ክፍል 4
ጥፋት
ጥፋት ከገደብና ከስርዓት መውጣት ነው፡፡ ጥፋት ከትዕዛዝና ከህግ ውጭ መሆን ነው፡፡ ጥፋት ከልክነት ማነስ ከሰውነት መጉደል ነው፡፡ የሰው ልጅ ለጥፋት የተፈጠረ ሆኖ የተሰራ ባይሆንም ባህሪው ግን ስህተት እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ ይህንን ወደ ኋላ መለስ ብለን አዳምንና ሄዋንን ብናስተውል የምናረጋግጠው ጉዳይ ነው፡፡ ተፈጥሯቸው ውብ አምላክ ሲሰራቸውም እንከን አልባ ቢሆንም ግን አታድርጉ የተባሉትን አድርገው ውበ ከሆነው ከገነት; አስገኝ ከሆነው ከእግዚአብሔር ተለይተዋል፡፡ ይሄ ለእነእርሱ ትልቅ ክስረት ነው፡፡ ይሄ በመጀመሪያ የሰሩት ወደር የሌለው ጥፋት ነው፡፡
እኛ ግን “ለምን ጥፋት ሰሩ?” ብሎ መጠየቅ አለብን፡፡ ሆን ብለው ከአምላካቸው መነጠል ፈልገው ይሆን? ገነትስ ስላልተመቻቸው በዚህ መላ ቦታ እንዲቀየርላቸው በማሰብ ይሆን? ወይስ ባለማወቅ አምላካቸውን ለመፈታተን ይሆን? ወይስ እንደሚባለውና አንዳነበብነው እግዚአብሔርነትን ሽተው አድራጊ ፈጣሪ መሆን ተመኝተው ይሆን? የቱ ይሆን አታድርጉ የተባለውን አምላካዊ ትዕዛዝ የጣሱበት ምክንያት? ይሄ አሁንም ጥያቄ የሚያስነሳ እና ምርምርን የሚፈልግ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ እነእርሱ ጥፋት ሰርተዋል፡፡ ለምን ጥፋት ሰሩ?
አዳምና ሄዋን ብቻ ሳይሆኑ ከእነእርሱ ቀደም ብለው የተፈጠሩት መላዕክት እኮ ጦርነት ከፍተው ነበረ፡፡ ጦርነቱ የተካሄደው ደግሞ እርስ በእርሳቸው ነው፡፡ የሳጥናኤል ወገን እና የሚካኤል ወገን ነበር ጦርነቱን በበላይነት ሲመሩት የነበረ፡፡ በመጨረሻም የቅዱስ ሚካኤል ወገን ድል አድርጎ ሲመለስ የሳጥናኤል ወገን ግን በጫካና በገደል ተበታትኖ ቀረ፡፡ ይሄ የሚነግረን መላዕክት በላይኛው ሰማይ ጥፋት ፈፅመው እንደነበር ነው፡፡ እኛ መጠየቅ ያለብን ሳጥናኤል ለምን ጥፋት አጠፋ? ብለን ነው፡፡ ምድር ላይ እንዳሉት አሸባሪዎች ሽብር ለመፍጠር አስቦ ይሆን? ነው ወይስ አቅምና የተደራጀ የመላዕክት ሃይል እንዲሁም ለጦርነት የሚያገለግሉ ግብዓቶች ስላነሱት ለድል አልበቃ አለ እንጅ ትክክል ነበረ ያስብላል? ምክንያቱም ጦርነትን የሚያሸንፈው ትክክል የሆነ ብቻ አይደለምና፡፡ ብቻ ግን አዳምና ሄዋን ከመፈጠራቸው በፊት በመላዕክት ዘንድ ጥፋት ተሰርቶ ነበር፡፡ ለምን ጥፋት ተሰራ ብሎ መጠየቅ አሁንም ተገቢ ነው፡፡ ትክክለኛውን መልስ ማግኘት ካልቻልን ከንቱ ፈራጅ ነው የምንሆነው፡፡
