ከእኛ ጋር ስለሆነ ነው
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ
እኛ ኢትዮጵውያን ልንኮራበት የሚገባ ብዙ ነገር አለን፡፡ ከእነዚህ መካከል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀግን ነን፡፡ የሰው ልጅ መገኛ ነን፡፡ “አንገዛም” ብለው ነፃነታቸውን ያስጠበቁ የጀግኖች ልጆች ነን፡፡ ብዙ ማለት እንችላለን፡፡ ትኩረት ያልሰጠነው ግን ደግሞ የታደልነው በአብዛኛው እኛ ኢትዮጵያወያን አማኝ መሆናችን ነው፡፡ አማኝ የሆነ ህዝብ የብዙ መልካም ነገር ምንጭ ነው፡፡ እንደ ሀገር ይህንን እንደቀላል ነገር ተመልክተነው ይሆናል እንጅ ብዙ ተጠቅመንበታል፡፡ ይህ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ እምነት አልባ የሆኑትን ሀገራት መመልከትና ማጤን
ተገቢ ነው፡፡
መልካም የሆነ እምነት በጣም ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ መልካም እምነት ጠንካራ ያደርጋል፡፡ መልካም እምነት ከጭንቀትና ከውጥረት ይከላከላል፡፡ እምነት አዛኝ እንድንሆን፣ ከእንሰሳት በተሻለ ሩህሩህ ልቦና እንዲኖረን፣ በጥቅሉ መልካም እንድናደርግ ይገፋፋናል፡፡
ሁለት ሰዎችን ብንወስድና አንደኛውን ስለፈጣሪ ህልውና እና ገዥነት እያስተማርነውና የተፈጥሮንም ስርዓት ከዚህ አንፃር እያስቃኘን ብናሳድገው፤ ሌላኛውን ደግሞ ስለእምነትና ሀይማኖት ሳናስተምረው ብናሳድገው በሁለቱ መካከል የሚኖረው ልዩነት በእጅጉ የሰፋ ነው የሚሆነው፡፡
ስለፈጣሪው እሰማ ያደገው ልጅ ሃማኖተኛ ሆኖ ያድጋል፡፡ ለዚህም በምግባሩ የታነፀ ይሆናል፡፣ አስተዋይ ይሆናል፡፡ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለሌሎቹ ፍጥረታት የሚያስብ ይሆናል፡፡ ትግስተኛ፣ ታዛዥ፣.... ወዘተ ይሆናል፡፡ በተቃራኒ ስርዓት ያደገው ልጅ ደግሞ ፈጣሪን የማያውቅ ቅዱስ ቁራንንም ሆነ መፅሐፍትን የማያነብ ከመሆኑ የተነሳ የሰው ልጅ ሊኖረው የሚገባውን ሰዋዊ ባህሪ፣ እይታና አመለካከት የሌለው ይሆናል፡፡ የጭካኔ በትሩን ለማሳረፍ የፈጠነ፣ ለራሱ ብቻ የሚያስብ ስስታም፣ ንግግሩ የማይመች፣ እሞታለው ብሎ የማያስብ አረመኔ፣ እኖራለው ብሎ ለነገ የማይል ይሆናል፡፡ ትውልድ የሚሞተው ሀገርም የምትካደው እነዚህን መሰል ሰዎች ካፈራች ነው፡፡
አሁን በኢትዮጲያ ላይ እያየን ያለነው እነዚህን ነው፡፡ ትላልቅ ሰዎች ሳይቀሩ “እምነት አለን፤ ሃይማኖተኛ ነን” ብለውን ምግባረ ከንቱ ሆነው እያየናቸው ነው፡፡ ከላይ የዘረዘርናቸው ሰዋዊ አመለካከትና ባህሪ የሌላቸው ሆነው አይተናቸዋልም፡፡
በአምላክ ህልውና አምነው የሚኖሩ ለእርሱም መገዛትን ዘወትር የሚለማመዱ ሰዎች ከክፋት የራቁ ይሆናሉ፡፡ በመልካም ምግባር የደመቁ ሆነው ይታያሉ፡፡ በፍቅርና በመተሳሰብ መኖር የሚችሉ ይሆናሉ፡፡
እነዚህ ፈርሃ ፈጣሪ የተቸሩ ሰዎች በእውቀትና በጥበብ የከበሩ በማስተዋልም ረቀቅ ያሉ ስለሚሆኑ በግለሰብም ሆነ በሀገር ትክክለኛ ለውጥ ይኖራል፡፡
በነገራችን ላይ ለውጥ የሚገለፀው ብዙ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ስለበዙ፣ ሰፋፊ በመንገዶች ስላሉ፣ ውብ የሆኑና የሚያምሩ ቢሮዎች፣ የመኪና ጋጋታ ስለታዬ፣ …ወዘተ አይደለም፡፡ ምክንያም ለውጥ ከውስጥ ተፈጥሮ ወደ ውጭ ሲወጣ እና ሲታይ ነው፡፡
በአንድ ሀገር ለውጥ አለ የሚባለው የሰው ልጅ በማህበራዊ ኑሮው ከግላዊነት ወጥቶ ስለ ሀገርና ስለወገን ሲጨነቅ፣ በኢኮኖሚ ደግሞ የተሻለና የሚፈልገውን ማድረግ የሚችልበትን አቅም ሲገነባ፣ በስነ ልቦና ደግሞ “እችላለው” ብሎ የሚያምን ጠንካራ መሆን ሲችል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቁ መሰረቱ እምነት ያለው ሲሆን ነው፡፡ የሃይማኖት መነሻው እምነት ነው፡፡
