ዋና ዋና የኩላሊት በሽታዎች
የኩላሊት በሽታዎች ሁለት ዓይነት ይዘት ያላቸው ናቸው። ያለ ቀዶ ህክምና የሚታከሙ እና ቀዶ ጥገና የሚፈልጉ በማለት፡፡ የቀዶ ጥገና ህክምና የማያስፈልጋቸው የኩላሊት በሽታዎች አንድ አንዶቹ በመድሐኒት ብቻ ታክመው መዳን ሲችሉ አንዳንዶቹ ደግሞ የኩላሊት እጥበት ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ እንደ ጠጠር ያሉ እና ሌሎች ደግሞ ቀዶ ህክምና ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡
የኩላሊት ተረፈ ምርትን የማጣራት እና የማስወጣት ችሎታዋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት ወይም የኩላሊት ሥራ መታወክን ያመጣል፡፡ ይህም የኩላሊት ውድቀት እንለዋለን፡፡ በሌላ መልኩ የቆሻሻ ምርቶች እና የኤሌክትሮላይት ሚዛን የመጠበቅ አቅሟ ሲዳከም የኩላሊት ውድቀት ይባላል፡፡ የሴረም ክሬቲኒን (Creatinine) እና በደም ውስጥ የዩሪያ መጠን መጨመር (BUN) አብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት ሥራ እየተዳከመ እንደሆነና እና በሽታ መኖሩን ያመለክታል፡፡ የኩላሊት ሽንፈት አብዛኛውን ጊዜ በሁለት ይከፈላል፡- አጣዳፊ እና ስር የሰደደ የኩላሊት ውድቀት ተብለው፡፡
አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት
አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት (AKI) ምንድን ነው?
አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት (AKI) በመባል የሚታወቀው፣ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወይም በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚከሰት ድንገተኛ የሆነ የኩላሊት ውድቀት ወይም የኩላሊት ስራ መዳከም ነው፡፡ አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት በደም ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ ተረፈ ምርቶች እንዲከማቹ ያደርጋል፡፡ በዚህ ምክንያት ኩላሊት በሰውነት ውስጥ ትክክለኛውን የፈሳሽ ሚዛን ለመጠበቅ አቅም ያጣል። አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት ከተከሰተ ባጠረ ጊዜ እንደ አንጎል፣ ልብ እና ሳንባ ያሉ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። በሆስፒታል ውስጥ በመሆን እና ከፍተኛ ክትትል በማድረግ ማከም ይቻላል፡፡ አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት ምልክቶች ምንድን ናቸው? ለዚህ የሚያበቁትስ ምን ምን ናቸው የሚሉትን እንመልከት፡፡
አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት ምልክቶች እንደ መንስኤው ይለያያሉ፡፡ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላሉ-
• የሽንት መጠን መቀነስ
• በእግር፣ በቁርጭምጭሚት፣ እና በአይን አካባቢ እብጠት መኖር
• ድካም መኖር
• የትንፋሽ እጥረት መኖር
• ግራ መጋባት
• ማቅለሽለሽ
• የደረት ሕመም እና የግፊት መጨመር
በአንዳንድ ሁኔታዎች አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት ምንም ምልክት ላያሳይ ስለሚችል በጤና ተቋም በሚደረግ ምርመራ ሊታወቅ ይችላል፡፡
አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላል።
በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል:
• የደም ግፊት ወይም ፍሰት መቀነስ ("hypotension" ይባላል)
• ፈሳሽ በሰውነታችን ውስጥ በበቂ ሁኔታ አለመኖር
