part two //“አሸናፊዎች ለሁሉም ችግር መልስ ያያሉ፤ተሸናፊዎች ደግሞ ለሁሉም መልስ ችግር ያያሉ” ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ// Prime Minister Dr. Abiy Ahmed said, "Winners see answers to all problems; "Losers see problems in every answer."

 


ከባለፈው የቀጠለ ነው፡፡

ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ስለአሸናፊና ተሸናፊዎች ሲናገሩ “አሸናፊዎች ለሁሉም ችግር መልስ ያያሉ፤ ተሸናፊዎች ደግሞ ለሁሉም መልስ ችግር ያያሉ” ብለዋል፡፡ ይህንንም የተናገሩት ከኢትዮጵያውያን የጥበብ ሰዎች ጋር በነበራቸው የውይይትና የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡ በእርሳቸው ንግግር ውስጥ አንድ መሰረታዊ ነጥብ አለ፡፡ ይህም ለችግራችን የምንሰጠው መልስ እና ለመልሳችን የምንሰጠው እይታ አሸናፊም ተሸናፊም ሊያደርገን ይችላል፡፡ በህወታችን ብዙ ዓይነት ችግር ይገጥመናል፡፡ ለችግራችን የምንሰጠው መፍትሄ ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡ ለምንሰጠው የችግራችን መፍትሄ ግን ችግር ልናይለት አይገባም፡፡ምክንያቱም የመፍትሄውን ችግር የምናይ ከሆነ ወደ ችግሩ እንጅ ወደ መፍትሄው መቅረብ አንችልም፡፡ ይስበናልና፡፡ እንደዚህ ማድረግ እችል ነበር ግን እንደዚህ አይነት ነገር አለ፡፡

ይቺ “ግን “ የምንላት ቃል ቀጣይ ልናደርግ የሚገባንን ተግባር እንዳናደርግ የአቅም ውስንነት እንዲገጥመን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አላት፡፡ ይህ ደግሞ ተሸናፊ እንድንሆን ዕድል እናገኛለን ማለት ነው፡፡ ከ “ግን” በኋላ ያለውን ሀረግ ብንመለከት “ችግር ” እያየን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ለምሳሌ፤  ከዚህ በታች ያለውን በደንብ መመልከት እንችላለን፡፡

በሀገራችን ብዙ ተሸናፊ ስነ ልቦና ያላቸው ተማሪዎች፣ ነጋዴዎች፣ አስተማሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች….ወዘተ አሉ፡፡ ተማሪዎቹ ውጤታቸው ዝቅተኛ ሲሆን “ በደንብ ማጥናት እችል ነበር ግን ቤተሰቦቼ ስራ ያበዙብኛል”፤ ነጋዴው “ትርፋማ መሆን እችል ነበር ግን ጠላቴ አላንቀሳቅስ አለኝ”፤ አስተማሪው ደግሞ “ውጤታማ ትውልድ መፍጠር ይቻል ነበር ግን የትምህርት ስርዓቱ ችግር አለበት”፤ የመንግስት ተወካዮችና ደግሞ “የህዝባችንን ፍላጎት ማሳካት እንችል ነበር ግን የሰው ሀይልና የበጀት እጥረት ችግር አለብን”፤…ወዘተ፡፡ እንደዚህ ዓይነት አመለካከትና ስነልቦና ያላቸው ሰዎች ችግርን መፍታት አይችሉም፡፡ ችግር መፍጠር እንጅ፡፡

የምናደቃቸው የዓለማችን ሀገራት ዛሬ ከደረሱበት የእድገት ደረጃ የደረሱት ችግር የሚባል ነገር ስላልገጠማቸው አይደለም፡፡ ለችግራቸው የመፍትሄ ሀሳብ የሚያፈልቁ የፈለቀውንም ሀሳብ የሚመረምሩ መርምረውም ወደ ተግባር የሚቀይሩ ጠንካራ ትውልድ በመኖሩ ነው፡፡ ትውልዱ ሁሉም አሸናፊ ላይሆን ይችላል፡፡ በዚህ ትውልድ ውስጥ አሸነፊ ስነ ልቦና ያላቸው ሰዎች ተሸናፊ ከሆኑት ስለበለጡ ሀገራቸው ማሻገር ችለዋል፡፡ ወደ ዛሬ በስልጣኔ ላይ በመሆን መሻገር ችለዋል፡፡

 ወደ እኛዋ ኢትዮጵያችን ስንመጣ ሁላችንም ሀገራችን ተለውጣ ማየት እንፈልጋለን፡፡ ግን የአንድ ሰው እንቅስቃሴ በሀገራችን ለውጥ ላይ ምን ያህል አስተዋፅዖ እንዳለው እንዘነጋለን፡፡ የእኔም፣ የአንተም፣ የአንችም ለግል ችግራችን መፍትሄ በመፈለግ ደፋ ቀና ብለን መፍትሄ ፈልገን ችግራችንን መቅረፍ ስንችል ሀገራችን እየተለወጠች እንደሆነ ማሰብ እንችላለን፡፡ ይሄ ደግሞ አሸናፊ መሆንን እንለማመዳለን ማለት ነው፡፡ የራሳችንን ችግር መቅረፍ ከቻልን ደግሞ የጎረቤትን መቅረፍ እንችላለን፡፡ ቀስ ብለን ደግሞ በቀበሌ ውስጥ ያለውን ችግር ለመቅረፍ እንሞክራለን፡፡ ይሄ ማለት ሀገራችንን በለውጥ ጎዳና ላይ እንድትሄድ እያደረግን እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊ መሆን ይሄ ነው፡፡ አመንም አላመንም ሀገራት የበለፀጉት በዚህ መንገድ እንጅ በሌላ አይደለም፡፡ መንግስት ጠንካራ ስለሆነ አይደለም፡፡

