“ሀገር የምታድገው በቅብብሎሽ ነው፡፡”
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ
አንድ ደስ የሚል የስፖርት ውድድር አለ፡፡ ይህ የስፖርት ውድድር በሁሉም ሀገር በሚባል ደረጃ የሚዘወተር ነው፡፡ ውድድሩ አስተውሎ ለተመለከተ አንድ የሚረዳው ሚስጥር አለ፡፡ ይህ ሚስጥር በስፖርቱ ሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በዓለም የወድድር ሜዳ ላይም እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል የሚያስረዳ ነው፡፡ በዚህ ውድድር ውስጥ አንድኛው አጠር ያለች ዱላ ነገር ይዞ ይነሳል፡፡ ይሮጣል፡፡ ከፊት ለፊቱ ደግሞ አንድ ለማሸነፍ የጓጓ፤ ስኬት ላይ ለመድረስ የናፈቀ ጓደኛው ይጠብቀዋል፡፡ አስተውለን ከሆነ ቆሞ አይጠብቀውም፡፡ በከፍተኛ ጉጉትና በእልህ እንዲሁም በከፍተኛ ቁጭት ነው የሚጠብቀው፡፡ የዘገዬ መስሎ ከታየው ደግሞ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይቀበለውና ይሮጣል፡፡ በተመሳሳይ ከፊት ለፊቱ አንድ እንደእርሱ ለማሸነፍ የቸኮለ ጓደኛውን ያገኘዋል፡፡ እርሱም በከፍተኛ ትጋት በከፍተኛ ቁጭት እየተዘጋጀ ይጠብቀዋል፡፡ የያዘውንም ዱላ ተቀብሎ ይሮጣል፡፡ አሁንም ይሮጣል፡፡ በመጨረሻም ያሸንፋል፡፡
የእዚህ የስፖርት ውድድር ዋናው የማሸነፊያው ሚስጥር በፅናትና በጉጉት እንዲሁም በእልህ ስሜት መቀባበል መቻል ነው፡፡ ቅብብሉ ተራ ቅብብል አይደለም፡፡ ቅብብሉ ሙሉ ሃላፊነት ያለበት ቅብብል ነው፡፡ የተቀባዩ ደካማ መሆን የአቀባዩን ጠንካራነት ያጠፋዋል፡፡ በተባለውና በታሰበው ሰዓት ከታሰበበት ቦታ ለመድረስ እንደገናም አሸንፎ ወርቅ ለማጥለቅ ሁሉም በቅብብሉ ውስጥ የሚሳተፉ አካላት ሁሉም እኩል ተሳትፎ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የአንዱ ስንፍና ለሌላው ይተርፋል፡፡ የለሌላኛው ጠንካራ መሆን ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ ሁሉም ሰነፍ ከሆኑ ክስረት ነው፡፡ ሰነፍ መቀባበል አይችልም፡፡ ሰነፍ መጀመር እንጅ መጨረስ አይችልም፡፡ ሰነፍ ከአዲስ መነሳት እንጅ ከተሰራው ላይ መቀጠል አይችልም፡፡
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ስልጣን በያዙ በትንሽ ወራት ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያመጡ ኩሩ ኢትዮጲያዊ መሪ ናቸው፡፡ እርሳቸው በሀዋሳ ከተማ በተደረገው 11ኛው የኢ.ሕ.ዲ.ግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የተናገሩት ድንቅ ንግግር አለ፡፡ “ ሀገር የምታድገው በቅብብሎሽ ነው፡፡” ነበር ያሉት፡፡ ይህ ንግግር ተራ አይደለም፡፡ የዚህ ንግግር ትርጉሙና አንደምታ ብዙ ሊያስብለን የሚችል ነው፡፡ ብቻውን አንድ መፅሐፍ መሆን የሚችል ሀሳብ የያዘ ቢሆንም እኔ ግን ቀንጨብ አድርጌ አቀርበዋለው፡፡
ለአንድ ሀገር ብልፅግና የትውልድ ቅብብሎሽ የግድ ያስፈልጋል፡፡ ቅብብሎሽ ከሌለ ባለበት ላይ ብቻ እንደሚረግጥ ተራማጅ ግለሰብ ነው የምንሆነው፡፡ የሰው ልጅ ዘላለማዊ አይደለም፡፡ እርሱ ቢበዛ ሀምሳ ከፍ ቢል ደግሞ ሰባ አመት ቢኖር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አንድ ሰው የጀመረውን ስራ ወይም ሌላ ነገር ከቻለ እርሱ ካልቻለ ደግሞ ሌላ ሊቋጭለት የሚችል ሰው ያስፈልገዋል፡፡ ቅብብሎሽ ማለት ምንም ማለት ሳይሆን የተፈጥሮ ህግ የሆነና ዓለም እንድትቀጥል ሲባል የሚተገበር ከአምላክ የተሰጠን አደራ ነው፡፡ አዳም በመጀመሪያ ከአፈር ሲሰራ አምላኩን እያመሰገነ ተፈጥሮን እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ ነው፡፡ ከሄዋን ጋር በመሆን ልጅ እንዲወልዱ ሲደረግ ቅብብሎሽ እንዳለ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ የሚወለደው ልጅ የቤተሰቡን ስራ ያስቀጥላል፡፡ ከዚያ የጀመረ መቀባበል ከአሁኖቹ ትውልዶች ደርሶ እያየን ነው፡፡ ከዚህም ዘመን አልፎ ወደ ፊት ይቀጥላል፡፡ እኛም ይችን ዓለም ተቀብለን አሳምረንና አስውበን ለሚቀጥለው ትውልድ የማቀበል ግዴታ አለብን፡፡
ቀደምት አባቶቻችንን ብንመለከት አሁን ያለንበትን ዓለም ሰርተውና ጠብቀው እንዳስረከቡን እናስተውላለን፡፡ ለምሳሌ እሳትን ፈጥረው ለሚቀጥለው ትውልድ አቀበሉ፡፡ የሚቀጥለውም ትውልድ እሳትን ተቀብሎ አሳትን ተጠቅሞ ሌላ የጎደለውን ለመሙላት ሲል ፈጥሮ እርሱም ተጠቅሞ ለሚቀጥለው ትውልድ አስረከበ፡፡ አሁን ላይ ያለን ትውልዶች ይህንን ውብና በብዙ ነገር የተሞላ ዓለምን የተቀበልነው በዚህ መልኩ ሁሉም የሚጠበቅበትን አያደገ ስለመጣ ነው፡፡ እኛም ያለፈው ትውልድ የሰራውን ተቀብለን ጠብቀንና ተንከባክበን ለሚቀጥለው ትውልድ የማስረከብ ከፍተኛ አደራ አለብን፡፡
የተባረከ ትውልድ የተቀበለውን ጠብቆና ተንከባክቦ እርሱም የድርሻውን ጨምሮበት ለሚቀጥለው ያስረክባል፡፡ ግድ የሌለው ትውልድ ደግሞ የያዘውን ብቻ ጠብቆ ምንም ሳይጨምርበት ደግሞም ምንም ሳያጎድልበት ለሚቀጥለው ባላደራ ትውልድ ያስረክባል፡፡ የተረገመ ትውልድ ደግሞ የተቀበለውን አደራ ሳይጠብቅ የእርሱን ድርሻም ሳይጨምርበት፤ ይባስ ብሎ አፍርሶና አበላሽቶ ለሚቀጥለው ትውልድ ይሰጣል፡፡ ይሄ ትውልድ ሀገርን የሚበድል ትውልድን የሚገድል ነው፡፡ ከእዚህ አንፃር እኛ ኢትዮጲያኖች ከየትኛው ዓይነት ትውልድ እንደምንመደብ እናተው አስቡት፡፡ ምክንያቱም ትላንት ምን ያህል ትልቅ እንደነበርን እና ዛሬ ደግሞ ምን ያህል ትንሽ እንደሆንን ማሰብ ስለሚቻል፡፡ ለዚህ ሁሉ መነሻ ምክንያት የነበረው ትውልድ ሀገርን ሲቀባበል በሀላፊነት ስሜት ባለመሆኑ ነው፡፡ ያማ ባይሆን እና ሁሉም ካለው ላይ እየጨመረ እያሳመረና እያስዋበ ቢሄድ ኖሮ ይች ሀገር ዛሬ ካለችበት ደረጃ ባልደረሰበች ነበር፡፡
ትውልድ የመቀባበልን የጨዋታ ህግ ማወቅ አለበት፡፡ ሀገር የምትበለጽገውና ስኬታማ መሆን የምትችለው ዜጎቿ መቀባበል ሲችሉ ነው፡፡ ሲቀባበሏት ደግሞ በፍፁም የሀላፊነት ስሜት መሆን እንዳለበት ማወቅ አለባቸው፡፡ ዛሬ ለመሄድ የምንጎመጅባቸው ሀገራት ከትንሽ አመታት በፊት እኮ እንደአሁኗ ኢትዮጲያ የነበሩ ናቸው፡፡ እንዲበለጽጉና እንድንሳሳላቸው ያደረጋቸው በሀላፊነት ስሜት የሚቀባበል ትውልድ ስላፈሩና ስላላቸው ጭምር ነው፡፡ ልክ እንደ ዱላ ቅብብሎሽ የጨዋታ ህግ አንደኛው እስከተወሰነ ምዕራፍ ይመጣና የሚቀጥለው ትውልድ ደግሞ ልክ ከኋለኛው ተቀብሎ የሚችለውን ያህል ወደ ፊት ይወስዳታል፡፡ ወደ ኋላ የሚመለስበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ የሚቆምበትም እንዲሁ ምክንያት የለውም፡፡ ያቅሙን ግን ወደ ፊት ይሮጣል፡፡ ይሄ ነው ሀገርን የማበልጸጊያው ሚስጥር፡፡
…….ይቀጥላል
.........................................................................................................................................................
