መልካምነት
እኔ “መልካምነት”ን በአጭር ቃል ስገልፀው “ሰው የመሆን ምልክት” ብዬ ነው፡፡ ሰው በብዙ ዉጣ ውረድ ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑ ደጉንና ክፉውን መለየት ይችላል፡፡ አንድም የሚያስብ ነውና ምን ማሰብ እንዳለበት ያውቃል፡፡ ምን ማድረግ እንዳበትም ይለያል፡፡ ክፉ ከሰራ የመጀመሪያውን ቅጣት የሚቀበለው ከራሱ ነው፡፡ አዎ የሰው ልጅ ሲያጠፋ የሚቀጣው በጎ ሲሰራ ደግሞ “አበጀህ” ብሎ የሚያበረታው በራሱ ውስጥ የሚኖር የራሱ አለቃ አለው፡፡ ደግ ደጉን ከሰራ ደግሞ የራሱ አዕምሮ ብቻ ሳይሆን ከውጭ ያለው የህብረተሰብ ክፍልም ያወድሰዋል፡፡ ያሞግሰዋል፡፡ እርሱ ደግ ነው ተብሎ ክብር ይሰጠዋል፡፡ እውቅናም በየጊዜው የሚቸረው ይሆናል፡፡
መልካምነት ሰው የመሆን ልክ ነው፡፡ ሰው ተፈጥሮው ለክፉ ተግባር የሚመች ሆኖ ሳይሆን ለበጎ/ ለመልካም የታደለ ተደርጎ ነው፡፡ የተሰጠው ባህሪ፣ የተቸረው አካል፣ ማሰቡ መመራመሩ፣ማመዛዘኑ ሁሉ ክፉ የሆነውን ትቶ በጎ የሆነውን እንዲይዝ በሚያመች መልኩ ነው፡፡ ይህ ባይሆንማ ማሰብ እንዲችል ለምን ሆነ? በጎውን ለመፍጠር ካልታደለ እጁና እግር ምንም አያደርግለትም ነበር፡፡ መመራመር፣ መጠየቅ፣ ወዘተ ለምን እንዲችል ሆነ? ለጥፋት ወይም ለክፋት አይደለም ለመልካም እንጅ፡፡ ስለዚህ ሰውነት መልካምነት ነው፡፡
ነገር ግን ዋናው ጥያቄ የሰው ልጅ እንዴት ክፉ ለማድረገ ታደለ? እንዴትስ መልካም ለማድረግ ወደደ? የሚለው ነው፡፡ ክፉ አድራጊዎች ክፉ ማድረግን እንዴት ወረሱት መልካም የሚያደርጉስ መልካም ማድረግን ከማን አገኙት ብሎ መጠየቅ የወግ ነው፡፡ ከድሮ ጀምረን ታሪክን ብንጠይቅ በጣም ብዙ ሰዎች ክፋትን ያደርጉ ነበር፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች መልካም ነበሩ፡፡ ደግ አድራጊ ሆነው በቅዱስ መፃህፍት እንደተገለፁ ሁሉ ክፉና አረመኔያዊ ድርጊት ፈጽመውም የተጠቀሱም አሉ፡፡ ሁለቱም ይህንን ባህርያቸውን ከየት አመጡት? ከየትስ ወረሱት?
