስተማሪ የሆነ ነው፡፡ በተለይ ለእኛ ለኢትዮጲያውያን ብዙ ጠቃሚ ነጥብ አለው፡፡ አብሮነት ምን ያህል ስኬታማ ሊያደርገን እንደሚችል የተገነዘብኩበት ታሪክ ነው፡፡ በህብረት ውስጥ ትልቅነት አለ፡፡ ተበታትነው ይኖሩ የነበሩት ጉንዳኖች ምንም ነበሩ፡፡ በኋላ ግን አንድ ላይ ተደምረው በፍቅር ሆነው ሀሳብ ተለዋውጠው መኖር ሲጀምሩ ስኬታማ መሆን ቻሉ፡፡ ለዚህም ከመደመራቸው ጋር እኩል ሚና የተጫወተው “አትጠራጠሩ እናሸንፋለን” የሚለው ቃል ነው፡፡

  ይህ “አትጠራጠሩ እናሸንፋለን” የሚለው የጠ/ሚንስትሩ ንግግር እንደ ማንኛውም የእርሳቸው ንግግር በመውሰድ የቃሉን አሻጋሪነት ልናጣው አይገባም፡፡ ይህ ቃል ነገን በብልፅግና ለመኖር፤ አሁን ካለንበት የችግር አዘቅጥ ለመውጣት በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ ጉንዳኖች ባቅማቸው ይህንን ትልቅ አቅም ያለውን ቃል ተጠቅመው ከትላንት በተሻለ ዛሬ መኖር ከቻሉ እኛ ሰዎች ደግሞ ምን ያህል ልንጠቀምበት እንደምንችል መገመት አያስቸግርም፡፡

ይህንን ትልቅ አቅም ያለውን ቃል የተጠቀሙ ሁሉ ትልቅ ሆነዋል፡፡ የማይቻሉ የሚመስሉትን ሁሉ ችለዋል፡፡ የማይታለፉ የሚመስሉትን የችግር ዘመናት ሁሉ አልፈዋል፡፡ ዛሬ በስልጣኔ ከፍ ያሉ ሀገራት ብዙ ውስብስብ ችግሮች ደርሰውባቸው ነበር፡፡ ይህንን ችግራቸውን አልፈው ለዚህ የበቁት “አትጠራጠሩ እናሸንፋለን” የሚለውን ጉልበተኛ ቃል ተጠቅመው ነው፡፡ ይህንን እንድል ያስቻለኝ ይህንን ቃል በቀጥታ መጠቀማቸውን የሚያሳይ መረጃ አግኝቼ ሳይሆን የአሸናፊነታቸው ሚስጥር ይህ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ስለሌለኝ ነው፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ከዘመናት በፊት በአሸናፊነት መንፈስ ተነስትን ታሪክ ሰርተናል፡፡ለምሳሌ ከመቶ ሃያ አራት አመት በፊት ታሪካችንን ሊቀማ፤ ባህላችንን ሊያጠፋ፤ እምነታችንን ሊያጎድፍ የመጣውን ወራሪ ሀይል መክተን አሳፍረን ሊከነዋል፡፡  ይህንን የጣልያንን ወራሪ ሀይል ድል ያደረግንበት አኩሪ ተግባራችን ዋና ሚስጥሩ በእንችላለን  መንሰፍ መነሳታችን ነው፡፡ በጣልያን ጦር እና በኢትዮጲያ ጦር መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት ከንግግር በላይ ነው፡፡ እነእርሱ እጅግ ዘመናዊ የሚባሉ የጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል፡፡ የእኛዎቹ አባቶች ደግሞ ከእነእርሱ አንፃር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ ግን በኢትዮጲያውያን አርበኞች አዕምሮ ውስጥ እንደሚያሸንፉ ምንም ጥርጥር የላቸውም ነበር፡፡ከሁሉም የኢትዮጲያ ክፍል ተነስተው ወደ አድዋ ሲዘምቱ እንሸነፋለን የሚል አንዳችም ጥርጣሬ አልነበራቸውም፡፡ የእነእርሱ ዘመናዊ መሳርያ የአሸናፊነት ስነ ልቦናቸው ነው፡፡ ይህ እምነት የጣሉበት የውስጣቸው የአሸናፊነት ሀይል የእነእርሱ ዘመናዊ መሳሪያቸው ነው፡፡ ዘመናዊ መሳሪያቸው እንደማያሳፍራቸው እርግጠኛ ስለነበሩ፤ የአንድነት መዝሙራቸውን በህብረት እያዜሙ በኩራትና በጉጉት ጉዞ ወደ አድዋ አደረጉ፡፡ አባቶቻችን አርበኞቹ ያንን ተደራጅቶ የመጣውን ጉልበተኛ ነኝ ባይ የጣልያን ሰራዊት አፈር ድሜ አብልተው ሰደዱት፡፡ በንቀት የመጣውን ይህ የጣልያንን ሰራዊት አሸንፈውና የውርደት ካባ አከናንበው ሸኝተው እነእርሱ ደግሞ “ኢትዮጲያችን ኩሪ እኛም በአንቺ እንኩራ” እያሉ በዜማ ተመለሱ፡፡