አዳምና ሄዋን ጥፋትን ሰርተዋል፡፡ እኛም ጥፋትን እንሰራለን እየሰራንም ነው፡፡ ለምንድነው ጥፋት እየሰራን ያለነው? ሰውን ገድለናል፣ ይህንን ባናደርግ እንዲገደል አድርገናል፣ ይህንም ባንፈፅም ሲገደል አይተን ዝም ብለናል፣ እሺ ከዚህ ብናመልጥ ለመገደል ሲወሰድ አይተናል፣ እሽ ከዚህ ሁሉ ንፁህ ብንሆን የሰውን ልጅ ካደገበት ከቦረቀበት ቀዬ እንዲሰደድ አድርገናል ወይም አመቻችተናል፡፡ አሁንም ከዚህ እጃችን ከሌለበት ቢያንስ በማህበራዊ ኑሮ አግልለን በዘሩ በሃይማኖቱ ምክንያት እኩል ተሳታፊ እንዳይሆን በተግባርም በሃሳብም ለይተን እንዲሸማቀቅና ሰላም እንዳይሰማው አድርገናል፡፡ የሁላችንን እጅ ብንፈትሽ እጃችን በደም የጨቀዬ ነው፡፡ ማናችንም ከጥፋት ንፁህ አይደለንም፡፡ ለምን ጥፋትን እንሰራለን? ለምን እራሳችንንም ሆነ ሌላውን ሰው እንበድላለን? ለምንስ አምላካችንን እናሳዝናለን? ለምን? ስለዚህ እራሳችንን መመርመር አለብን፡፡
የሰው ልጅ በሁለት መንገድ ጥፋትን ሊፈፅም ይችላል፡፡ አንደኛው ባለማወቅ ውስጥ ሆኖ ሊሰራ ይችላል፡፡ እርሱ ደግ ያደረገ፣ መልካም የተናገረ፣ ጥሩ የሰራ ሊመስለው ይችላል፡፡ ነገር ግን ያልተረዳው ወይም ተግባሩን ሁሉ በክፉ ያየበት ሊያዝንበት ሊከፋበት ይችላል፡፡ ጥፋትም ሆኖ ሊመዘገብበት ይችላል፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎችን በምክር መመለስ ይቻላል፡፡ ክፉ መናገርና መግፋት አያስፈልግም፡፡ ተገቢም አይደለም፡፡ ተው ሲባሉ በቶሎ ይመለሳሉና፡፡
ሁለተኛው ግን በማወቅ ውስጥ ሆኖ የሚሰራ ጥፋት ነው፡፡ ይህንን መንገድ አሁንም በሁለት መንገድ መመልከት እንችላለን፡፡ አንደኛው ጥፋትን በማናለብኝነትና በድፍረት መስራት ነው፡፡ ሆን ብሎ ሰውን መግደል ወይም መግፋትና ማንገላታት በዚህ ውስጥ የሚጠቃለሉ ጥፋቶች ናቸው፡፡ ሌላኛው ግን ጥፋትን አማራጭ መፍትሔ በማጣት መስራት ነው፡፡ እንደዚህ ያሉ ጥፋቶች ባይሰሩ በተወደደ ነበር፤ ነገር ግን መፍትሄው በመጥፋቱ ወይም በመጋረዱ ምክንያት ሳንፈልጋቸው ይሰራሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የምትሆነን በእረኛዬ ተከታታይ ድራማ ላይ የምናውቃት ወጋየው ናት፡፡ ይቺ ሴት ለትምህርት ከቤተሰብ በተለየችበት ወቅት ሴት ናትና ድንገት በፍቅር ወደቀች፡፡ እራሷንም አሳልፋ ሰጠችው፡፡ ፀነሰችም፡፡ ያውም መንታ የሆኑ ልጆችን፡፡ የትምህርት ጊዜዋን ጨርሳ ወደ ቤተሰብ ስትመጣ ግን የጠበቃት ሌላ ነገር ነው፡፡ እርሷ ለመውለድ የደረሰች ነፍሰጡር ሆና ሳለ ነገር ግን እናት እና አባቷ ለሌላ ሰው አጭተው ሊድሯት ጣጣቸውን ጨርሰዋል፡፡ ቤተሰቦቿ የሰርግ ድግሳቸውን እየጨረሱ ሲመጡ እርሷም የመውለጃ ጊዜዋ እየደረሰ ነበር፡፡ ለመናገር ዛሬ ነገ እያለች ስትፈራ ስትቸር በሰርጓ ዋዜማ ድንገት ወለደች፡፡ እርሷም ግራ ገባት ቤተሰብም ተደናገጠ፡፡ የሚይዙት የሚጨብጡትን አጡ፡፡ ለክብራቸው ሲሉ ሊሸሽጓት ወደዱ፡፡ በዚህ ምክንያት የምትወደውን አባቷን አጣች፡፡ ቤተሰብም ለውርደት ለድህነት ተጋለጠ፡፡ ከዘመን በኋላ በፀፀት የበገነ ሰውነቷን ይዛ ይቅርታን ፈልጋ ብትመለስም የፈለገችውን አላገኘችም፡፡ ያ ያለፈው ጥፋቷ አሁንም በሰፈሩ ሰው እንደ አዲስ መወራት ጀመረ፡፡
