"A man without faith; Don't live." P.M Dr abiy ahimed ali /// “እምነት የሌለው ሰው ; አይኑር፡፡” ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ




እምነት የሌለው ሰው ; አይኑር፡፡”

ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ



እኛ የሰው ልጆች ፈጣሪን መፍራት ካልቻልን በክፋት ከሰይጣን በብዙ እጥፍ ብሰን ልንገኝ እንችላልን፡፡ ሲዖል ሰውን ስንበድል አምላክን ስናሳዝን የምንገባበት የቅጣት ስፍራ እንደሆነ ማመን ክፉ የሆነውን ባህሪያችንን እንድንሸሸው ያደርገናል፡፡ ከዚህ አንፃር ካስተዋልነው አሁን በኢትዮጲያ ምድር ላይ የተሰሩት ክፋቶች እምነት ከማጣት የመነጩ እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ለሰው ልጅ መፈናቀልና ሞት ምክንያት የሚሆኑት እምነት የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ባጠቃላይ እነእርሱ የጥፋት ሁሉ ምንጭ ናቸው፡፡ ዓለም እየታመሰች ያለችው በእነዚህ እና መሰል ሰዎች ነው፡፡

      ኢትዮጵያን ብንመለከት የምናረጋግጠው እውነት ይህንን ነው፡፡ የሃይማኖተኛ ህዝብ ምድር ብትባልም መሬት ላይ ያለው ሀቅ ግን ሌላ ነው፡፡ ሰው እምነት ካለው የበለጠ መልካም ተግባር እየሰራ የሚሄድ እንጅ በተቃራኒው የሚቆም አልነበረም፡፡ ወደ አምላኩ ለመጠጋት የሚጥር እንጅ በተቃራኒው የሚሸሽ መሆን የለበትም፡፡ የሰው ልጅ ፈጣሪውን አምኖ ለትዕዛዙ ተገዥ ሲሆን ይጠቀማል፡፡ ሌላውንም ይጠቅማል፡፡ ይሄን ማመን አለብን፡፡ 

      በዚች ሀገር ያለን ሰዎች በባህል፣ በአመለካከት፣ በቋንቋ፣ ....ወዘተ እንለያያለን፡፡ ይሄ መለያየታችን ለመገፋፋት መንስኤ ሊሆነን አይችልም፡፡ ነገር ግን ፖለቶከኞቻችን ይህን ልዩነት እንደምክንያት እያነሱ አንደኛው ሌላኛውን እንዳያምን ማድረጋቸው መቋጫ የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከተቱን እንጅ፡፡ የትኛውም ሰው ሌላውን ሰው ወገኔ ነው፣ ዘመዴ ነው፣ እረዳቴ ነው፡ ብሎ ማመንና መቀበል አለበት፡፡ በዚህ የማያምን ሰው ለመግፋት፣ ለማፈናቀል፣ ለመግደል፣ ለማሳዘን፣ ....ወዘተ በጣም ቅርብ ነው፡፡ 

    ስለዚህ እምነት የሌለው ሰው አይኑር፡፡ ለዚህ ሀሳብ ማጠናከሪያ የጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድን በአንድ ወቅት የተናገሩትን ንግግር ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ እርሳቸው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፡፡

           “... ከፍልስፍናው  አንፃር የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት ለብዙዎች እውቀት የሆኑ አባት ናቸው፡፡ በአንድ ወቀት ሀሳብ አንስተዋል፡፡ እኔም ትንሽ ለመጨመር ወደድኩ፡፡ እናም በፍልስፍናው ዓለም ጎበዝ ፈላስፋዎች ተብለው የሚወደሱና የሚነገርላቸው ሰዎች አብዝተው በመጠየቅ የሚያምኑ ናቸው፡፡ ለምሳሌ “ፈጣሪ አለ ወይ” ብለው ሲጠይቁ ተፈላሰፉ ይባላል፡፡  ግን ብዙ ብዙዎቹ ፈላስፋዎች መልስ የላቸውም፡፡ የወሎ ፈላስፋዎች ግን መልስ አላቸው፡፡