• የደም ወይም ፈሳሽ ወደ ውጭ መፍሰስ ካለ, ለምሳሌ፤ ከባድ ተቅማጥ እና ትውከት ካለ….ወዘተ
• የልብ ድካም ካለ
• እና ሌሎች የልብ ተግባርን የሚረብሹ ሌሎች ሁኔታዎች ወይም የአካል ክፍሎች መጎዳት
• ራስ ምታት፣ ጉንፋን፣ እና ሌሎች ህመሞች ሲከሰቱ ያለሀኪም ትዕዛዝ ህመምን ለማስታገስ የሚያገለግሉ “NSAIDs” የተባሉ የህመም ማስታገሻዎችንና መድሃኒቶችን መውሰድ።
• ከባድ የሆነ የአለርጂ በሽታ
• ቃጠሎ ካጋጠመ
• በኩላሊቶች ላይ ቀጥተኛ ምት ወይም ሌላ ጉዳት
• የወባ በሽታ
• አንዳንድ በሽታዎች እና ሁኔታዎች ኩላሊትዎን ሊጎዱ እና ወደ አጣዳፊ የኩላሊት ውድቀት ሊያመሩ ይችላሉ፡፡
ዘላቂ ኩላሊት ድክመት
ለበርካታ ወራት አልፎም አመታት ውስጥ የቆዬ የኩላሊት ተግባር ቀስ በቀስ መዳከም፣ ወደ መጀመሪያው ጤናማ አገልግሎት የማይመለስ (የማይቀለበስ) ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ወይም - ሲኬዲ (chronic kidney failure) ይባላል። በዘላቂ የኩላሊት መድከም ውስጥ የኩላሊት ተግባር ቀስ በቀስ ያለማቋረጥ ይቀንሳል። ከረዥም ጊዜ በኋላ ኩላሊቶቹ ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ መሥራታቸውን የሚያቆሙበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። ይህ የላቀ እና ለሕይወት አስጊ የሆነ የመጨረሻ ደረጃ (ESKD/ESRD- end stage kidney disease)) ይባላል።
በዘላቂነት የኩላሊት መድከም ዝምተኛ በሽታ ተብሎ ይጠራል፡፡ በመሆኑም ብዙ ጊዜ ሳይስተዋል ይቀራል። ዘላቂ የሆነ የኩላሊት ድክመት በየመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ምልክቶቹ ጥቂት እና በደንብ መለየት የማይችሉ ናቸው። የተለመዱ የ C.K.D ምልክቶች አጠቃላይ ድክመት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ፣ አጠቃላይ እብጠት፣ የደም የደም ግፊት መጨመር፣……. ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁለቱ በጣም የተለመዱ የ CKD መንስኤዎች የስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ናቸው።
በሽንት ምርመራ ወቅት የፕሮቲን መገኘት፣ በደም ውስጥ ያለው ከፍተኛ ክሬቲኒን እና በአልትራሳውንድ ላይ ትንንሽ ሆነው መታየትና ኩላሊቶቹ የተኮማተሩ መምሰል የCKD ፍንጮች ናቸው። የሴረም ክሬቲኒን መጠን የኩላሊት በሽታን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይህ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
በ C.K.D የመጀመሪያ ደረጃዎች ውስጥ ታካሚው ተገቢ መድሃኒቶች እና የአመጋገብ ለውጦች ያስፈልገዋል፡፡ ይህንን በሽታ ሊፈውስ የሚችል የተለየ ሕክምና የለም፡፡ አንድ ሰው ዕድሜው እየገፋ ሲሄድ የኩላሊት ሥራም እንደሚቀንስ መገንዘብ አለበት፡፡ እንደ የስኳር በሽታ ያሉ ተጓዳኝ በሽታዎች እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የደም ግፊት መጨመር ከዕድሜ ጋር ተያይዞ የኩላሊት ተግባርን በፍጥነት እና በሂደት እንዲቀንስ ያደርጋል። የሕክምናው ዓላማ የበሽታውን እድገት መቆጣጠር፣ የተወሳሰቡ ችግሮች ካሉ መከላከል እና ምንም እንኳን የሕመሙ ክብደት ወይም ደረጃ ከባድ ቢሆንም መምተኛውን ግን በደንብ መንከባከብ አስፈላጊ ነው፡፡
በሽታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ (የመጨረሻ ደረጃ ሲሄድ ከ 90% በላይ የኩላሊት ተግባር ይቀንሳል፡፡ (ሴረም ክሬቲኒን አብዛኛውን ጊዜ ከ 8-10 mg / dl ይደርሳል፡፡) በዚህ ደረጃ ያሉት ህሙማን ብቸኛ የሕክምና አማራጫቸው ዲያሊስስ (የኩላሊት እጥበት) ወይም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ናቸው።