ወጋየው የሰራችው ጥፋት እንዳይከሰት ማድረግ የሚቻልበት ብዙ አማራጭና መፍትሔ ይኖረው ይሆናል፡፡ ይህንን እርሷ ጠፍቷት ሳይሆን ከምትኖርበት ባህልና እምነት አንፃር ተቀባይነት አለው ብላ ስላላመነች ነው፡፡ እንጀ እርሷማ ከባህሏና ከእምነቷ አንፃር የሚመጥን መፍትሔ ፍለጋ ላይ ነበረች፡፡ እርሷ ስህተት ውስጥ መሆኗንና አለመሆኗን ከአደገችበት ባህልና እምነት አንፃር አይታ ጥፋት እንደፈፀመች አውቃለች፡፡ ግን ደግሞ ጉዳዩን በብዙ አቅጣጫ ማየት ከቻልን “እውነት ጥፋት ሰርታለች ወይ?” ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡
ሐዋርያቱ ዘማዊ የሆነችውን ሴት እንውገራት ሲሉት ክርስቶስ ግን እንዲህ ነበር ያላቸው “ከእናንተ መካከል ሃጥያት የሌለበት ቢኖር ይህንን ያድርግ” ክርስቶስ ይህንን ያለበት ምክንያት የእርሷን መሰል ጥፋትና ኋጥያት ባይሰሩም ግን ሃዋርያቱ ንፁህ አለመሆናቸውን ለመግለፅ ነው፡፡ እርሷን ለመውቀስ የሚበቃ ጥፋት ያልሰራ ብቻ ነው፡፡ ጥፋተኛ ሰው ሌላውን ጥፋተኛ ሊነቅፍ ሊተች ከቶ አይችልም፡፡ “እኔ ማን ነንና እርሱን ምን እላለው” ነው ማለት ያለበት፡፡
ጣታችንን ሌላ ሰው ላይ ከመቀሰራችን በፊት እራሳችንን መለስ ብለን ማየት መለማመድ አለብን፡፡ “እከሌ እንዲህ ነው፤ አከሊት እንዲህ ናት” ከማለታችን በፊት “እኔስ” ብሎ እራስን መፈተሸ ትክክለኝነት ነው፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ከአባ ጅፋር መንደር
......................................................................................................................
........................................................................................................
Section 4
making mistake
Crime is going out of bounds and order. Crime is being out of order and law. Humans are not made to make mistakes, but their nature makes them prone to make mistakes. If we look back at Adam and Eve, we can confirm this. Their nature is beautiful when God made them flawless, but they did what they were told not to do, from the beautiful paradise; They are separated from God who made them. This is a great loss for them. This is an incomparable mischief they have done in the first place.