የአዳምና የሄዋን ልጆች የሆኑት አቤልና ቃየን ብንመለከት አንዱ መልካም አድራጊ ሌላኛው ደግሞ ክፉ አድራጊ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ አቤል በግ ጠባቂ ነበረ፡፡ ቃየን ደግሞ መሬትን የሚያርስ ነበረ፡፡ ሁለቱም ለአምላካቸው መስዋዕትን ማድረግ ወደዱ፡፡ አቤል ከሚጠብቃቸው በጎች የሰባውን መርጦ ሰጠ፡፡ ቃየን ደግሞ ካረሰው ካመረተው ላይ ሰጠ፡፡ እግዚአብሔርም የአቤልን መስዋዕትነት ተቀበለ፤ የቃየንን ግን እንኳን ሊቀበለው ሊመለከተውም አልወደደም፡፡ በዚህ ምክንያት ቃየን ተናደደ ፊቱም ተቆረ፡፡ እግዚአብሔርም አለው “ለምን ተናደድህ ለምንስ ፊትህ ተቆረ” እግዚአብሔርም መልሶ እንዲህ አለው “መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚያበራ አይደለምን መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፍቃዷም ወደ አንተ ነው፡፡” አለው፡፡ የእነዚህ ሁለት ወንድማማቾች ባህሪ መስዋዕት እስከአቀረቡበት ሰዓት ድረስ ምን ይመስል እንደነበር ቅዱሱ መፅሐፍ ባይጠቅስም ይህ ድርጊታቸው ግን ሁለቱም ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ አሳየን፡፡ ሁለቱም በፈጣሪ ህልውና የሚያምኑ በእርሱ እንደተፈጠሩ ያልዘነጉ ናቸው፡፡ ተፈጣሪ ናቸውና ለፈጣሪያቸው መስዋዕትን በራሳቸው ፍቃድ ያዘጋጁ ናቸው፡፡ እስከዚህ ድረስ አላጠፉም፡፡ ነገር ግን ከዚህ በኋላ የውስጣቸው እየተገለጠ መጣ፡፡ አቤል የሰባውን የተመረጠውን ሳይሰስት፣ “የእኔ ይቅር” በሚል እምነት ለእግዚአብሔር ሰጠ፡፡ ቃየን ደግሞ “እግዚአብሔር አይበላም አይጠጣም፡፡” ብሎ “የእኔ ይብለጥ” በሚል የተሻለ ያልሆነውን ሰጠ፡፡ ፍሬውን ሳሆን ገለባውን መስዋዕት አደረገ፡፡
እውነት ነው እግዚአብሔር አይበላም አይጠጣም፡፡ ፈጣሪ የእርሱን መስዋዕት ለመመልከት ያልወደደበትን ምክንያት አባቶች ሲናገሩ “በመልካምነት ስላላቀረበ ነው፡፡ በቅንነት ማቅረብ ሲገባው በስስት ስለሰጠ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ነገር ግን ቃየን ለራሱ አብዝቶ እንዲያስብና ስስታም እንዲሆን ያደረገው ምንድነው? በኋላም ይህ ስስታም ባህሪው ወደ ሰማይ ማረግ ያልቻለ መስዋዕት ከማቅረብ ጀምሮ ወንድሙን እንዲጨክንበት አድርጎታል፡፡ በእኛ ሀገርም እየሆነ ያለው ከዚህ የተለዬ አይደለም፡፡
ሰው ነፃ ፍቃድ አለው የምንለው የተሻለውን የማሰብና የማድረግ ችሎታ ስላለው ነው፡፡ ሰው በጎና የተሻለ ማድረግ እንደሚችል ሁሉ የማይረባውንና ክፉ ሊያስብለው የሚችለውን ከመስራት መታቀብ ይችላል ማለታችን ነው፡፡ እኛ ደግሞ ሰው ሆነን ስንፈጠር ለበጎ ተግባር ነው፡፡ በጎ ለማሰብ፤ በጎ ለመስራት፤ በጎ የሆነ ስፍራ ለመገኘት፡፡ አቤል በጎ አሳቢ እንደነበረ ከበጎ ተግባሩ አረጋግጠኛል፡፡ ቃየንን ደግሞ በውስጡ ክፉ ሀሳብ እንደነበረ ካደረገው ክፉ ተግባር አይተናል፡፡
መልካም የሆነውን የማናደርግ ከሆነ በሰውም በእግዚአብሔርም ተወቃሽ ነው የምንሆነው፡፡ በጎነትን የምናመጣው ከውስጣችን እንጅ ሰዎች የሚሰጡን አይደለም፡፡ ክፉ ማድረግንም እንዲሁ፡፡ በእረኛዬ ድራማ በክፍል ስድስት ውስጥ እናና በቅጡ ያላወቀችው ሰው እንዳልሆነ ሆኖ በበረት ውስጥ ያገኘችውን ከታሰረበት ገመድም ያላቀቀችው በጎ ለማድረግ የተፈጠረው ሰውነቷ እንድትተወው ስላልፈቀደላት ነው፡፡ እንጅ ከብቶቿን ብቻ አስወጥታ ትታው መሄድ ትችል ነበር፡፡ ሰው ስንሆን መልካም ተግባር ካልሆነ በስተቀረ አይስማማንም፡፡ እናና በገመድ ታስሮ ያገኘችው ሰው ባይሆንና በግ ወይም ሌላ ቢሆንም ትፈታው ነበር፡፡ ምክንያቱም አዕምሮዋ ለመጨከን እሽ አይላትምና፡፡
