የቀጠለ…
ክፍል 1
መተባበርና መሳተፍ
“ለምን መተባበር አስፈላጊ ሆነ?” ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡ መተባበር ለ 4 ዋና ዋና ጉዳዮች ያስፈልጋል፡፡
መተባበር ለህልውና ያስፈልጋል፡፡ መተባበር ለራሳችን ህልውና እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የምንተባበረው ለመንግስት ጥቅም ብቻ ብለን አይደለም፡፡ እኛ መኖር ምንችለው እነእርሱ መኖር ሲችሉ ነው፡፡ እንኳን ሰውን ያህል ትልቅ ፍጥረት ይቅርና ባክቴሪ እና ቫይረስ እንኳን ከምድር ከጠፉ ዓለም ትቀያየራለች፡፡ እፅዋት ከአካባቢችን ቢርቁ የእኛ ህልውና አደጋ ነው፡፡ ሰው የሆነ ሁሉ የሚኖረው ሰው ስላለ ነው፡፡ አንድ ሰው ብቻውን በረሃ ውስጥ መኖር አይችልም፡፡ አስር ከሆኑ ግን መኖር ይችላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚቸገር ሰው ብዙም አይታይም ነበረ፡፡ ምክንያቱም ትብብር ስላለ ነው፡፡ በአንድ አንድ ቦታ ደቦ በሌላ አካባቢ ደግሞ ወንፈል የምንለው የደከመን የምናበረታበት ነው፡፡ እሩብ የምንለውም በተለይ በሰርግና በሌሎች ድግሶችም ትብብራችንን የምናሳይበት ትልቅ የባህል እሴታችን ነው፡፡ ቤት ሲሰራ፣ እርሻ ሲታረስ፣ አረም ሲታረም፤ በለቅሶው በሀዘኑ ሁሉ ተባብረን ከሰራን መሻገር ቀላል ነው፡፡ በእራኛዬ ድራማ ውስጥ በተለይ በመጀመሪያው ክፍል ያሳየን ይህንን ነው፡፡
ብቻውን የሆነ ማህበረሰብ ሆነ ብቻውን የቆመ ሀገር ህልውናው አደጋ ውስጥ ነው፡፡ አውሮፓውያውን የአውሮፓ ህብረት ብቻውን አልበቃ ስላላቸው ኔቶ የሚባል መከላከያ ገንብተዋል፡፡ ሌሎች ሀገራት ደግሞ “እባካችሁ የህብረታችሁ አካል አደርጉል” እያሉ በየቀኑ ማመልከቻ ያስገባሉ፡፡ ይሄ የሆነበት ዋናው ምክንያት በአሁን ዘመን በተናጠል ህልውናን ማስቀጠል ስለማይቻል ነው፡፡ በእኛ ሀገር ደግሞ በተቃራኒው “እባካችሁ እኛም መገንጠን እንፈልጋለን” የሚሉ እንመለከታለን፡፡ ይሄ ትክክል አይደለም፡፡
መተባበር እንድንሻሻል እና እንድናድግ ይረዳናል። ብቻን ማደግ አይቻልምም፡፡ አይጠቅምም፡፡ ይሄ ስስታም ፀባይ ያላቸው እና ገና ከጫካ ያልወጡ ሰዎች ሀሳብ ነው፡፡ አንድ ሰው የሚበለጽገው በእራሱ ጉልበት ብቻ ሰርቶ፣ በራሱ ቅንጭላት ብቻ አስቦ፣ የእራሱን እውቀት ብቻ ተጠቅሞ፣ የራሱን ጥበብ ተጠቦ ብቻ አይደለም፡፡ በሌላውም ጭምር እንጅ፡፡ የትኛው ሰው፣ የትኛው ሀገር፣ የትኛው ድርጅት ነው በራሱ እቅድ፣ በራሱ የሰው ሃይል፣ በራሱ በጀት ብቻ ሰርቶ ለስኬት የበቃው? የለም፡፡ የራሱን ከሌላው ጋር እየደመረ እንጀ፡፡
አንድ ማህበረሰብ ወይም ሀገር ሊበለፅግ የሚችለው በሌላው ማህበረሰብ ወይም ሀገር ነው፡፡ ለምሳሌ ማብራትን የሰሩት የሌሎች ሀገራት ሰዎች ናቸው፡፡ ሮኬትን የፈበረኩት ሌሎች ናቸው፡፡ በአብዛኛው አሁን የምንጠቀመው ሁሉ የመጣው ከሌላ ሀገር ነው፡፡ እኛ በሌላው ሀገር ምክንያት የበለፀገ ኑሮ መኖር እየቻልን ነው፡፡ አፍሪካ ሀገራት በአብዛኛው በእኛ ምክንያት ነው ከወረራ ነፃ የወጡት፡፡
እርሻን ያስተማረ ማህበረሰብ ስላለ ነው ሌላውም እየተጠቀመበት ያለው፡፡ የሆነ ማህበረሰብ ልብስ ሸምኖ መልበስ ጀመረ ሌላውም ያንን እያዬ ተከተለ፡፡ መተባበር በጋራ ማደግን ያመጣል፡፡ በመተባበር የሚያምን ሰው አሁንም ታሪክ መስራት እንደሚችል መጠራጠር አያስፈልግም፡፡
ነገር ግን በህብረት ለመቆም የሚያንገራግር እና ለመተባበር ዝግጁ ያልሆነ ሰው ወይም ማህበረሰብ ወይም ሀገር መቀየር አይችልም፡፡ ከድህነት መላቀቅ አይችልም፡፡ አዲስ ነገር መፍጠር አይችልም፡፡
