ክፍል 1
መተባበርና መሳተፍ
ኢትዮጵያ እድልም ድልም የተቸረች ሀገር እንደሆነች የምናውቀው ስንቶቻችን እንሆን? ስለኢትዮጵያ በዚህ መንገድ ሲገለፅ እውነት የማይመስላቸው ሰዎች እንዳሉ አውቃለው፡፡ ምን አለባት እርስዎ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ይሆኑ እንዴ? ከሆኑ በጣም ይቅርታ፡፡ ሀሳቡ እውነት መሆኑን ግን አምነው እንዲቀበሉ ልመክረዎት እወዳለው፡፡
የቅ/ሲኖዶስ ዋና ፀሃፊ ብፁህ አቡነ ጴጥሮስ “እንደ ኢትዮጵያ ዕድል ተሰጥቶት ዕድሉን ያመከነ ሀገር በዓለም ላይ የለም፡፡” ይላሉ፡፡ አዎ ኢትዮጵያ አድልም ድልም ያለባት ሀገር ናት፡፡ በዚች ሀገር ውስጥ ብዙ ዓይነት ባህልና ቋንቋ፣ ተጠንቶ የማያልቅ ጥበብ፣ ለሁሉ የሚበቃ እውቀት፣ የተፈጥሮ ሀብት በበቂ ክምችት መኖሩና ሌላም ያልጠቀስኩትን በረከት የታደለች ሀገር ናት፡፡ ይሄ ጥንትም የነበረ አሁን ያለ ምንአልባትም በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን አብሮን የሚኖር ነው፡፡ እንድንጠቀመው የተሰጠን፣ እንድንበለፅበት የታደልነው እንዲሁም ሌላውን እንድንረዳበት የተሰቸርነው ነው፡፡ ይህንን እስካላደረግን ድረስ እኛን እየታዘበ አብሮን እንደኖረው ሁሉ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡
ብዙ ባህል የብዙ ጥበብ መገኛ ነው፡፡ ብዙ ቋንቋ የብዙ እውቀት መፍለቂያ ነው፡፡ የተፈጥሮ ሀብት ክምችት መኖሩም እንዲሁ እውቀትና ጥበብ ብቻቸውን ምንም ስለማይሆኑን ወደ እሚታይ፣ እሚዳሰስ፣ የሚለካ፣ የሚቆጠር ተግባር ለማዋል የሚረዳን ግብዓት ነው፡፡
ይህንን የተሰጠንን አድል ወደ ድል ለመቀየር ከኢትዮጵያውያን ሁለት መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮች ይጠበቃሉ፡፡ አንደኛው ልዩነት የማይታይበት ትብብር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አሳታፊነት ነው፡፡
ትብብር የሚያስፈልግበት ምክንያት ማንም ብቻውን ሙሉ ስላሆነ ነው፡፡ የሆነ ነገር ለማድረግ የግድ ከሌላ የምንፈልገው ይኖረዋል፡፡ “እኔ ብቻዬን እበቃለው፡፡” ብሎ የሚያስብ እርሱ አላዋቂ ወይም አዕምሮ ችግር ያለበት ነው፡፡ ይህንን ሀሳቡን አሳድጎት የቀበሌ አመራር ወይም የክልል ወይም የአንድ ብሔር መሪ ሆኖ “እኛ ለአካባቢያችን በቂ ነን፡፡” ብሎ ቢናገር ይህንን ሰው ወደ አማኑኤል የአዕምሮ የህክምና ሴንተር መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚበላውን ዳቦ፣ የሚለብሰውን ልብስ፣ የተጫማውን ጫማ፣ የሰራውን ቤት በሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደተሰራ ከረሳ ይሄ መሪም ተጠሪም መሆን አይችልም፡፡ ሰው ማለት የትብብር መርህን የሚጠብቅና በህብረት መኖርን የሚወድ ማለት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ለዚህ የምንታማ አይደለንም፡፡ በህብረት ለረጅም ዘመን ኖረናል፡፡ በትብብር ሰርተን ኢትዮጵያን ዛሬ ላይ አድርሰናታል፡፡ በትብብር መኖር ምን ያህል ተቃሚ እንደሆነ ዳሰሳ ሳይሰራ፣ ሙህራን ትንታኔ ሳይሰጡበት፣ ፖለቲከኞች ሳይደሰኩሩ አባቶቻችን ኢትዮጰጵያውያን ገብቷቸው በተግባር ሲኖሩት እንደቆዩ ተመልክተናል፡፡ ተፋቅረን ተጋምደን እሴቶቻችንን በጋራ ጠብቀን ዛሬ ላይ ላለው ትውልድ እንዲደርስ ሆኗል፡፡
መተባበር ያለውን አካፍሎ የሌለውን ደግሞ ካለው ተቀብሎ የሚኖርበት የኑሮ መሰረት ነው፡፡ ሁሉም የሚሆነውም የሚኖረውም በህብረት ነው፡፡ ስለህብረት ስናስብ የሰውን ልጅ ብቻ አናስታውስም፡፡ ሌሎች ፍጥረታትም የሚጠቀሙበት የኑሮ መሰረታቸው ነው፡፡ እፅዋት ከእኛ የሚወስዱት እንዳለ ሁሉ እኛም ከእነእርሱ የምንቀበለው አለ፡፡ እንስሳት የሚሰጡን አለ፡፡ የምንቀበላቸው አለ፡፡ ይህንን እውነት የሚጋፋው አዕምሮው በትክክል የማያስብ ሰው ከሆነ ብቻ ነው፡፡
በህብረት ውስጥ ያለው መስተጋብር የሚጎላው በሰዎች መካከል ነው፡፡ ምክንያቱም ከሁሉም ተሽለው በሁሉም ላይ ስልጣን ተሰጥቷቸው የተፈጠሩት ሰዎች ናቸውና፡፡ ከሰኞ እስከ አርብ የተፈጠሩት ፍጥረታት ሁሉ የሰውን ልጅ ጥበቃ ይሻሉ፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ እውቀቱን ጥበቡን ተጠቅሞ የሚሞላው፣ አቅሙን ብርታቱን ይዞ የሚሰራው ብዙ ነገር አለ፡፡ በዚህ ሁሉ ትብብር አስፈላጊ ነው፡፡ አያስፈልግም የሚል ሰው መስራት የማይወድ፤ አዲስ ነገር መፍጠር የሚሳነው ደካማ ከሆነ ነው፡፡
የትብብር አቅም የጎላ መሆኑን ያወቁ ሰዎች ተጠቅመውበታል፡፡ እውቀቱንና ጥበቡን የወሰዱት ከእኛ እስኪመስል ድረስ በህብረት ቆመው የድህነት ታሪካቸውን ፍቀውበታል፡፡ እኛም ብንሆን ወራሪዎቻችን ብንከላከል ይህንን ተጠቅመን ነው፡፡ አሁን ላይ በየትኛውም አቅጣጫ የመጣው ችግር ማሸነፊያው መንገድ ትብብር ነው፡፡
ከመከፋፈል ወደ መተባበር ለመሸጋገር ቁልፉ አንድነችንን የሚያጎለብቱ ተግባራት ላይ መስራት ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱ ለዚህ ምቹ ሁኔታዎችን መጀመር ነው። ሰዎች ሁሉ ተፈጥሮ እንድንዋሃድና በህብረት እንድንኖር እንደሚፈልግ ግንዛቤ ላይ መድረስ አለባቸው። የማይቻለውን ከሰዎች አንጠይቅም፤ ማንም ሰው የማይፈልገውን ነገር እንዲያደርግ አናስገድድም።
“ለምን መተባበር አስፈላጊ ሆነ?” ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡ መተባበር ለ 4 ዋና ዋና ጉዳዮች ያስፈልጋል፡፡
…….. ይቀጥላል፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ከአባጅፋር መንደር
.............................................................................................................................................................
EPISODE 1
Cooperation and participation
How many of us know that Ethiopia is a country blessed with opportunity and victory? I know there are people who do not think it is true when Ethiopia is described in this way. Are you one of them? So sorry if they are. But I would like to advise you to accept that the idea is true.