አሁን አሁን የምናስተውለው ነገር ቢኖር ክፉ ክፉውን እንጅ መልካም የሆነውን መስራት እየተውን እንደሆነ ነው፡፡ አዕምሯችንም ይህንን ተግባራችንን እየተላመደው ስለሆነ ምንም እየመሰለው አይደለም፡፡ አካባቢያችንን ብንመለከት የእኛን መልካም መስዋዕት የሚፈልግ ነው፡፡ የታመመ ሰው በአካባቢያችን አይጠፋም፣ የሚላስ የሚቀመስ በቤቱ ጠፍቶ የሚጨነቅ አለ፣ የሚደግፈው አጥቶ የሚሰቃይ ብዙ ነው፣ ጧሪ ቀባሪ ያጡ አዛውንት፣ የሚጠይቃቸውና ዋስ የሚሆንላቸው ያጡ እስረኞች አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚጠብቁት የእኔንና የአንተን የሁላችንን መልካም እጅ ነው፡፡
እንደ እናና ሳያመነታና ሳይፈራ ለመልካም ተግባር በቶሎ የሚዘረጋ እጅ፣ እንስፍስፍ የሚል አንጀት፣ ያለስስት የሚሄድ እግር ያስፈልገናል፡፡ ይሄንን ስናደርግ መልካም መስዋዕት እንደ አቤል ለእግዚአብሔር እንደሰጠን ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው የምናደርግ ከሆነ እንደሀገርም እንደግለሰብም ከገባንበት ውስብስብ ችግር ውስጥ አንወጣም፡፡ የበለጠ ተቅበዝባዥ እየሆንን ነው የምንሄደው፡፡ የኖርን ይመስለናል ግን ካለመኖር የተሻለ ኑሮ አንኖርም፡፡ እንበላለን እንጠጣለን ግን አንረካም፡፡ እንለብሳለን ግን አያምርብንም፡፡ እንስቃለን ግን ደስተኛ አንሆንም፡፡ እናመሰግናለን ግን ከልባችን አይሆንም፡፡ እንሰራለን ሀብትም እናከማቻለን ግን አንጠቀምበትም፡፡ መቅበዝበዝ ማለት ይሄ ነው፡፡ ነገር ግን ለፈጣሪም ለሰውም ቅን ሆነን ስንታዘዝ በረከትም አይርቀንም፤ አምላክም የምህረት ዓይኑን አያዞርብንም፡፡
“በጎነት ለራስ ነው፡፡” የሚለው የሀገራችን አባባል በትክክል እንደተነገረ ዛሬ ላይ ምርምር ያደረጉ ሰዎች ይመሰክራሉ፡፡ ይህንንም “ዳንኤል ፌስለር “ የተባለ ተመራማሪ የሰራውን ዳሰሳ መመልከት ይቻላል፡፡ እርሱም መልካም የማድረግ አንዱ ጥቅሙ እድሜን ማርዘም መቻሉ ነው፡፡ ይህንን ስመለከት “እኛ አፍሪካውያን እድሜያችን ያጠረውም መልካም ማድረግ ባለመቻላችን ነው” የሚለውን አስተሳሰቤን አጽንቶልኛል፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ፣ ከአባጅፋር መንደር
Goodness
When I describe "goodness" in a short word, it is "a sign of being human". As a person goes through many ups and downs, he can distinguish between the good and the bad. He is a thinker and knows what to think. It also determines what to do. If he does evil, he receives the first punishment from himself. Yes, the man who punishes when he destroys, and when he does good, encourages him by saying, "You are the best." He has his own boss who lives inside himself. If he does a good deed, not only his own mind but also the outside society will praise him. He praises him. He will be honored because he is kind. Acknowledgment is always appreciated.
Goodness is the essence of being human. Man's nature is not suitable for evil deeds, but for good. His character, his body, his thinking, his reasoning are all in such a way that he abandons what is bad and holds what is good. If this is not the case, why should he be able to think? If he was not fortunate enough to create good, his hands and feet would do nothing for him. Why is he able to research, question, etc.? Not for destruction or evil, but for good. Therefore, the body is goodness.