መተባበር ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ማህበረሰቡን ያገለግላል፡፡ መተባበር ለሞራል ግንባታ ይጠቅማል፡፡ እሴቶቻችን ተጠብቀው የሚቆዩት፣ ነፃነታችንን ማንም የማይደፍረው ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለመፍጠርም ሆነ ለመስራት ድፍረት የምናገኘው የመተባበር ባህል ሲኖር ነው። ይሄ ባል ካለ ሳናስበው የሚሆን፣ ሳንጠይቅ የሚሰጠን፣ ኮሚቴ ሳናዋቅር ህግ ሳናወጣ የሚተገበር ነገር ኖራል፡፡ ሁላችንም ተባብረን ስንሰራ በፍጥነት ትላልቅ ነገሮችን እናሳካለን። ሁላችንም የምናዋጣው ነገር አለንና።
ሌላው በህይወታችን ውስጥ ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንገናኛለን፡፡ እነዚህ ሰዎች እኛ የማናውቀውን ነገር ላያውቁ ይችላሉ፡፡ እነእርሱ ደግሞ እኛ የምናውቀውን ላያውቁ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም እርስ በርሳችን የምንገናኝ ከሆነ እንኳን መግባባት ችለን ይቅርና መግባባት ባንችልም እርስ በርስ እንማማራለን፡፡ የማይቻል የሚመስለውን ነገር ማድረግ እንድንችል እድል እናገኛለን፡፡ ይሄ መተባበር የሚሰጠን ትልቅ ሚስጥራዊ ሃይል ነው፡፡
መተባበር ድፍረት ይሰጣል፡፡ ሰው በምድር ሲኖር በራሱ ማድረግ የሚችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሁሉ ከእርሱ አቅም በላይ የሆኑ ነገሮች ያጋጥሙታል፡፡ አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ የማድረግ አቅም ቢኖረውም ብቸኛ በመሆኑ ፍርሃት ይከብበውና ሳያደርገው ይቀራል፡፡ ይሄ በግለሰብ ብቻ ሳይሆን ብቻውን በሆነ በማህበረሰብ የሚስተዋል እውነት ነው፡፡ በሀገር ደረጃም ከፍ ሲል ደግሞ በአህጉርም ደረጃ የምናየው ነው፡፡
በግል ደፋር የምንሆነው ከእኛ ጋር የሚተባበረን እንዳለ ስንረዳ ነው፡፡ ሀሳባችን ሀሳቡ የሆነ፣ ምን እንደጎደለንና ምን እንደሚያስፈልገን ያወቀ፣ ልናደርግ የወደድነውን የወደደ፣ ….ወዘተ ሰው ካገኘን ደስ ይለናል፡፡ ይሄ ሰው ከጎናችን መሆኑን ስናውቅ ደግሞ የበለጠ ደስ ይለናል፡፡ የፈለግነውን ለማድረግ ደግሞ ከጎናችን እንደሆነ ሲነግረን ደግሞ ደፋር ሆነን እንበረታለን፡፡
እንደ ብሔር ደግሞ ካሰብነው አንድ ብሄር ደፋር የሚሆነው ሌላኛው ብሄር ከጎኑ እንደሆነ ካወቀ ነው፡፡ መብት ሲጣስ እንዲከበር የሚደረገው ወይም ህግ እንዲረቅ መዋቅር እንዲዘረጋ የሚደረገው በአንድ ብሄር ጩኸት ብቻ አይደለም፡፡ በህብረት እንጅ፡፡ አንድ ብሄር ይህንን ለማድረግ ድፍረት ሊኖረው አይችልም፡፡ ያሳለፈውን ህይወት ማሻሻል ሳይችል እየደጋገመ ይኖራል፡፡
አንድ ሀገር ብቻውን ፈሪ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ፡፡ ጠላትን ለመከላከል፣ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ፣ የአየር ንብረት መዛባትን ለመጠበቅ፣ …...ወዘተ ትብብር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ መስራቅ አፍሪካ ውስጥ ያለውን ሰላም ማስጠበቅ የሚቻለው በዚህ አካባቢ ያሉ ሀገራት ሲተባበሩ ብቻ ነው፡፡ የአየር ንብረት መዛባትን ለመጠበቅ የግድ የአለም ሀገራት በትብብር መሆን አለበት፡፡
ትብብር ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለም ሀገራት ውስጥ የሚሰራ ሀያል ነገር ነው፡፡ ላለመተባበር የወሰነ ሰው ላለመደመር የፈለገ ማህበረሰብ እና ሀገር ወደፊት መሄድ አይችልም፡፡