  መንግስት ብቻውን ያለአሸናፊ ሰዎች ምንም ሊያደርግ አይችልም፡፡ ከህዝብ ላይ ግብር ሰብስቦ ደሞዝ እንዲከፈል፣ የመሰረት ድንጋይ እንዲቀመጥ፣ የተለያዩ አስፈላጊ ነገሮችን ለማከናወን ጥረት ሊያደርግ ይችላል፡፡ በዛም አለ በዚህ እነዚህ ሁሉ ሊከናወኑ የሚችሉት በሰው ነው፡፡ ሰው  ደግሞ በአሸናፊነት መንፈስ ለሀገራቸው ተቆርቁረው የማይሰሩ ከሆነ ኪሳራ ነው፡፡ ለዚህ ነው በእኛ ሀገር በየቦታው ያለተቋጬ ግንባታዎችና ጥራት የጎደላቸው መሰረተ ልማቶች የምንመለከተው፡፡ ምክንያቱም የሚሰሩት ሰዎች በአሸናፊነት መንፈስ ለውጥ እምዲመጣና ችግር እንዲቀረፍ ስላልጣሩ የሆነ ነው፡፡ ጠጋ ብሎ “ለምን እንደዚህ ሆነ?” ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቃቸው በሚሰጡት መልስ ውስጥ ችግር እንሰማለን፡፡ ምክንያቱም ተሸናፊ ሲለሆኑ፡፡

ኢትዮጲያን እንለውጥ ካልን ከራሳችን ጀምረን ለሚገጥመን ችግር ትክክለኛውን መፍትሔ እምፈልግ፡፡ “የኔ ችግር መፍትሄ የለውም፡፡” የሚባል የደከመ አስተሳሰብ ካለ በቶሎ ከአዕምሮ ውስጥ እንዲወጣ መደረግ አለበት፡፡ ይሄ የተሸናፊ ሰው የመሸነፊያ መንገድ ነው፡፡ ያገኘነውን ትክክለኛ መፍትሄ በመጠቀም ችግራችንን እናሽሽ፡፡


ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ከአባጅፋር መንደር:

...................................................................................................................................................

....................................................................................................................................................



It is a continuation of the past.


Speaking about winners and losers, Prime Minister Dr. Abiy Ahmed said, "Winners see answers to all problems; "Losers see problems in every answer." He said this in a discussion and consultation forum with Ethiopian artists. There is a basic point in his speech. This answer to our problem and the perspective we give to our answer can make us a winner or a loser. We face many problems in our life. Our solutions to our problems must be right. But we should not see a problem in the solution of our problem, because if we see the problem of the solution, we cannot approach the solution. Because it attracts us. I could do it like this but there is such a thing.

This word "but" has a great contribution to make us face the limitations of our ability to do what we should do next. And this means that we will have the chance to be a loser. If we look at the phrase after "but", we will understand that we are seeing a "problem". For example; We can take a closer look at it below.

In our country, there are many students, businessmen, teachers, administrators, etc. who have a losing mentality. "I could study well, but my family makes me busy" when the students' grades are low; The merchant said, "I could be profitable, but my enemy told me not to move." And the teacher said, "It was possible to create an effective generation, but the education system has problems"; Government representatives and also "we could achieve the needs of our people, but we have a problem of lack of human resources and budget"... etc. People with such attitude and mentality cannot solve problems. Instead of causing trouble.

It is not because the countries of the world that we are crushing have reached the level of development they have reached today because they did not face any problems. It is due to the existence of a strong generation who come up with ideas for solutions to their problems, who investigate the idea and turn it into action. The generation may not be all winners. In this generation, people with a winning mindset have outnumbered the losers. They were able to cross over to today's civilization.

  When it comes to our Ethiopia, we all want to see our country change. But we forget how much a person's movement can contribute to the change of our country. We can think that our country is changing when we look for solutions to our personal problems, mine, yours, and yours. This means we practice winning. If we can solve our own problem, we can solve the neighbor's problem. We are slowly trying to solve the problem in Kebele. This means that it should be known that we are making our country go on the path of change. That's what being a winner is all about. Believe it or not, countries have prospered in this way and not in any other way. Not because the government is strong.

   Government alone can do nothing without winning people. He can collect taxes from the people, pay salaries, lay foundation stones, and try to do various important things. And he said that all these things can be done by man. If a person does not work for their country with a winning spirit, it is a loss. This is why we are seeing unorganized constructions and poor-quality infrastructure everywhere in our country. This is because the people who work in the spirit of winning do not want change to come and problems to be solved. He approached and asked, "Why did this happen?" If someone asks them, we will hear problems in their answers. Because when you are a loser.

If we want to change Ethiopia, we must start from ourselves and find the right solution to the problem we are facing. "My problem has no solution." If there is a tired thought, it should be removed from the mind as soon as possible. This is a loser's way of losing. Let's solve our problem using the correct solution we found.


 BY;           Bamlaku Abebaw, jimma (From abajifar village)

key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post