እንደሚታወቀው በአለም ላይ ብዙ ሃይማኖቶች አሉ፡፡ በእኛ ሀገርም እስልምና እና ክርስትናን ማዕከል ያደረጉ በርከት ያሉ የሃይማኖቶች ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህ ሃይማኖቶች መሰረታቸው እምነት ያለው ዜጋ ስላለ የተገኙ ናቸው፡፡ እነእርሱም ዋና ግባቸው ሰውን ሰው አድርጎ ከፈጣሪው ጋር ማገናኘትና በስርዓት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ሰውን የእንስሳ ባህሪ እንዲኖረውም ማድረግ ስለሚቻል ማለት ነው፡፡
የሰውን ልጅ ሰው ሊኖረው የሚገባውን ባህሪ፣ አመለካከት፣ አረዳድ፣ አተያይ፣ አነጋገር፣ ….ወዘተ እንዲኖረው ካደረግነው የብልፅግና መሰረት እንደጣልን ማወቅ አለብን፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው ሰው መሆናችንን እንድንረሳ፣ ለአምላካችን እንዳንገዛ፣ ለቤተሰብን እና ለሀገር ክብር እንዳይኖረን፣ የመፍጠርና የመከወን አቅማችንን እንዳንጠቀም፣ የመበልፀግ ፍላጎታችን ካጠፋብን፣ ተመልካችና ተመፅዋች እንድንሆን ከገፋፋን፣……..ወዘተ ከሆንን ወደ ውድቀት እየተጓዝን እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል፡፡
አሁን በየትኛው ላይ ነን?
መንግስት የዜጎቹን የነገ አኗኗር፣ የነገ አስተሳሰብ፣ የነገ እንቅስቃሴያቸው ምን ሊመስል እንደሚችል ቀድሞ መረዳት አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ እያንዳንዱ ሰው የሚከተለውን ሃይማኖት ይዘቱ እና አስተምሮው ምን እንደሚመስል ማወቅ አለበት፡፡ ሰዎች ዛሬ የተማሩትን ነው ነገ ላይ በተግባር የሚያንጸባርቁት፡፡ ዛሬ የሰሙትን ነው ነገ የሚተገብሩት፡፡ ዛሬ ያነበቡትን ነው ነገ የሚኖሩት፡፡ የነገዋ ኢትዮጲያ ማለት ዛሬ በወጣቱ አዕምሮ ውስጥ የሚዘራው ዘር ውጤት ናት፡፡ ዛሬ ትውልዱ የሚሰበከው፣ የሚያነበው፣ የሚሰማው፣ የሚያየው መልካም ከሆነ ያለምንም ጥርጥር የነገዋ ኢትዮጲያ እንደመልካም ቤተሰብ የሚደጋገፉ፣ የሚተባበሩና “አንተ ለእኔ እኔ ላንተ” የሚባባሉ ህዝቦች መኖሪያ ትሆናች፡፡ የዚህ መሰረት ደግሞ የሃይማኖት ተቋማት ናቸው፡፡ ስለዚህ መንግስት እንደመንግስት መከታተል ግዴታው ይሆናሉ፡፡ በተቃራኒ ካሰብነውም የሚሆነው መልካም ያልሆነ ነው፡፡
ትውልዱ ሰውነትን በሚገነባ ሀገርን በሚያስቀድም ሃይማኖት ውስጥ ማደግ አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ በሃይማኖት ውስጥ ያለፉ እና ሰው ሆነው አርዓያ መሆን የሚችሉ መሪዎች ያስፈልጉናል፡፡ ሰው መስለው ግን የሰው ስብዕና ሳይኖራቸው ሰውን ለመምራት የሚያስቡ ሰዎች የተሻለ ትውልድ ማፍራት አይችሉም፡፡ በየትኛውም ደረጃ ያሉ መሪዎች እንደ እንስሳ ለግላቸው የሚያስቡ ከሆኑ ሀገርን ማሻገር አይችሉም፡፡ መልካም ስብዕና ገንብተው ለሁሉም ማሰብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ እንደ ሰው ማዘን የሚችሉ፣ ትርፍ ለሆነ ነገር የማይሽቀዳደሙ፣ ሰውንም ፈጣሪንም የሚፈሩና የሚያከብሩ ሰው የሆኑ ሰዎች መሪ ከሆኑ ትውልዱም በዛው መስመር የሚሄድ ይሆናል፡፡ ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ፈጣሪን ደጋግመው የሚያመሰግኑ ሃየማኖተኛ ሰው መሆናቸውን ድርጊታቸው ይመሰክራል፡፡ ሁሌም የመልዕክታቸው ማሳረጊያ እንኳን የፈጣሪ ስም ነው፡፡ የትኛውንም ስራ በሚያስጀምሩበት ጊዜ በፈጣሪ ስም ባርከው ነው፡፡ ለስኬት እንዲበቃም በህዝብ ፊት ፀሎት አድርገው ነው፡፡ ምንም እንኳን በፈተና ውሰጥ ያሉ ቢሆንም ሃሳባቸው ወደ ተግባር እየተቀየረ ፍሬ እያየን ነው፡፡ የእርሳቸው እንደዚህ ማድረግ ሰዎች ሃይማኖትን እንዲጠብቁ እና በሃይማኖት ጥላ ስር እንዲሆኑ ያግዛል፡፡ እድልም ይሰጣል፡፡