"A country grows by relaying."
Prime Minister Dr. Abiy Ahmed
There is an interesting sports competition. This sports competition is frequent in almost every country. The competition has a secret that will help one who observes it. This secret explains how we can win not only on the sports field but also on the world stage. In this competition, the one with the shorter stick takes off. He runs. In front of him, he is eager to win. A longing friend waits for him to achieve success. If we notice, he does not stand and wait. He waits with great enthusiasm and patience. If he seems to be late, he turns back and runs away. Likewise, he finds a friend in front of him who is as eager to win as he is. And he is waiting for it, preparing with great diligence and great patience. He takes the stick he is holding and runs. It still runs. In the end, he wins.
The main secret of winning this sports competition is to be able to accept it with perseverance and enthusiasm. The relay is no ordinary relay. The relay is a fully responsible relay. Weakness of the receiver destroys the strength of the receiver. In order to reach the intended place at the intended time and win again, all parties involved in the relay must have equal participation. The laziness of the one is spared for the other. Another's being strong alone is not worth it. If they're all lazy, it's a waste. A lazy person cannot accept. A lazy person cannot start but finish. A lazy person can't move on from what he has done but start anew.
Prime Minister Dr. Abiy Ahmed is a proud Ethiopian leader who has brought great changes in the few months he has been in power. There is a wonderful speech he gave at the 11th EHDG organizational meeting in Hawassa city. "A nation grows by relaying." They said it was. This speech is not ordinary. The meaning and meaning of this speech can make us think a lot. Although it contains an idea that could be a book by itself, I will present it as a thumbnail.
For the prosperity of a country, generational transmission is necessary. Without a relay, we become a progressive individual who just steps on the ground. Humanity is not eternal. If he was fifty at most, he would have lived seventy years. For this reason, if a person is able to do the work or something else that he has started, he needs someone else who can finish it. Relay does not mean anything, it is a law of nature and a mandate given to us by God to keep the world going. When Adam was first created from the soil, he thanked God for protecting and caring for nature. It is reasonable to think that there is a relay when they are made to have children together with Eve. The child to be born will continue the work of the family. We are witnessing the reception that started then from the present generations. It will continue beyond this era. We also have a duty to accept this world and make it beautiful and beautify it and pass it on to the next generation.
If we look at our ancestors, we will notice that they created and preserved the world we are in today. For example, they created fire and passed it on to the next generation. The next generation received fire and used asat to fill in another, and he used it and handed it over to the next generation. Our current generation has accepted this beautiful and abundant world because it has not grown up in this way where everyone is expected. We also have a great responsibility to accept what the previous generation has done, preserve it and take care of it and hand it over to the next generation.
A blessed generation preserves and takes care of what it has received and hands it on to the next one, including its share. A careless generation will keep only what it has and hand it over to the next generation without adding anything to it or subtracting anything from it. And a cursed generation who did not keep the trust he received and did not add his share to it. Worse, he breaks it down and spoils it and gives it to the next generation. This is the generation that abuses the country and kills the generation. From this point of view, let's imagine what kind of generation we Ethiopians belong to. Because it is possible to think how big we were yesterday and how small we are today. The root cause of all this was that he did not have a sense of responsibility when welcoming his native country. If it wasn't for Yama and if everyone kept on beautifying and beautifying what they have, this country would not have reached the level it is today.
A generation must know the rules of the game of reception. A country can prosper and be successful when its citizens are welcoming. And when they welcome her, they should know that it should be done with a sense of responsibility. The countries we are planning to go to today were like Ethiopia a few years ago. It is also because they have produced and have a generation that welcomes them with a sense of responsibility. Like a baton relay game, the rule of the game is that one reaches a certain point, and the next generation carries it forward as much as it can receive from the last. He has no reason to hold back. It has no reason to stop either. But he will run forward. This is the secret of the development of the country.
...to be continued
Bamlaku Abebaw (jimma, from abajifar village)