ሁለተኛው የተሰጠንን እድል ወደ ድል የምንቀይረው በሁሉም ነገር ላይ ሁሉም ማህበረሰብ ተሳታፊ የሆነበት ስራ ሲሰራ ነው፡፡ ስራ በህብረት ሊሰራ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው ያመነበት፣ የተስማማበት፣ የመከረበትና ሀሳብ የሰጠበት መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን በጋራ የሰራነውን ስራ ለኪሳራ ሊዳርገው ይችላል፡፡ የአንድ ሀገር ህዝብ በመተባበር የሰራውን ትልቅ ሀገራዊ ልማት አንድ ሰው ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ለዚህ ነው አሳታፊነት የሚያስፈልገው፡፡
የአሳታፊነት ችግር በሀገር ደረጃ ማየት ይቻላል፡፡ እያየንም ነው፡፡ መሰረተ ልማቶች የሚወድሙት፣ የሚሰራውን ሁሉ እያጣጣሉ የሚናገሩ፣ ህዝቡን ለአመፅና ለሁከት የሚያነሳሱ ሰዎች በሁሉም ተሳታፊ ስላላደረግናቸው ነው፡፡ በክብር ጠርተን ምን ብንሰራ መልካም እንደሆነ ጠይቀናቸው ፣ እነእርሱ ካነሱት በተጨማሪ እኛ ያሰብነውን ነግረናቸው፣ በጋራ መክረን፣ እነእርሱ እኛን ሰምተውን እኛም እነእርሱን ሰምተን ያፀደቅነው ሃሳብ ከሆነ የተተገበረው የእኛም የእነእርሱም ስለሚሆን ተጠቃሚ እንጅ የሚያፈርስ አይኖረውም፡፡ ደስታችን ሙሉ የሚሆነው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ያላሳተፍነው ሰው በአንድም ሆነ በሌላ ይጎዳናል፡፡
እኛ ሀገር ላይ የሆነ ፕሮጀክት ሲቀረፅ፣ የሆነ አጀንዳ ሲፀድቅ የሚጠሩት ሰዎች ማህበረሰቡን የሚወክሉ ናቸው ቢባልም እውነታው ግን ይሄ አይመስልም፡፡ ማህበረሰቡ ያለበት ችግር እና እነእርሱ የሚናገሩት ለየቅል ሆኖ እያስተዋልን ነው፡፡ ለዚህ ነው አገልግሎት ሳይሰጥ የሚያበቃው፡፡ የአካባቢው ችግር ንፁ የመጠጥ ውሃ ሆኖ ደን ብንተክልልት ደኑ የችግሩ መፈትሔ አይመስለውም፡፡ ለዚህም ከመንከባከብና ከመጠበቅ ይልቅ ጠባቂው በሌለ ሰዓት እየቆረጠ አጥር ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ የደስታችን ተካፋይ ከመሆን ይልቅ የችግራችን ምንጭ የሚሆኑት ያላሳተፍናቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያን ሀዘን ውስጥ የሚከቷት ቦታ የነፈግናቸው አካላት ናቸው፡፡ አይመለከታቸውም ብለን የናቅናቸው ወይም ትኩረት ያላደረግንባቸው ሰዎች በተደጋጋሚ የችግሮቻችን ምንጭ ሲሆኑ አይተናል፡፡ አሁን ይሄ የገባን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ሁሉን ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ የሚያደርግ የውይይት መርሃ ግብር እየተዘጋጀ ነውና፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ መናገር ፈልጎ የሚከለከል፣ መተንፈስ አምሮት ተው የሚባል መኖር የለበትም፡፡ ሀሳቡ የሚጣል፣ እውቀቱም የሚናቅ ሰው እንዲኖር መፍቀድ የለብንም፡፡
አዘጋጅ፤ ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ከአባጅፋር መንደር
.......................................................................................................................................
Continued…
Cooperation and participation