በአሁን ሰዓት ይህ ቃል ያስፈልገናል፡፡ ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግመው ደጋግመው በየመድረኩ የሚናገሩት፡፡ ሁላችን በአንድተባብረን ከቆምንና ይህንን ቃል ተጠቅመን ከሰራን የማንበልፅግበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ በህብረት ተደጋግፈን፤ በሙሉ እምነት አምነንና በአሸናፊነት መንፈስ ከሰራን የችግራችንን መፍትሄ ቀላል በሆነ መንገድ ማግኘት እንችላለን፡፡

 እስከዛሬ ከተሳሳትናቸው ስህተቶች ዋናው ሁላችንም በአንድነት በአሸናፊነት መንፈስ ተባብረን አለመስራታችን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ዋጋ ከፍለናል፡፡ በብዙዎቹም ተቀድመን መሳቂያ መሳለቂያ ሆነናል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ይህንን አላዋቂነታችን ትተን ለነገው ትውልድ መስራት አለብን፡፡

 ለዚህ ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር የህይወታችን መመሪያ ልናደርገው ይገባል የምለው፡፡ እንደ ግል ለሚገጥመን ማንኛውም ችግር “አሸንፋለሁ አልጠራጠርም” እያልን እንደ ቡድንና እንደ ሀገር ለሚገጥመን ችግር ደግሞ “አንጠራጠርም እናሸንፋለን” ብለን መነሳት አለብን፡፡

 ባምላኩ አበባው፣ ጅማ፣ ከአባጅፋር መንደር




...................................................................................................................................



 Continued ….

"Don't doubt, we will win."

