“እናንተ መምህራን በር ከፋች መንገድ አመልካችም ናችሁ፡፡” ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ// part one "You teachers are the ones who open the door and show the way." Prime Minister Dr. Abiy Ahmed

 


    ከአስር አመት በፊት ዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለው አንድ መምህራችን እንዲህ ብለውን ነበር፡፡  “ አንድ ወዳጄ ወደ አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ያቀናል፡፡ የሄደውም የመስሪያ ቤቱን ሀላፊ ለማነጋገር ነበር፡፡ ይህ ሰው ትምህርቱን ያቆመው ሶስተኛ ክፍል ላይ ነው፡፡ እናም ጥበቃውን አልፎ ብዙ ወደ ውስጥ ከሄደ በኋላ ግቢው ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሰው እንኳን የለም፡፡ እርሱ ደግሞ የሀላፊው ቢሮ የት ጋር እንዳለ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም እዚህ ግቢ የመጣው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ ወደዚህ ወደዚያ እያለ ለብዙ ሰዓት ቆዬ፡፡ ተመልሶ ወደ ግቢው በር ሄዶ ጥበቃውን እንዳያናግር እራቀበት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን በሚዘዋወርበት አካባቢ በአንድ እንጨት ላይ ብዙ ባለቀስት የቆርቆሮ ቁርጥራጮች ተሰካክተው በቆርቆሮዎቹ ላይም ፅሁፍ ተፅፎባቸው ተመለከተ፡፡ እንደምነም ብሎ ፊደል እየቆጠረ አነበባቸው፡፡ 

አንድ አንዱንም ፉደላት እረስቶ ስለነበር የሚሰጡት ትርጉም ሊገባው አልቻለም፡፡ ከእንጨቱ አናት ላይ አንድ ቁጥር ተፅፋ ከፊት ለፊት ደግሞ ጭረት ከጭረቱ ጫፍ ላይ ቀስት ተደርጎ ከተቀመጠ በኋላ ሀላፊ የሚል ፅሁፍ አለ፡፡ ይህም እንዲህ ነበር ይላል፡፡

                                               ተራ ቁ 1         ሀላፊ”

 “ላ” ፊደል “ሳ” እየመሰለችሁ ትርጉሙ ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ከብዙ መንገላታት በኋላ ሌላ አንድ ባለጉዳይ መጣ፡፡ 

ይህ ባለጉዳይም ከዚህ ከወዳጄ በብዙ ነገር ይሻል ነበርና ሁሉንም ነገር አስረዳው፡፡ እርሱም እረዳውና ወደ ሀላፊው ቢሮ ገባ፡፡ ባለመማሩም እጅግ አብዝቶ ተማረረ፡፡” አሉ እኝህ መመህሬ፡፡ ተማሪዎች ሲስቁ እኔ ግን በአዕምሮዬ ብዙ ነገር አስብኩ፡፡ በመጨረሻም መመህሬ “ በዘመናችን ብዙ ሰዎች የህይወት አቅጣጫ የጠፋባቸው አሉ፡፡ ብዙ የህይወት መንገድ እያለ ነገር ግን እቅጣጫ አመልካቹን ባለማግኘታቸው ዘወትር ባልሆነ ጎዳና ገብተው የሚርመሰመሱ አሉ፡፡ እናንተ ተማሪዎች የነገ የህይወታችሁንአቅጣጫ የሚጠቁሙት መምራኖቻችሁ ናቸው፡፡ እባካችሁ አስተውላችሁ ተማሩ፡፡ 

አለበለዚያ እንደዚህ ወዳጄ የተወሰነ መንገድ ተጉዛችሁ ግራ መጋባታችሁ አይቀርም፡፡” ብለው ወደ እለቱ ትምህርት አመሩ፡፡እኔም ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ይህንን ሲናገር አስታወስኩና እንዲህ አልኩ፡፡

“የሰው ልጅ ከእናቱ ማሕፀን ተፀንሶ ሲወለድ ልክ አንድ ጥቅጥቅ ያለ ደን ውስጥ ድንገት እንደተገኘ ሰው ይቆጠራል፡፡ አቅጣጫው የጠፋበት ሁሉም ነገር እንግዳ የሆነበት ምንም የማያውቅን ሰው ይመስላል፡፡ 