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ሃይማኖተኛ መሆናቸውን የሚያሳዩ በዙ የአደባባይ ንግግሮች፤ የፓርላማ ማብራሪያዎች፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎች፣ የጽሁፍ ማሳረጊያዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት የውጭ ዜጋ ለጠየቃቸው ጥያቄ የሰጡትን መልስ እንመልከት፡፡
“....ከሰሞኑ አንድ የውጭ ሀገር ወዳጅ ነበረኝና በርከት ያሉ ፕሮጀክቶችን ካሳየውት በኋላ እንዲህ ሲል ጠየቀኝ፡፡
“በስራዎቻችሁ እጅግ በጣም ተደንቂያለው ተደምሚያለው፡፡ ግን አንድ ጉዳይ በጣም ያሰጋኛል፡፡ “ይህን ሁሉ ገንዘብ ከየት አምጥታችሁ ነው?” መባላችሁ አይቀርም፡፡ አሁን ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ “ ገንዘቡ ከየት እየመጣ ነው ይሄ ሁሉ ስራ የሚሰራው?” የሚል ስለሆነ ለመልሱ ተዘጋጁ አለኝ፡፡ እኔም እንዲህ አልኩት “አይ ጀምሮ የሚያስጨርሰው ከእኛ ጋር ስለሆነ ነው፡፡” ብየዋለው፡፡”
( የጣና በለስን የስኳር ፋብሪካ ባስመረቁ ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ)
እርሳቸው እንደ አንድ መሪ ለዚህ ጥያቄ ብዙ መልስ መስጠት ይችሉ ነበር፡፡ “ብልፅግና ፓርቲ ገና ከጅምሩ ለውጥ እያሳየ ያለና ቃሉን ወደ ተግባር እየለወጠ ያለ ጠንካራ የህዝብ ልጆች ስብስብ ነው፡፡ እና ገና ከዚ በላይ ማሳየት ይችላል፡፡” ማለት ይችሉ ነበር፡፡ ወይም ደግሞ “የገነባነው ጠንካራ መዋቅር እና የህዝብ አደረጃጀት እንዲሁም አሳታፊ ፖሊስ ይህንን ስራ በአጭር ጊዜ እንድናከናውን እረድቶናል፡፡” ብለው የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነውን ፈጣረን የዘነጋ ንግግር ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ የጠነከረ የህዝብ አደረጃት፣ የተማረ አመራር ወይም የጠነከረ ኢኮኖሚ ብቻውን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ካለ ፈጣሪ እርዳታ በስተቀር፡፡ ይህንን ሁላችን ማወቅ ያለብን እውነት ነው፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ
.......................................
.......................................................................................
Because it is with us
P.M.Dr abiy ahimed
We Ethiopians have a lot to be proud of. Among these, we are rich in natural resources. We are the origin of humanity. We are the children of heroes who protected their freedom by saying "we will not rule". We can say a lot. What we didn't pay attention to, but what we are blessed with is that most of us are Ethiopian believers. A believing nation is the source of many good things. As a nation, we may have taken this for granted, but we have taken advantage of it. To see if this is true, it is worth looking at and considering the faithless nations.
Good faith has many benefits. Good faith makes strong. Good faith protects against stress and anxiety. Faith prompts us to be compassionate, to be more compassionate than animals, to do good in general.