But the main question is how human beings are destined to do evil? How did he like to do good? That's what it says. It is traditional to ask how evil doers inherited doing evil and from whom do good doers get good doing. If we go back to history, there were many people who did evil. A lot of people were good. Just as they are described in the holy books as benefactors, there are those who have committed evil and barbaric acts. Where did they both get this trait? Where did you get it from?
If we look at Abel and Cain, the sons of Adam and Eve, one of them is a good person and the other is a bad person. Abel was a shepherd. And Cain was a farmer. Both loved to make sacrifices to their God. Abel chose the fattest of the sheep he was tending. And Cain gave from what he plowed. God accepted Abel's sacrifice. But he did not even want to accept or look at Cain's. Because of this, Cain was angry and his face was cut. And God said to him, "Why are you angry, why is your face cut?" And God replied to him, "Doesn't your face shine if you do good, but if you do not do good, sin is at the door and its will is towards you." it has. Although the holy book does not mention what the behavior of these two brothers was like until the moment they offered sacrifices, this action shows us what kind of people they are. Both believe in the existence of a Creator and do not forget that they were created by Him. Because they are creatures, they prepare sacrifices for their Creator of their own free will. They have not destroyed it so far. But after this, their insides were revealed. Abel gave the fat one to God without mistaking the chosen one, saying, "Forgive me." And Cain said, "God neither eats nor drinks." He gave what was not better, saying, "Let mine be better." When I harvested the fruit, he sacrificed the chaff.
It is true that God neither eats nor drinks. The Fathers say that the reason why the creator did not like to look at his sacrifice is because he did not offer it well. Because he gave greedily when he should have given sincerely." He said. But what caused Cain to think too much of himself and be greedy? Later, this greedy behavior caused him to abuse his brother, starting with offering a sacrifice that could not ascend to heaven. What is happening in our country is no different.
We say that man has free will because he has the ability to think and do what is best. We mean that as much as a person can do good and better, he can refrain from doing what he thinks is bad and absurd. And when we were created as human beings, it is for good deeds. To think good. To do good. To be in a good place. Abel's good deeds proved to me that he was a good thinker. We have seen that Cain had evil thoughts in him from the evil deeds he did.
If we do not do what is good, we will be blamed by man and God. We do not bring virtue from within ourselves, but from what people give us. And also to do evil. In episode six of the drama of iregnaye, Anana pretends to be someone she didn't recognize in the cage and freed him from the rope he was tied to because her body did not allow her to leave him. But she could have just driven her cattle away. As human beings, we do not agree unless it is a good deed. If Anna had found him tied with a rope, she would have untied him if it had been a sheep or something else. Because her mind does not allow her to be cruel.
What we notice now is that we are doing good instead of evil. Our mind is getting used to this activity, so it doesn't seem like anything. If we look at our environment, it requires our good sacrifice. A sick person does not disappear in our area, there are those who are lost at home and are worried, there are many who are suffering because of the lack of support, there are old people who have lost a gravedigger, there are prisoners who have lost someone who can ask them and be a surety for them. All these wait for the good hand of mine and yours.
Like our mother, we need a hand that quickly reaches out for good deeds without hesitation or fear, a gut that wants to be open, and feet that walk without hesitation. When we do this, it is considered that we have given a good sacrifice to God like Abel. But if we do the opposite, we will not get out of the complex problem we are in as a country and as individuals. We are becoming more and more wandering. We think we live, but we live no better than not. We eat and drink but are not satisfied. We wear it but it doesn't make us look good. We laugh but we are not happy. Thank you, but not from the bottom of our hearts. We work and accumulate wealth but we do not use it. This is what wandering means. But when we sincerely obey the Creator and man, blessings will not be far from us. And God will not turn his eyes of mercy away from us.
"Virtue is to oneself." People who have done research today will testify that the saying of our country is said correctly. This can be seen in a survey done by a researcher named "Daniel Fessler". And one of the benefits of doing good is that it prolongs life. When I saw this, it confirmed my thinking that "we Africans are short because we are not able to do good".
Bamlaku abebaw, jimma (From abajifar village)