በሌላ ምሳሌ ለማስረዳት ሰው እንደተወለደ በአዕምሮው ውስጥ ምንም ነገር ስለሌለ ምንም ያልተፃፈበትን አንድ ነጭ ወረቀትን ይመስላል፡፡ እያደገ ሲሄድ ከእናቱ እንቅስቃሴ ጀምሮ በአካባቢው የሚያገኘውን መረጃበአዕምሮው ወረቀት ላይ መከተብ ይጀምራል፡፡ ከዚያም ይቀጥልና እያንዳንዱን የውሎውን እንቅስቃሴ መመዝገብ ይጀምራል፡፡ በአዕምሮው መዝገብ ላይ የሚያኖረው ነገር መልካም ሊሆንም ይችላል፡፡ ደግሞም ላይሆንም ይችላል፡፡ ሁሉንም በቤተሰብና በማህበረሰብ ውስጥ የሚያገኘውን ሁሉ ስለሚከትብ ማለት ነው፡፡  የሰው ልጅ የልጅነት ጊዜው መልካምም መጥፎም ለመሆን የሚረዳውን ማንነት ለመያዝ የሚጀምርበት ሰዓት ነው፡፡

ለሰው ልጅ ቤተሰቡም አካባቢውም ተፈጥሮም መምህር ናቸው፡፡ ልብ ብሎ ለሚከታተላቸው፡፡ እነዚህ መደበኛ ያልሆኑ መምህራን መደበኛ ከሆኑት ጋር ተደምረውና ተናበው ሲያስተምሩ ትውልድ ዘመን የሚሻገር ተግባር ይፈፅማል፡፡ ሁለቱም መምህራን በአንድ ትውልድ ውስጥ እኩል አስተዋፅዖ ያበረክታሉ፡፡

መምህራን ትውልድን ለማስተማር ከሶስት ዓመት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳን መደበኛ ያልሆኑት መምህራን ስርዓት ባለው መንገድ ባይመሩትም እነዚህ መደበኛ የሆኑት ግን ወደ ትክክለኛው መንገድ የመምራት ትልቅ አቅም አላቸው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚታወቁት ዝነኛ ሰዎች መሰረቶቻቸው መደበኛ መምህራን ናቸው፡፡ ጠፈር ላይም ያሉት ጠፈርተኞች ለዚህ እንዲበቁ ያደረጋቸው መደበኛ መምህራኖች ናቸው፡፡ ብዙ ህዝብን ከኋላቸው አሰልፈው ፊት ለፊት ሁሉን ነገር እየተጋፈጡ ለትውልድ የተሻለ ሀገር ለማስረከብ የሚደክሙት መሪዎችም የመደበኛ መምህራን ውጤቶች ናቸው፡፡

ዘወትር ለችግር መፍትሄ ፍለጋ ሲደክሙ የሚውሉት ተመራማሪዎችም የመምህራን ውጤት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች መደበኛ መምህራንን ባይገናኙ ኖሮ ለዚህ እንደማይበቁ ማመን አለብን፡፡ አንድ ሰው ስኬታማ ነው ማለት ከጀርባው ጠንካራ መምህር አለ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አንድ ሰው ሰነፍ ነው ማለት መደበኛ መምህራኖቹ ሰነፍ ነበሩ፤ እርሱም ከኢ-መደበኛ መምህራኖቹ ትምህርት አልቀሰመም እንደማለት ነው፡፡

ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ “እናንተ መምህራን በር ከፋች መንገድ አመልካችም ናችሁ፡፡”  ብለው ነበር፡፡  ንግግራቸው እጅግ በጣም እረቂቅ ቢሆንም የገባኝና ያህል መከተብ ፈለኩ፡፡ እውነት ነው መምህራን በር ከፋች ናቸው፡፡ ትክክለኛውንም መንገድ ማመላከት የሚችሉም ናቸው መምህራን፡፡ በተለይም መደበኛ መምህራን፡፡