Cooperation is necessary for survival. Cooperation is vital to our survival. We are not cooperating only for the benefit of the government. We can live only when they can live. If even bacteria and viruses disappear from the earth, let alone a creature as big as a human being, the world will change. If plants are removed from our environment, our existence is in danger. Everything that is human exists because there is a human being. One cannot live alone in the desert. But if you are ten, you can live.
It was rare to see a person in trouble in Ethiopia. Because there is cooperation. In one place, we call it "Debo" and in another area, "Wenwel" where we encourage the tired. It is our great cultural value to show our cooperation especially in weddings and other parties. When building a house, plowing a field, weeding; It's easy to get through it if we work together through all the crying and all the sadness. This is what he showed us in the first part of the drama.
The survival of a single society or a single country is in danger. They said that the European Union alone is not enough, so they built a defense called NATO. And other countries submit applications every day, saying, "Please make me part of your union." The main reason for this is that it is impossible to survive in isolation these days. In our country, on the contrary, we see people saying, "Please, we also want to separate." This is not correct.
Collaboration helps us improve and grow. It is not possible to grow alone. It doesn't help. This is the opinion of people who have a bad temper and are not out of the woods yet. A person does not prosper only by working with his own energy, thinking only by his own details, using only his own knowledge, and only by his own wisdom. But also the other. Which person, which country, which organization is successful with its own plan, its own human resources, its own budget? There is none. Let's start adding one's own to another's.