General Secretary of the Synodos, Abune Petros, said that "There is no country in the world that has been given an opportunity like Ethiopia and has made the most of it." They say. Yes, Ethiopia is a country with Opportunity and victory. In this country, there are many kinds of culture and language, never-ending wisdom, enough knowledge for everyone, abundant natural resources and many other blessings that I have not mentioned. This has existed in the past and will probably exist with us if we continue in this situation. It is given to us to use; we are blessed to thrive, and we are blessed to help others. As long as we don't do this, he will continue to watch over us and continue to live with us.
Many cultures are home to many arts. Many languages are the source of many knowledge. The existence of natural resources is also a resource that helps us to use visible, tangible, measurable, and calculated activities because knowledge and wisdom alone are nothing.
In order to turn this opportunity into a victory, two fundamental issues are expected from Ethiopians. One is cooperation and the other is participation.
Cooperation is necessary because no one is complete alone. In order to do something, we must have what we need from someone else. "I can do it alone." He who thinks so is either ignorant or mentally challenged. He developed this idea and became the leader of a kebele or a region or a nation and said, "We are enough for our area." If he says, it is important to take this person to Emmanuel Mental Medical Center. If he forgets that the bread he eats, the clothes he wears, the shoes he wears, the house he built was built with the help of millions of people, this leader cannot be accountable. A person means one who maintains the principle of cooperation and loves to live together.
We Ethiopians have lived together for a long time. We worked together and brought Ethiopia to where it is today. We have observed that our forefathers, Ethiopians, have been living in practice without conducting a survey on how difficult it is to live in cooperation, without giving an analysis of muhran, and without the support of politicians. Let's love each other and protect our values together and reach the present generation.
Cooperation is the basis of living by sharing what you have and accepting what you have. Everything happens and exists together. When we think of fellowship, we don't just think of humanity. Other creatures also use it as their source of livelihood. Just as plants take from us, we also receive from them. There are animals that give us. We will accept them. Only a person whose mind does not think properly can deny this truth.
The interaction in a union is emphasized between people. Because they are the people who were created to be superior to all and given authority over all. All beings created from Monday to Friday seek the protection of mankind. There are many things that human beings can use their knowledge and wisdom to fill and do with their strength. Cooperation is essential in all of this. Someone who doesn't like to work. Innovation fails if it is weak.
People who have realized the potential of cooperation have taken advantage of it. They stood together and shared their stories of poverty until it seemed that they took the knowledge and wisdom from us. We used this to defend against our invaders. The way to overcome any problem now is cooperation.
The key to moving from division to cooperation is to work on activities that strengthen each other. It is to start favorable conditions for this in every school. All people need to come to the understanding that nature wants us to blend in and live together. We do not ask the impossible from people; We don't force anyone to do anything they don't want to do.
"Why is cooperation important?"
Collaboration is needed for 4 main reasons.
…….. to be continued.
By Bamlaku Abebaw, Jimma, from Abajfar village