P M Dr. Abiy Ahmed

  Regarding the "word", PM/Dr. Abiy said this in a forum before he came to his current position of responsibility. He will plant a word. They said, "He will pull out a word." It is true that words dry up. Words don't attract. This idea is explained by the book "The Secret" written based on the law of attraction.
Let us return to these two words and consider their greatness. The world came from darkness to the light age because there were people who worked hard for the spirit of not doubting, we will win. If there had been doubt in them when they first tried to create fire, they would not have seen the good results. To create a fire, they had to rub their hands until they were numb. This was very exhausting. But because they tried with a spirit of victory, they achieved results. The other thing is the same. Doubt has found its place. Success comes only because winning comes first. Therefore, it cannot be denied that these two words played a significant role in reaching this level. They believe that what they do will produce results. They also use the word "we will win" from the bottom of their hearts so that they don't lose and their work is left at the beginning. That is why they were able to tear down the hill and make it a field. Push away the darkness and show us the path of light.
The words we grow up hearing from childhood have the power to shape our personality. A child who grows up hearing good things will do good things in his life. A child who grows up listening to bad words will also lose what is corrected by doing evil in his life. It's not surprising that a child who grows up being told at home that you can't, you're not stupid, you're lazy, you can't win, etc., is not successful in the end. It is because his family raised him by being an obstacle for him to succeed.
  On the contrary, a child who grows up being told that you can, you are smart, you will win, you are a hero, etc. will be successful in life. Because he always works with invincibility, he can use the potential of his mind.
  "Don't doubt it, we will win." I remember the story my father told me when I heard our general's speech. The story revolves around an ant hill and that's what I said.
   “A long time ago, ants did not live together like they do now. As soon as they start moving after birth, they follow their path and disappear there. Then they will re-establish their own lives there. They all established their own philosophy of life, created their own culture and beliefs. They preferred single life to unity. As a result, they suffered a lot of abuse. Their lives were very short because they were troubled by many problems. Because they died quickly, their numbers were not as great as ants are today. They suffered a lot because they couldn't find a solution to a problem. They were struggling to find food and shelter.
  Elderly people said, "Ants have many things in common, but they have suffered a lot of abuse without living together. They say that they were suffering because they were not united due to lack of understanding and ignorance. The ants had no leader in the old days. They were going through a lot of trouble because they had no direction to go with this goal.
  But later, one by one, ants began to rise up everywhere. They were always trying to find a solution to our problems because they were able to think better. They decided to get together one day. A proclamation was made and everyone was gathered together. In the valley, in the cave, in the river, in every street, all those in the house of man were gathered together to give their opinion. Many ideas were raised and discussed at the meeting. Just as there are those who are less wise than they are, there are those who say that it is better to live apart than to live together. In the end they agreed to live together and they all started living together happily. But when they started to live together, they were tested by many things. They lost their language. Their culture and beliefs could not be reconciled. Their views were different, so it took a long time to bring them together. But they are gradually fixing this. Focusing only on what unites them, they strengthened their solidarity.
  When they started living together, they started experiencing many good things on a daily basis. They became happier. They said that the problems that were bothering them in the past do not seem to matter now. When they face any kind of problem, they stop and gather together and start consulting. They contribute ideas and come up with a solution to the problem. But they were afraid to implement the solution. This is because they suffered a lot during their solitary days and it did not disappear from their minds. You can. They work. They have the capacity. But fear and lack of winning mentality made it hard for them. At this time, the big and fat ants called a meeting again and decided to discuss.
The agenda of their meeting was "How can we solve the problems we face and live a successful life?" It was. An ant, who was leading the discussion from the front, gave a broad explanation of the agenda. He said, "We have lived a life full of temptations due to ignorance and ignorance. There are many things that can be solved, but he tried to pass us and killed us. Now we come to unity. This is our right and good deed. But no matter what happens after this, it shouldn't bother us. This is why it is so important for us to come together. So let's all give ideas and implement today's decision without needing to reconvene." He started looking at the others. Much thought arose. They exchanged pleasantries. An elderly ant raised his hand when the chairman was about to end the agenda of the meeting.They said, "All of us can live by giving solutions to our problems in the way we have discussed now." But I don't think it's enough to just know the solutions. In addition, we must remove doubt from within so that we can use the potential within us. We must get rid of the evil spirit of defeat and believe that we will overcome everything. Otherwise, we will be afraid of tomorrow. Fear does not bring solutions. We must make the motto of our lives, "We shall not doubt, we shall overcome." They said with emotion. They all applauded. They all accepted and agreed to implement and ended their meeting.
  Starting from this day, the ants united and started working miracles. Together they traverse seemingly insurmountable paths. Something as difficult as a river to cross together, but they will cross it. If they enter a very steep place, they will get stuck and no one will come out. If dust falls on them, they will come out with wisdom and wisdom. A bully animal like a lion will lose its ability together. They made a song called "Don't doubt we will win" and they all went through many problems together with a winning spirit. And yet they shall pass.
  And boy, if we have a union of ants, we can do anything. Otherwise, we will only be exhausted."
       And in the book of Proverbs 6:6, "Go to Gebre Gandan, you greedy one." And consider her ways and be wise." I thought of being wise, thinking of the words of Solomon.
  This ant story my father told me is very instructive. It has many important points especially for us Ethiopians. It is a story where I realized how much success togetherness can make us. There is greatness in union. The scattered ants were nothing. But later, when they started living together in love, they exchanged ideas and became successful. For this, the word "Do not doubt, we will win" played an equal role with their addition.
   We should not lose the transcendence of the words by taking this "Do not doubt, we will win" speech of the Prime Minister as any of his speeches. This word to live prosperously tomorrow. We desperately need to get out of our current predicament. If ants can use this powerful word and live better today than yesterday, it is not difficult to imagine how much we humans can use it.
All who have used this powerful word have become great. They have achieved the seemingly impossible. Gone are all the seemingly insurmountable times of trouble. Today, the highly civilized countries faced many complex problems. They overcame this problem by using the bully words "Don't doubt, we will win". I am able to say this not because I have found evidence of their direct use of this word, but because I have no doubt that this is the secret of their victory.
We, the Ethiopians, rose up in the spirit of victory centuries ago and made history. To destroy our culture. Shame on the invading force that came to destroy our faith. The main secret of our success in defeating this Italian invasion force is that we are able to stand up. The vast difference between the Italian army and the Ethiopian army is beyond words. They used very modern weapons. And our fathers were insignificant from their point of view. But there was no doubt in the minds of the Ethiopian patriots that they would win. When they marched from all parts of Ethiopia to Adwa, they had no doubt that they would lose. Their modern weapon is their winning mentality. This belief in their inner power of victory is their modern weapon. Because they were sure that their modern equipment would not embarrass them; They marched to Adwa with pride and enthusiasm, singing their unity song together. Our forefathers, the patriots, sent that organized bully to the dust of the Italian army. They defeated this Italian army that came with disdain and escorted them with a cloak of shame and they returned with a song saying "We are proud of our Ethiopia and we are also proud of you".
We need this word right now. That is why the Prime Minister is saying it again and again in every forum. If we all stand together and use this word, there is no reason why we can't be better. Together we support each other. If we believe with full faith and work with a winning spirit, we can find the solution to our problem in an easy way.
  The biggest mistake we have made so far is that we all did not work together in a winning spirit. As a result, we paid a heavy price. We have already become a laughing stock in many of them. But after this, we have to leave this ignorance and work for the future generation.
  This is why I say that we should make the Prime Minister's speech the guide of our lives. For any problem we face as individuals, we must say "I will win without doubt" and for any problem we face as a team and as a country, we must stand up saying "we will win without doubt".

  Bamlaku abebaw ,(from the village of abajifar, jimma)


key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post