But we ask, "Why did you do evil?" We must ask. Did they deliberately want to separate from their God? Is it because Heaven is not comfortable with this whole place, thinking that it will be changed for them? Or will it be to challenge their god without knowing? Or as it is said and we have not read it, did they desire to be a creator who smells God? What is the reason they broke God's commandment not to do? This is still a big issue that raises questions and needs research. They have done wrong. Why did they make a mistake?
Not only Adam and Eve, but the angels who were created before them had started a war. And the war was fought against each other. It was the side of Satanel and the side of Michael who were leading the battle. Finally, Saint Michael's side returned victorious, but Satan's side was scattered in the forest and cliffs. This tells us that the angels were wreaking havoc in the upper heaven. We have to ask why Satan destroyed destruction? We say. Did he intend to create terror like the terrorists on earth? Or does he think that he was correct because he said that he was not enough to win because of the capacity and the organized power of the angels and the resources used for war? Because it's not just what's right that wins a war. But before Adam and Eve were created, destruction was done by the angels. It is still appropriate to ask why the offense was committed. If we cannot find the right answer, we are useless judges.
Adam and Eve sinned. We also do damage and we are doing it. Why are we doing wrong? We killed a person, if we didn't do this, we caused him to be killed, and even if we didn't do this, we were silent when we saw him killed, if we escaped, we saw him being taken to be killed, even if we were innocent of all this, we made or facilitated the migration of a human being from the village where he grew up. If he is still out of our hands, at least in social life, we have isolated him from his race and religion so that he cannot participate equally in thought and action, so that he feels ashamed and does not feel at peace. If we check all of our hands, our hands are covered in blood. None of us are innocent. Why do we do evil? Why do we wrong ourselves and others? Why do we grieve our God? why? So we need to examine ourselves.
Humans being can commit crimes in two ways. One may act unconsciously. He may seem to have done good, said good, done good. But the one who does not understand or sees all his actions in a bad way may feel sorry for him. It can also be registered as a misdemeanor. Such people can be answered through counseling. There is no need to speak evil and push. It is not appropriate. For when they are told to leave, they will soon return.
But the second is a crime that is done knowingly. We can still look at this path in two ways. One is to act with integrity and courage. Deliberately killing or pushing and harassing a person are included in this offense. The other is to commit crimes without an alternative solution. It would have been better if such misdemeanors had not been committed; But they work when we don't need them because the solution is lost or crashed.
A good example of this is "wogayew" that we know in the "iregnaye drama" series. When this woman was separated from her family for education, she suddenly fell in love because she is a woman. She gave herself up to him. And she became pregnant. That is, twin children. But when she came back to the family after her schooling, something else awaited her. She was pregnant enough to give birth, but her mother and father married someone else and ended their efforts to save her. When her family was finishing their wedding party, she was about to give birth. Scared to say that today is tomorrow, Stecher suddenly gave birth on the eve of her wedding. She was confused and the family was shocked. Those who hold lose what they hold. They wanted to hide her for their honor. As a result, she lost her beloved father. The family was exposed to shame and poverty. After a while, she returned with her body full of regret and sought forgiveness, but she did not get what she wanted. That past crime of hers was still being talked about anew by the villagers.
The victim may have many options and solutions to prevent the crime she committed from happening. This is not because she has lost it, but because she does not believe that it is acceptable in terms of the culture and beliefs in which she lives. However, she was looking for a suitable solution in terms of her culture and beliefs. She saw whether she was in the wrong or not in terms of the culture and beliefs she grew up in and knew that she had done something wrong. But if we can look at the issue from many angles, "Did she really do something wrong?" It makes us wonder.
When the apostles asked him to rebuke the woman, Christ said, "If there is no sin among you, let him do this". It is enough to blame her for not committing any crime. A guilty person can never criticize another guilty person. He should say, "Who am I and what shall I say to him?"
Before we point the finger at someone else, we need to practice looking back at ourselves. “This is how it is. It is right to check yourself with "What about me" before saying " why someone is like this".
Bamlaku Abebaw, jimma from abajifar village