 መምህራን የሰው ልጅ የተሰጠውን እምቅ አቅም እንዲጠቀም በር የሚከፍቱና ወደ ተለያዬ ቀና መንገድ የሚመሩ ናቸው፡፡ አዎ የሰው ልጅ መሪ አመለካች ያስፈልገዋል፡፡ የዚህ ሀላፊነት ደግሞ የወደቀው መደበኛ መምህር ላይ ነው፡፡ የሰውን ልጅ ያለመምህር መሪነት ዝም ብለህ ብትተወው አዲስ ነገር መፍጠርም ማግኘትም አይችልም፡፡ ሁል ጊዜ የሚኖረው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ነው፡፡ ትንሽ ይሰራል ያንን ይበላል፡፡ ይህ አዙሪት ነው በህይወቱ የሚመላለሰው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጥፎውናን ጥሩውን መለየት ስለማይችል አደበላልቆ ነው የሚኖረው፡፡ የሰው ልጅ መምህር ባይኖረው ኖሮ በቀና ጎዳና ሄዶ ዛሬን አያሳየንም ነበር፡፡ ትክክለኛውን መንገድ መምህራን ስላመላከቱን ነው የዛሬይቱን ዓለም ያየናት፡፡

  ሰዎች ወደጠፈር የሚገቡት የጠፈርን በር መምሀራን ስለከፈቱላቸው ነው፡፡ ሰዎች ጥበብ ውስጥ ገብተው እንደፈለጉት የሚዋኙት በሩን መመህራን ስለከፈቱላቸው ነው፡፡ ምሁራን የተለያዬ የምርምር ውጤትን የሚፈጥሩት በመምህራን በር ከፋችነት ነው፡፡ እኔም እንዲህ የምፅፈው መምህራን በከፈቱልኝ በር ገብቼ ነው፡፡ አዎ መምህራኖች በር ከፋች ናቸው፡፡


  ባምላኩ አበባው፣ ጅማ

...................................................................................................................................
................................................................................................
"You teachers are the ones who open the door and show the way."
  Prime Minister Dr. Abiy Ahmed
 
     
                "When a human being is conceived from his mother's womb and born, he is considered as a person suddenly found in a dense forest. He looks like a disoriented person, where everything is strange.
To illustrate another example, when a person is born, there is nothing in his mind, so he is like a blank sheet of paper. As he grows up, he begins to inject the information he finds in the environment from his mother's activities into his mental paper. Then it goes ahead and starts recording every movement of the plant. What he puts on his mental record may be good. And maybe not. It means that everyone he meets in the family and community. Childhood is the time when a person begins to acquire an identity that helps them become good and bad.
He is the teacher of man, his family, environment and nature. For those who follow them carefully. When these non-formal teachers are combined with the formal ones and teach together, a task that transcends generations is done. Both teachers contribute equally in a generation.
Teachers can start at age three to teach a generation. Although the informal teachers do not lead in a systematic way, these formal ones have a great potential to lead to the right path. Most of the famous people in the world today have their foundations as regular teachers. The astronauts in space are the regular teachers who make them fit for this. Leaders who put a lot of people behind them and face everything head on to hand over a better country to the next generation are also the results of formal teachers.
The researchers who are constantly working hard to find solutions to problems are also the result of teachers. We have to believe that all these people would not have made it if they had not met regular teachers. A person who is successful means that there is a strong teacher behind him. On the contrary, to say that a person is lazy is that his regular teachers were lazy; It is as if he did not learn from his informal teachers.
Prime Minister Dr. Abiy Ahmed said this in his discussion forum with teachers. "You teachers are the ones who open the door and show the way." They said. Although their speech was very abstract, I wanted to inoculate as much as I could understand it. It is true that teachers are door openers. Teachers are also able to point the right way. Especially regular teachers.
  Teachers are the ones who open the door for human beings to use their potential and guide them on the right path. Yes, humanity needs a leader. The responsibility for this falls on the regular teacher. If you simply leave the human being without the guidance of a teacher, he will not be able to create or discover new things. He always lived a hand-to-mouth existence. He works a little and eats that. This is the cycle he walks in his life. In addition, he cannot distinguish between good and bad, so he lives in confusion. If mankind had not had a teacher, he would not have followed the right path and shown us today. We have seen the world today because teachers have shown us the right way.
   Humans enter space because teachers open the door of space for them. People enter the wisdom and swim as they please because the teachers have opened the door for them. Academics create unique research results through teachers. I am writing like this because I have entered the door opened for me by the teachers. Yes, teachers are door openers.


Bamlaku Abebaw, jimma
key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post