አዎ መምህር መንገድ አመላካችም ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የተከረቸሙ በሮች አሉ፡፡ ብዙ የተሰወሩ ቀና መንገዶችም እንዲሁ አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚፈልጉት ትጉህና ጠንካራ እንዲሁም ሀገር ወዳድ መምህራንን ነው፡፡ ያለእነእርሱ በሩም እንደተከረቸመ መንገዱም እንደተሰወረ ይቀራል፡፡ ይህንን አምነን መቀበል ይኖርብናል፡፡ የዚች ሀገር የችግር ቁልፍ የሚገኘው፤ የብልፅግናውንጉዞ ለመጀመር ትክክለኛውን መንገድ የሚያውቁትና የሚያመላክቱን መምህራን ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ መምህራን ትልቅ አደራ አለባቸው፡፡
መምህራን ተማሪዎችን ብቁ በማድረግ የስልጣኔን መንገድ ማመላከት፣ የብልፅግናውን አቅጣጫ ማሳየት ዋና ተግባራቸው ነው፡፡ መምህራን ሀላፊነታቸውንም መወጣት የሚችሉት ይህን በማድረግ ነው፡፡ መምህራን “በር ከፋች ናቸው” ስንል ትውልድ እነእርሱ በከፈቱት በር በመግባት የሚፈልገውን ይሆናል፡፡ ለሀገር የሚበጀውንም ይሰራል ማለት ነው፡፡ መምህራን “መንገድ አመላካች ናቸው” ስንል የስልጣኔውን ጎዳና ያሳያሉ እንጅ ፊት ለፊት ተሰልፈው አይመሩም፡፡ ለዚህም የዚችን ሀገር የችግር መፍትሄ የሚያገኙት መምህራን በከፈቱት በር ተማሪዎች ገብተው ነው፡፡ የኢትዮጲያን ስልጣኔ ከፍ የሚያደርጉት መምህራን ባመላከቱት ቀና መንገድ ተማሪዎች ተጉዘው ነው፡፡ አለበለዚያ አይታሰብም፡፡ አይሆንም፡፡
የኢትዮጲያ ብልፅግና ያለመምህራን ተሳትፎ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ ለምን ከተባለ ቁልፉ ያለው በእነእርሱ ውስጥ ነውና፡፡ መንገዱንም የሚመሩን የእነእርሱ ውጤቶች ናቸውና፡፡ እናም ይህን ያህል ከባድ ሃላፊነት እንዳለባቸው ገብቷቸው በዚያው ልክ የሚለፉ መምህራንን ኢትዮጲያ ትፈልጋለች፡፡
የኢትዮጲያ መምህራን በሩን በትክክለኛ ቁልፍ በመክፈትና ትክክለኛውን የስልጣኔ ጎዳና ከማሳየት አንፅር ብዙ ስኬታማ ናቸው ብዬ በበኩሌ አላምንም፡፡ ለዚህ ደግሞ ወደ ተከፈተው በር ገብተው የተጠቀሙትና ሀገርን የጠቀሙትን ምን ያህል እንደሆኑ መመልከት በቂ ነው፡፡
በትክክለኛው የስልጣኔ ጎዳና ላይም ያሉትን ማየት እንዲሁ በቂ ነው፡፡ካሳዩትና ካመላከቱት እጅግ በጣም አነስተኛው እንደሆነ መመልከት እንችላለን፡፡
ዶ/ር አብይ አህመድ በዚሁ መድረክ ላይ እንዲህ የሚል ንግግርም ጨምረው ነበር፡፡ “መምህር ለመሆን ማወቅና ማሳወቂያ መንገዱንም ማወቅ ያስፈልጋል፡፡” ነበር ያሉት፡፡ ትውልድ ለምን በአካባቢው ብዙ ችግር እንዳለ እያወቀመፍትሄ ፈላጊ አልሆነም? ለምን መፍትሄው የሚገኝበት ቦታ ቁልፉ ተዘጋበት? ለምን ትክክለኛ የስልጣኔው መንገድ ተሰወረበት? ለምን የስኬት መንገዱ ጠፋበት? ይሄ ሁሉ ጥያቄ ጠቅለል ባለ በአንድ መልስ ሊሰጠው ይችላል፡፡ አንደኛው መምህራን ትክክለኛውን በር በትክክለኛ ቁልፍ አልከፈቱም፡፡እንዲሁም የስልጣኔን ጎዳና ማመላከት አልቻሉም የሚል ሊሆን ይችላል፡፡
ስለዚህ መምህራን ስኬታማ ትውልድ ለመፍጠር የመጀመሪያው ማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ግን ማሳወቂያ መንገዱን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ምን አልባትም የመምህራን ድካም ውጤት ያላመጣው ማሳወቂያ መንገዱን ባለመለየት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም ውጤታችሁ ባዶ መሆን የለበትምና ማሳወቂያ መንገዱን ለይታችሁ እንድታስተምሩ አደራ እላለሁ፡፡
መምህር የተዘጋውን በር የሚከፍተውም ቀናውንም ጎዳና የሚጠቁሙት በክፍል ውስጥ በማስተማር ብቻ አይደለም፡፡መምህር የሆነ ሰው ሁሉም ነገሩ አስተማሪ መሆን አለበት፡፡ የሚናገረውና የሚተገብረው የተገናኘ መሆን ይኖርበታል፡፡ በክፍል ውስጥ ብቻ አስተምሮ የሚወጣ ከሆነ ተረት የተናገረ ያህል ነው ተማሪዎቹ የሚረዱት፡፡ አንድ ሰው ያደገበትን ማሕበረሰብ ቋንቋ፣ ባሕል፣ እምነት እና ሌሎች ድርጊቶችን በቀላሉ የሚረዳውና የሚተገብረው ከአፋዊ በዘለለ በተግባር ሲደረግ ስለሚመለከት ነው፡፡ ከመስማት ይልቅ በተግባር ማሳየት በብዙ እጥፍ ለእውቀት ያስፈልጋል፡፡
አንድ መምህር ትክክለኛ መምህር የሚሆነው የሚናገረውን በተግባር እያሳዬ የሚሄድ ነው፡፡ ተማሪዎቹ እንዲያደርጉት የሚፈልገውን እርሱም እያደረገ የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ ውጤታማ መሆን አለባችሁ ብሎ የሚያስተምር መምህር እርሱ እራሱ ውጤታማ ሆኖ መታየት አለበት፡፡
ታላላቆቻችሁን አክብሩ ብሎ የሚያስተምር መምህር እርሱ እራሱ አክብሮ ማሳየት ይኖርበታል፡፡ እራሳችሁን ጠብቁ ብሎ የሚመክር አንድ መምህር እርሱ እራሱ እራሱን ጠብቆ ማሳየት ያስፈልጋል፡፡ አለበለዚያ ቀልድ ወይም ተረትነው፡፡
በመጨረሻም
መምህራን ሆይ ፤፤
ያለ እናንተ ለውጥ የለም፡፡ ያለእናንተ ለችግር መፍትሄ ማግኘት አይታሰብም፡፡
ያለእናንተ ነገን በተስፋ መመልከትም አይቻልም፡፡ ያለእናንተም ተመራማሪ፣ አስተማሪ፣ ዶክተር፣ ነርስ፣ መሪ፣ …ወዘተ መሆን አይቻልም፡፡
ያለእናንተ መበልፀግ ወደ ስኬትም መድረስ አይቻልም፡፡ ያለእናንተ ኢትዮጵያን ማሻገርም እንዲሁ አይታሰብም፡፡ ስለዚህ አብዝታችሁ
ተማሩ አብዝታችሁም አስተምሩ፡፡ ድካማችሁ ውጤት ያመጣ ዘንድ ትክክለኛውን መንገድ ተከተሉ፡፡
.........................................
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ፣ ከአባ ጅፋር መንደር
.......................................................................................................
Yes, the teacher is also a guide.
There are many locked doors in Ethiopia. There are also many hidden paths. All these need diligent, strong and patriotic teachers. Without them, the door remains barred and the road hidden. We must admit this. The key to this country's problem lies in; They are the teachers who know and show us the right way to start the journey of prosperity. For this, teachers have a great responsibility.