ዲያሊሲስ ኩላሊቱ ሥራ ሲያቆም በሰውነት ውስጥ ሊከማቹ የሚችሉ ቆሻሻዎችን እና ከመጠን በላይ ፈሳሾችን ከሰውነት ውስጥ ለማስወገድና ለማጣራት የኩላሊትን ስራ ተክቶ የሚሰራ መሳሪያ ወይም ማሽን ነው። ዳያሊስስ ዘላቂ ኩላሊት ድክመት ላለባቸው ሰዎች በዘላቂነት መፍትሔ የሚሰጥ አይደለም። የደከመወ ኩላሊት እስከሚቀየር ድረስ የሚተካ እንጅ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የተጎዳ ወይም መጨረሻ ደረጃ ላይ ያለ ኩላሊት (ESKD) በሽተኛው የዕድሜ ልክ ወይም መደበኛ የዳያሊስስ ሕክምና ያስፈልገዋል፡፡ (ኩላሊት በተሳካ ሁኔታ ካልተተከለ በስተቀር) ። ሁለት የዳያሊስስ ዘዴዎች ሄሞዳያሊስስና የፔሪቶናል እጥበት ናቸው።
ሄሞዳያሊስስ በብዛት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ የዳያሊስስ አይነት ነው። ሄሞዳያሊስስ ውስጥ ልዩ ማሽን በመጠቀም የቆሻሻ ምርቶችን እና ከመጠን በላይ ፈሳሽ እና ጨው በሰውነት ውስጥ ሲበዙ ያስወግዳሉ፡፡ ሌላው ደግሞ ቀጣይነት ያለው የአምቡላቶሪ ፔሪቶናል እጥበት (CAPD) የሚባለው ነው፡፡ ይህም ዳያሊሲስ ኩላሊቶቹ ሲደክሙ ወይም አቅም ሲያጥራቸው ቆሻሻዎችን እና ከመጠን በላይ ፈሳሾችን ከደም ውስጥ የማስወገድ ሰው ሰራሽ ዘዴ ነው። ለየት ያደረገው ያለ ማሽኑ እገዛ በቤት ውስጥ ወይም በሥራ ቦታ ሊከናወን የሚችል ሌላ ዓይነት የዳያሊስስ ዘዴ መሆኑ ነው። ነገር ግን በእኛ ሀገር ገና አገልግሎት ላይ አልዋለም፡፡
ዋ፣ነ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በጣም ጥሩው የሕክምና አማራጭ እና ብቸኛው የፈውስ ማግኛ ዘዴ ነው ፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ፣ ከአባ ጅፋር መንደር
....................................................................................................................................
..........................................................................................................................................................
Major kidney diseases
Kidney diseases are of two types. Saying those who can be treated non-surgically and those who need surgery. Some kidney diseases that do not require surgery can be treated with medication alone, while others may require dialysis. Such as gallstones and others may require surgery.
A significant reduction in the kidney's ability to filter and excrete waste products can lead to acute kidney failure or kidney dysfunction. We call this kidney failure. Otherwise, when its ability to maintain waste products and electrolyte balance is weakened, it is called kidney failure. Elevated serum creatinine and blood urea nitrogen (BUN) usually indicate renal dysfunction and disease. Kidney failure is usually divided into two categories: acute and chronic kidney failure.
Acute renal failure
What is acute kidney failure (AKI)?
