የእረኛዬ ፍሬ
በሀገራችን ውስጥ ብዙ ፊልሞች ተሰርተዋል፡፡ ብዙ ቲያትሮች በመድረክ ላይ ታይተዋል፡፡ ብዙ ጭውውቶች ተመልክተናል፡፡ ብዙ የቴሌቭጅንና የሬዲዮ ተከታታይ ድራማዎች ቀርበዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ በቀረቡበት ዘመን በእርግጠኝነት ከአቀራረባቸው ጀምሮ እስከ አስተላለፉት መልዕክት እንከን አልባ ሆነው አልፈው ይሆናል፡፡ ይሄ መልካም ነው፡፡ እኔ የዛሬ ትውልድ አባል ነኝ፡፡ መመስከር የምችለው በእኔ ዘመን ስለሆነውና ስላየውት ነገር ብቻ ነው፡፡
እረኛዬ ተከታታይ ድራማ በእኔ ዘመን ያለ እጅግ ተወዳጅ ድራማ ነው፡፡ ተወዳጅ ያደረገው ደግሞ ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው በድራማው ውስጥ ያሉት ተዋንያን በመምሰል ሳይሆን በመሆን እየተወኑ መሆናቸው ነው፡፡ ሲከፉ፣ ሲደሰቱ፣ ሲራመዱ፣ ሲናደዱ፣ ሲወድቁ፣ ሲነሱ፣ ሲማቱ፣ ሲጣሉ፣.....ወዘተ የእውነት ነው የሚመስለው፡፡ ሆኖ መተወን ማለት ይሄ ነው፡፡ ሁለተኛው ለተመልካቹ ይዞት የተነሳው ጭብጥ ወቅቱን የጠበቀና ሀገራዊ በመሆኑ ነው፡፡ ለሽማግሌ ወይም ለወጣት ወይም ለሴት ወይም ለወንድ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የሚሆን ሀሳብ ይዞ የመጣ በመሆኑ ተወዳጅ ያርገዋል፡፡
በእረኛዬ ተከታታይ ድራማ ውስጥ ብዙ እውቀቶች አሉ፡፡ ብልህ የሆነ ለቅሟቸዋል፡፡ ሞኝ የሆነ ደግሞ እንደነገሩ አልፎ ይሆናል፡፡ ፊልምም ሆነ ድራማ ቲያትርም ሆነ ጭውውት ሲሰራ አንድ ቁም ነገር ለማስተላለፍ ታስቦ ነው፡፡ እንጅ ሳቅ ብቻ ፈጥሮ ዘወር ለማት አይደለም፡፡ አላስፈላጊ ነገር አሳይቶም ተመልካችን ግራ ለማጋባትም አይደለም፡፡ የተሻለ ሀሳብ በአዕምሮ ውስጥ ለመጫን እንጅ፡፡ የተሻለ ሀሳብ ያለው ሰው ደግሞ የተሻለ ስራ ለመስራት በእጅጉ ይረደዋል፡፡
በዚህ ተከታታይ ድራማ ውስጥ በየክፍሉ ያሉትን መልካም ሀሳቦች በዚህ ብሎግ ውስጥ እኔ እንዲህ አድርጌ አቅርቤያቸዋለው፡፡ ይህንን ያደረኩበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ድራማውን በብዙ ምክንያት መከታተል የማይችሉ እንደሚኖሩ ስለማስብ ቁምነገሩ እንዲያመልጣቸው ስላልፈለኩ ነው፡፡ ይሄ ድራማው ላመለጣቸው ብቻ ሳይሆን ተመልክተው ቁም ነገሩን ለዘነጉትም ጭምር ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ግልፅ ማድረግ እፈልጋለው፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ፣ ከአባ ጅፋር መንደር
............................................................................................................................................
"EREGNAYE MOVIE"
Many films have been made in our country. Many plays were performed on the stage. We have seen many conversations. Many television and radio serials have been produced. All of these must have gone flawlessly from their presentation to the message they conveyed. This is good. I belong to today's generation. I can only testify about what happened in my time and what I saw.
"EREGNAYE MOVIE" series is one of the most popular Movie of my time. Two things made it popular. One is that the actors in the Movie are acting, not acting. When they are angry, happy, walking, angry, falling, getting up, kissing, fighting, etc., it seems real. This is what it means to let go. The second is that the theme brought to the viewer is contemporary and national. It is not only for the old or the young or the woman or the man, but because it comes with ideas for everyone, it makes it popular.
There is a lot of knowledge in the Shepherd series. He left them a smart one. A fool will pass away as they say. Whether it is a film or a Movie, a theater or a conversation, it is meant to convey a certain point. But it's not for those who just laugh and turn around. It is not to confuse our audience by showing unnecessary things. Instead of pressing a better idea into the mind. A person with a better idea will be greatly helped to do a better job.
I have presented the good ideas of each episode in this Movie series. The main reason I did this is because I don't want them to miss the point because I think there are people who can't watch the drama for many reasons. I want to make it clear that this drama is not only for those who missed it, but also for those who watched it and forgot about it.
Bamlaku Abebaw jimma from abajifar village)