It is the main task of teachers to point the way of civilization by making students qualified, to show the direction of prosperity. Teachers can also fulfill their responsibilities by doing this. When we say that teachers are "door openers", a generation will enter through the door they open and become what they want. It means that he will do what is best for the country. When we say that teachers are "indicators of the way", they show the way of civilization, but they do not lead in front. For this reason, the solutions to the problems of this country are found by the students through the doors opened by the teachers. Ethiopian civilization is enhanced by the students who have traveled the right path that the teachers have shown. Otherwise, it will not be considered. no way.
The prosperity of Ethiopia cannot be ensured without the participation of teachers. Why, because the key is in them. And it is their results that guide us on the way. And Ethiopia is looking for teachers who can handle such a heavy responsibility.
For my part, I do not believe that Ethiopian teachers are more successful than opening the door with the right key and showing the right path of civilization. For this, it is enough to look at how many people have entered the open door and used the country.
It is enough to see those who are on the right path of civilization.
Dr. Abiy Ahmed also added the following speech on the same platform. "In order to be a teacher, it is necessary to know and to know the notification way." They said it was. Why has the generation not become a solution seeker knowing that there are many problems in the area? Why is the solution locked? Why was the true way of civilization hidden? Why did he lose his way to success? All these questions can be answered in one summary. One could be that the teachers did not open the right door with the right key, nor could they point the way to civilization.
Therefore, in order to create a successful generation of teachers, the first thing is to know, and the second is to identify the path of notification. Perhaps the failure of the teachers was due to the lack of notification. And your result should not be empty, so I entrust you to separate the way of notification and teach.
A teacher opens the closed door and points the right path not only by teaching in the classroom. A teacher must be a teacher in everything. What he says and what he does must be connected. If he only teaches in the classroom, it is as if he is telling a story, the students will understand. A person can easily understand and apply the language, culture, beliefs and other practices of the society in which he grew up because he sees it being done more than verbally. Demonstrating is much more necessary for knowledge than hearing.
A teacher is a true teacher who practices what he says. It should show what he wants the students to do. A teacher who teaches you to be effective must be seen to be effective.
A teacher who teaches you to respect your elders should show respect himself. A teacher who advises to take care of yourself needs to show that he is taking care of himself. Otherwise, it's a joke or a fable.
Finally
Teachers!
There is no change without you. Without you, it is impossible to find a solution to the problem. It is impossible to look forward to tomorrow without you. Without you, it is impossible to be a researcher, teacher, doctor, nurse, leader, etc. Without you, it is impossible to prosper and achieve success. Crossing Ethiopia without you is also unthinkable. So learn more and teach more. Follow the right path so that your hard work will bear fruit.
Thank u.
Bamlaku Abebaw, jimma