Known as acute kidney failure (AKI), it is the sudden onset of kidney failure or kidney failure that occurs within hours or days. Acute kidney failure causes unnecessary waste products to accumulate in the blood. As a result, the kidney loses its ability to maintain the correct fluid balance in the body. In the short term, acute kidney failure can affect other parts of the body, such as the brain, heart, and lungs. It can be treated by staying in the hospital and with intensive care. What are the symptoms of acute kidney failure? Let's see what they say is the end of this.
Symptoms of acute kidney failure vary depending on the cause. They may include:
• Decreased urine output
• Swelling in the feet, ankles, and around the eyes
• Having fatigue
• Shortness of breath
• Confusion
• Nausea
• Chest pain and increased pressure
In some cases, acute kidney failure may not show any symptoms, so it can be detected by a test at a health facility.
Acute kidney failure can have a variety of causes.
It can happen for the following reasons:
• Decreased blood pressure or flow (called "hypotension")
• Lack of fluid in our body
• If there is a leak of blood or fluid, eg; If there is severe diarrhea and vomiting...etc
• If there is heart failure
• And other conditions that disturb the function of the heart or damage to organs
• Taking over-the-counter pain relievers and medications called NSAIDs for headaches, colds, and other ailments.
• Severe allergic disease
• In case of fire
• A direct blow or other injury to the kidneys
• Malaria
• Certain diseases and conditions can damage your kidneys and lead to acute kidney failure.
Permanent kidney failure
Chronic kidney disease or CKD (chronic kidney failure) is a gradual weakening of kidney function that lasts for several months or even years. In chronic renal failure, kidney function gradually declines. After a long time, it reaches a point where the kidneys stop working almost completely. This is called advanced and life-threatening end-stage kidney disease (ESKD/ESRD- end stage kidney disease).
Chronic kidney disease is called a silent disease. Thus, it often goes unnoticed. In the early stages of chronic kidney disease, the symptoms are few and often difficult to distinguish. Common symptoms of C.K.D include general weakness, loss of appetite, nausea and vomiting, general swelling, high blood pressure,……. They can be etc. The two most common causes of CKD are diabetes and hypertension.
The presence of protein in a urinalysis, high creatinine in the blood, and the appearance of small and shrunken kidneys on ultrasound are clues to CKD. Serum creatinine levels reflect kidney disease and this level increases over time.
In the early stages of C.K.D, the patient needs appropriate medications and dietary changes. There is no specific treatment that can cure this disease. One should realize that as a person ages, kidney function also declines. Co-morbidities such as diabetes and uncontrolled high blood pressure can cause rapid and progressive decline in kidney function with age. The goal of treatment is to control the progression of the disease, prevent complications, and take good care of the patient, regardless of the severity or level of the disease.
When the disease progresses to advanced stage (end stage), more than 90% of kidney function is reduced. (Serum creatinine is usually 8-10 mg/dl.) Patients at this stage have only dialysis (kidney dialysis) or kidney transplant. .
Dialysis is a device or machine that replaces the work of the kidneys to remove and filter waste and excess fluids from the body when the kidneys stop working. Dialysis is not a permanent solution for people with chronic kidney failure. A substitute for a tired kidney until it changes. Patients with advanced or end-stage renal disease (ESKD) require lifelong or regular dialysis. (Unless a kidney has been successfully transplanted). Two types of dialysis are hemodialysis and peritoneal dialysis.
Hemodialysis is the most commonly used form of dialysis. In hemodialysis, a special machine is used to remove waste products and excess fluid and salt from the body. Another is called continuous ambulatory peritoneal dialysis (CAPD). Dialysis is an artificial method of removing waste and excess fluids from the blood when the kidneys are tired or unable to function. What makes it different is that it is another form of dialysis that can be done at home or at work without the help of a machine. But it is not yet in use in our country.
Bamlaku Abebaw, Jimma, Ethiopia