      ሰይድ እና ሙሄ የሚባሉ የወሎ ሰዎች ከልብ ጓደኛሞች የሆኑ አንድ ቀን እየተጨዋወቱ እያለ፤ ሰይድ ሙሄን “እንደው ምህዋ አላህ እንዳለ በምን ታውቃለህ” ብሎ ጠየቀው ይባላል፡፡ ሙሄም ጥያቄው የፍልስፍና ጥያቄ እንደሆነ ስለገባው በፍልስፍናው መንገድ ሲመልስለት “ካላሰብኩት አያውለኝ” አለው ይባላል፡፡ “ፈጣሪ አለ ወይ የለም” ብሎ መጠየቅ ፍልስፍና ከሆነ ሙሄ እንዳለው ካሰብኩበት ውጭ ሆኜ መገኘት ደግሞ በእኔ ስልጣን የተወሰነ ስላልሆነ ከእኔ ባሻገር ሀይል አለ የሚለውን  ወሎዮዎች በእምነት ክርስትናና እስልምና ቅድም በተባለው ብቻ ሳይሆን በፍልስፍናም ያረጋገጣችሁት ስለሆነ እንዴው እምነት የሌለው ሰው አይኑር፡፡ እምነት አስፈላጊ ስለሆነ፡፡

     ሰው ፈጣሪውን ሲያምን፣ ሰው ወንድም እህቱን ሲያምን፣ ሰው ጎረቤቱን ሲያምን፣ ሰው ሀገሩን ሲያምን ፣ ብዙ መልካም ነገሮች አሉ፡፡ በተደጋጋሚ ብየዋለው እዚህ አዳራሽ ይህን የሚያክል ሰው የተሰበሰበው እምነት ስላለ ነው፡፡ እምነት ባይኖር ኖሮ ፊትለፊት የተቀመጡት ሰዎች ከኋላቸው ጀርባችን ለማያውቁት ሰው ሰጥተው ለአንድ ሰዓት መቀመጥ አይችሉም፡፡ ያምናሉ ከኋላ ወንድሜ ነው ክፉ አይደርስብኝብ ብለው፡፡ እምነት ከሌለ ወጥቶ መግባት አይቻልም፡፡ 

 (ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ከደሴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር 

በወሎ የባህል ማዕከል አዳራሽ ካደረጉት ንግግር ላይ የተወሰደ)

    አዎ እምነት የሌለው ሰው አስቸጋሪ ነው፡፡ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለሌሎቸ ፍጥረታትም ችግር የሚያመጣ ነው የሚሆነው፡፡ ሁሉንም የሚያሳዝን እንጅ ደስታን የሚሰጥ አይሆንም፡፡ እምነት ያለው ሰው በስርዓት የሚታዘዝ እንደገናም ደግሞ በማስረጃና በምክንያት የሚቃወምም ጭምር ነው፡፡ እንደ ይስሀቅ እና እንደ ሙሴ ማለት ነው፡፡ ይስሀቅ አባቱ ሊሰዋው ሲል አልተቃወመም፡፡ ሙሴ ደግሞ በምቾት ውስጥ ቢሆንም የዘመዶቹ እንግልት እንቅልፍ ስለነሳው አምላኩን ከፊት ለፊት አስቀድሞ ያንን አገዛዝ በምክንያት ተቃውሞ ህዝቡን ነፃ እንዲወጡ አድርጓል፡፡ ሁለቱም እምነት ስላላቸው ነው፡፡

    አዎ እምነት የሌለው ሰው መኖረ የለበትም፡፡ ውጣ ሲባል ያለምክንያት የሚወጣ፤ ግባ ሲባል ያለምክንያት የሚገባ፤ ተሳደብ ሲባል እሽ ብሎ የሚሳደብ፤ ዛሬ ደጋፊ ሆኖ ነገ ደግሞ የሚቃወም፣ ዛሬ ተቃዋሚ ሆኖ ነገ ደግሞ ከደጋፊ ጋር የሚጋፋ እምነትም እውነትም ከእርሱ ዘንድ ስለሌለ ነው፡፡ 

     እምነት የሌለው ሰው አቅጣጫውን አያውቅም፡፡ ማረፊያውን አያዘጋጅም፡፡ ነገን በበጎ ለመኖር ዛሬ አይጥርም፡፡ የዛሬን እንጅ ስለነገ አያስብም፡፡ ሲናገር አይመርጥም፡፡ ሲበላም አያተርፍም፡፡ ሲጠጣ አይቆጥብም፡፡ ለመቀማት እንጅ ለመስጠት እጁን አይዘረጋም፡፡ ምስጋና አያውቅም፡፡ ምሬትና ለቅሶ ግን የእርሱ ናቸው፡፡ ሲነካ ጩኸቱ ሲለካ ንቀቱ መከራ ነው፡፡ ሌላውን ሲበድልና ሲያሰቃይ ግን ደግ የሰራ ነው የሚመስለው፡፡ ምክንያቱም እምነት የለውምና፡፡ እናም እምነት የሌለው ሰው አይኑር ለሰላም፣ ለእድገት፣ ለአብሮነት፣ ለልማት፣…….ወዘተ ፀር ነውና፡፡


አመሰግናለው፡፡

ባምላኩ አበባው

ጂማ፣ ኢትዮጲያ

ከአባጅፋር መንደር


.........................................................................................................................................