If we take two people and raise one of them while teaching him about the existence and rulership of the creator and exploring the natural order from this point of view; And if we raise the other one without teaching him about faith and religion, the difference between the two will be much wider.
A child who grows up hearing about the Creator will grow up to be religious. For this, he will be educated in his behavior, he will be intelligent. He will care not only for humans but also for other creatures. He will be patient, obedient, etc. A child who grows up in the opposite system does not know the Creator and does not read the Holy Qur'an or books, so he does not have the human behavior, vision and attitude that a human being should have. He who is quick to lay down his cruel rod, who thinks only of himself, is a coward, whose speech is awkward, a savage who does not think that he will die, who does not say that he will live for tomorrow. A generation dies and a country is denied if it produces such people.
This is what we are seeing in Ethiopia now. Even great men say, "We have faith; "We are religious" and we are seeing them as useless. We do not see them as lacking the human attitude and character that we have listed above.
People who believe in God's existence and practice submission to Him will be far away from evil. They appear to be distinguished by good conduct. They will be able to live in love and compassion.
These people who create peace will be blessed with knowledge and wisdom and will be far-reaching in their understanding, so there will be real change in both the individual and the country.
By the way, change is not defined by the number of skyscrapers, wide roads, beautiful offices, cars, etc. The reason is that change comes from the inner nature and becomes visible.
It is said that there is a change in a country when a human being gets out of privacy in his social life and cares about the country and his people, economically when he builds the capacity to do better and what he wants, and psychologically when he is able to be strong enough to believe "I can". The biggest foundation for this is faith. The root of religion is faith.
As you know, there are many religions in the world. In our country, there are many religious institutions centered on Islam and Christianity. These religions are based on the fact that there is a citizenry that believes. Their main goal is to connect man to the Creator and make him live in order. It means that it is possible to make a person have the behavior of an animal.
We should know that if we make a human being have the behavior, attitude, understanding, perspective, speech, etc., we have laid the foundation of prosperity. But on the contrary, we need to know that we are on the way to failure if we forget that we are human beings, do not submit to our God, do not have respect for family and country, do not use our ability to create and succeed, if our desire to get rich destroys us, if we become spectators and rebels, etc.
Which one are we on now?
The government must first understand the citizens' lifestyle, thinking, and activities of tomorrow. For this reason, each person should know what the content and teaching of the following religion is like. What people learn today is what they will put into practice tomorrow. What they hear today is what they will practice tomorrow. What you read today is what you will live tomorrow. The Ethiopia of tomorrow is the result of the seeds planted in the minds of the youth today. If what the generation preaches, reads, hears, and sees is good today, the Ethiopia of tomorrow will undoubtedly be home to people who support each other like a good family, cooperate and say "you for me and me for you". The basis of this is religious institutions. Therefore, it will be the duty of the government to follow up as a government. If we think otherwise, it is not good.
The generation must grow up in a religion that builds the body and puts the nation first. For this, we need leaders who are experienced in religion and who can be role models as human beings. People who pretend to be human but do not have human personality and think to lead people cannot produce a better generation. If leaders at any level are as self-centered as animals, they cannot transcend the nation. They should develop a good personality and be able to think for everyone. If the leaders are people who are human beings who can grieve like human beings, who do not compete for profit, who fear and respect man and the Creator, then the generation will follow the same path. Prime Minister Dr. Abiy Ahmed
His actions testify that PM Dr. Abiy Ahmed is a religious person who repeatedly praises the Creator. Even their message header is always the creator's name. When you start any work, you bless it in the name of the creator. They prayed in front of the public for success. Although they are under trials, we are seeing the fruits of their ideas being turned into actions. His doing so helps people to maintain religion and stay under the shadow of religion. It also gives an opportunity.
PM/Dr. Abiy Ahmed's many public speeches showing that he is religious; There are parliamentary briefings, press releases, written submissions. For example, let's look at the answer they once gave to a question asked by a foreigner.
"...I recently had a foreign friend and after showing him several projects, he asked me this.
“I am very impressed with your work. But one issue really scares me. "Where did you get all this money?" You will be called. Now the next question is "Where is the money coming from to do all this work?" He told me to prepare for the answer. I said to him, "No, it's because he's with us." I called it."
(Taken from what he said during the inauguration of Tana Beles sugar factory)
As a leader, he could have given many answers to this question. "The Prosperity Party is a strong group of people who have been making changes since the beginning and are turning their words into actions. And he can show even more than that.” They could say. Or, "The strong structure and public organization we have built, as well as a participatory police force, have helped us accomplish this task in a short period of time." It was possible to make a speech that created and forgot the owner of everything. A strong public organization, an educated leadership or a strong economy alone cannot do anything. Except with the help of a creator. This is a truth we all need to know.
It will continue.
Bamlaku Abebaw, Jimma. from abajifar village