A community or country can only prosper through another community or country. For example, people from other countries made the lighting. Others invented the rocket. Almost everything we use now comes from another country. We are able to live a prosperous life because of the other country. African countries are mostly freed from invasion because of us.
It is because there is a community that has taught farming and another is using it. One community started weaving clothes and another followed suit. Cooperation leads to mutual growth. There is no need to doubt that anyone who believes in cooperation can still make history.
But a person or a society or a country that is hesitant to stand together and is not ready to cooperate cannot change. He cannot escape from poverty. It cannot create anything new.
Collaboration serves society in a mysterious way. Cooperation is good for morale building. It is only when there is a culture of cooperation that our values are preserved, that no one dares our freedom, and that we find the courage to create and act. If this husband exists, there will be things that happen without us thinking, things that are given without asking, things that are implemented without making a law without setting up a committee. When we all work together, we accomplish great things faster. Because we all have something to contribute.
Another is that we meet different people in our life. These people may not know something that we don't. And they may not know what we know. Therefore, even if we meet each other, we learn from each other even if we can't understand each other. We get the chance to do the seemingly impossible. This cooperation gives us a great secret power.
Cooperation gives courage. When a person lives on earth, there are things that he can do on his own, but he also encounters things that are beyond his control. Even if he has the ability to do it once, he is alone, so fear surrounds him and he does not do it. This is true not only of the individual but also of the community. We see it at the national level and at the continental level.
We become personally courageous when we understand that there is someone who is with us. We will be happy if we find someone who shares our thoughts, who knows what we lack and what we need, who likes what we like to do, etc. And when we know that this person is on our side, we are even happier. And when he tells us that he is on our side to do what we want, we become brave and strong.
If we think about it as a nation, one nation becomes brave if it knows that the other nation is on its side. When rights are violated, it is not only the cry of one nation that enforces laws or structures. But collectively. A nation cannot have the courage to do this. He keeps repeating the life he has lived without being able to improve it.
There is an opportunity for a country to become a coward. To prevent the enemy, to make poverty history, to protect climate change, etc., cooperation is essential. Peace in East Africa can only be maintained when countries in the region work together. In order to prevent climate change, the countries of the world must cooperate.
Cooperation is a powerful thing that works not only in Ethiopia but in the countries of the world. People who decide not to cooperate, a society and a country that wants to not join cannot move forward.
The second is that we turn the opportunity we have been given into a victory when the whole community is involved in everything. Work can be done collaboratively. But it should be something everyone believes in, agrees with, advises and gives advice to. Even one person can ruin the work we have done together. One person can make the great national development that the people of a country have done in cooperation useless. This is why participation is needed.
The problem of participation can be seen at the country level. We are watching. Infrastructures are destroyed, people who speak disparagingly about everything that is done, who incite the people to violence and violence because we did not make them all participants. We respectfully called them and asked them what we should do. In addition to what they mentioned, we told them what we thought, and we advised them together. This is when our joy is complete. Someone we don't involve will hurt us in one way or another.
In our country, when a project is formulated and an agenda is approved, it is said that the people who are called represent the community, but the reality is that this is not the case. We are noticing the problems of the society and what they are talking about. That's why it ends up not being served. The problem of the environment is clean drinking water and if we plant a forest, the forest does not seem to be the solution to the problem. For this reason, instead of taking care and protecting, the guard cuts and builds a fence in his spare time. Oftentimes, instead of being part of our happiness, it is the people we don't involve who are the source of our problems.
The place that puts Ethiopia in grief is the elements we have lost. We have often seen people we ignore or pay no attention to become the source of our problems. I think we've got this now. Because a dialogue program is being prepared that will involve all Ethiopians. There should not be anyone who wants to speak on this program and is not allowed to breathe. We must not allow a person whose ideas are thrown away and whose knowledge is despised.
By Bamlaku Abebaw, jimma from abajifar village