..........................................................................................................................................................


"A man without faith; Don't live."


P.M Dr abiy ahimed ali


If we human beings cannot fear the Creator, we can be many times more evil than Satan. Believing that hell is a place of punishment for wronging people and displeasing God makes us run away from our bad behavior. From this point of view, it can be confirmed that the evils that have been done on the land of Ethiopia are the result of lack of faith. It is unbelieving people who cause the displacement and death of humanity. In general, they are the source of all destruction. The world is troubled by these and such people.

       If we look at Ethiopia, this is the truth. Although it is called the land of religious people, the reality on the ground is different. A person does more good deeds than he has faith, but does not stand on the contrary. He should not be one who strives to get closer to God, but rather avoids it. Human beings believe in their Creator and obey His commands. It also benefits others. We have to believe this.

       The people of this country are different in terms of culture, attitude, language, etc. This separation cannot be a reason to push us. But our politicians citing this difference as a reason to make one of them distrust the other has put us in a never-ending civil war. Any person should believe and accept that the other person is my kindred, my relative, my helper. A person who does not believe in this is very close to being pushed, displaced, killed, saddened, etc.

     Therefore let there be no man without faith. To strengthen this idea, it is important to remember the speech of Prime Minister Dr. Abiy Ahmed. He once said so.

            "... In terms of his philosophy, Sheikh Hussain Jibril, as many of you know, is the father of knowledge for many. You picked up an idea in one moment. I also like to add a little. And in the world of philosophy, people who are praised and talked about as brilliant philosophers are those who believe by asking more. For example, when they ask, "Is there a creator?", it is called a philosopher. But many philosophers do not have an answer. But philosophers have an answer.

       Sayed and Muhe, people of Wolo who are good friends, were chatting one day. It is said that Sayyid Muheen asked him, "How do you know that Allah exists in space?" He understood that the question was a philosophical question and when he answered it in his philosophical way, he is said to have said, "Don't tell me if I don't think about it." If asking "Is there a creator or not" is a philosophy, then being outside of what I think exists is not determined by my authority, so there should not be a person who does not have faith, because you have confirmed that there is a power beyond me not only in the faith of Christianity and Islam, but also in philosophy. Because faith is important.

      When a person believes in the creator, when a person believes in his brother and sister, when a person believes in his neighbor, when a person believes in his country, there are many good things. I have said it repeatedly because there is faith in the gathering of such a large number of people in this hall. If there was no faith, the people sitting in the front would not be able to sit for an hour, giving their backs to strangers. They believe that it is my brother from behind, saying that no harm will befall me. Without faith, there is no way out.

  (Prime Minister Dr. Abiy Ahmed with the residents of Dese City

Taken from a speech given at Wolo Cultural Center Hall)

     Yes, a person without faith is difficult. It causes problems not only for humans but also for other creatures. It will not bring joy to everyone but make everyone sad. A person of faith is one who obeys order and again opposes it with evidence and reason. Like Isaac and Moses. Isaac did not resist when his father was about to sacrifice him. Even though Moses was in comfort, he woke up from the abuse of his relatives, so he asked God in front of him to free the people by protesting that rule. Because they both have faith.

     Yes, there should be no one without faith. One who goes out without a reason. Enter without reason. The one who swears when he is insulted. Today he is a supporter and tomorrow he is an opponent, today he is an opponent and tomorrow he fights with a supporter because there is no faith and truth in him.

      A person without faith does not know his direction. He does not prepare the accommodation. He does not strive today to live well tomorrow. He does not think about tomorrow but today. He does not choose when he speaks. And when he eats, he does not gain. He doesn't skimp when he drinks. He does not stretch out his hand to take but to give. He knows no gratitude. But bitterness and weeping belong to him. When it is touched, its noise is measured and its contempt is misery. But when he abuses and tortures others, he seems to be doing good. Because he has no faith. And let there not be a person without faith, because it is against peace, progress, solidarity, development, etc.




thank u.

Bamlaku Abebaw, jimma .

 Ethiopia, from abajifar village


 

key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post