know more about your kidney ደም እንዴት ይጸዳል? /How blood is clean? How is urine produced? / ሽንትስ እንዴት ይፈጠራል?

 


ደም እንዴት ይጸዳል? 

            ሽንትስ እንዴት ይፈጠራል?

    በደም ንፅህና ሂደት ውስጥ ኩላሊቶች ከፍተኛ ተግባርና ሚና አላቸው፡፡ ሁሉንም አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ፡፡ ያጣራሉ፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ ፈሳሽ፣ ኤሌክትሮላይቶችን እና ቆሻሻዎችን በመምረጥ ያስወግዳል፡፡ 

     ይህንን ውስብስብ እና አስገራሚ የሽንት መፈጠር ሂደት በደንብ እንረዳው፡፡ በየደቂቃው እስከ 1200 ሚሊ ሊትር ደም ወደ ኩላሊት ለመጣራት ይገባል፡፡ ይህም ከልብ ተገፍቶ ከሚወጣው አጠቃላይ 20 በመቶው መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ በአንድ ቀን ውስጥ 1700 ሊትር ደም ይጸዳል ማለት ነው፡፡ ደግማችሁ አንብቡትና ምን ያህል አስገራሚና ድንቅ እንደሆነ ትረዳላችሁ፡፡

      ይህ የማጣራት ሂደት የሚካሄደው በትናንሽ የማጣሪያ ክፍሎች ውስጥ ነው፡፡ እነዚህም “ኔፍሮን” ይባላሉ፡፡ እያንዳንዱ ኩላሊት አንድ ሚሊዮን ገደማ ኔፍሮን እና እያንዳንዱ ኔፍሮን ደግሞ የተሰራው ከግሎሜሩለስ እና ቱቡልስ ተብሎ ከሚጠራ በኩላሊት ውስጥ ከሚገኝ ነገር ነው፡፡  ግሎሜሩሊ የሚባሉት ደግሞ በጣም ጥቃቅን ቀዳዳዎች ያሉት ሲሆን የማጣራት ስራን የሚሰራ ነው፡፡ ውሃ እና አነስተኛ መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች በቀላሉ  ያልፋሉ፡፡ ነገር ግን ትልቅ መጠን ያላቸው እንደ ቀይ የደም ሴሎች፣ ነጭ የደም ሴሎች፣ ፕሌትሌቶች፣ ፕሮቲን ወዘተ በእነዚህ ቀዳዳዎች ውስጥ ማለፍ አይችሉም። ስለዚህ እንደነዚህ ያሉት ሴሎች በተለምዶ በጤናማ ሰዎች ሽንት ውስጥ አይታዩም፡፡ መታየትም የለባቸው፡፡


ትልቁ ነጥብ፤  የኩላሊት ዋና ተግባር ቆሻሻን እና ጎጂ ተረፈ ምርቶችን እና ከመጠን በላይ ውሃን በሽንት መልክ ማስወገድ ነው፡፡

የሽንት መፈጠር የመጀመሪያው ደረጃ በግሎሜሩሊ ውስጥ ይከሰታል፡፡ በደቂቃ 125 ሚሊ ሊትር ሽንት ይጣራል፡፡ በ 24 ሰአታት ውስጥ 180 ሊትር ሽንት መፈጠሩ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ በውስጡም ቆሻሻዎችን፣ ኤሌክትሮላይቶችን እና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ብቻ ሳይሆን ግሉኮስ እና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ያካትታል፡፡

 በዚህ ብልህ እና ትክክለኛ ሂደት ሁሉም አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እና 178 ሊትር ፈሳሽ በቧንቧዎች ውስጥ እንደገና እንዲዋሃዱ ይደረጋሉ፡፡ ነገር ግን 1-2 ሊትር ፈሳሽ, ቆሻሻ እና ሌሎች ጎጂ ንጥረ ነገሮች ይወጣሉ፡፡  በኩላሊት የተፈጠረው ሽንት ወደ ዩሬተር ይፈስሳል፡፡ እና በሽንት ፊኛ ውስጥ ያልፋል እና በመጨረሻም በሽንት ቱቦ ውስጥ ሽንት ሆኖ ይወጣል።


ጤናማ ኩላሊት ባለው ሰው ውስጥ የሽንት መጠን መለዋወጥ ሊኖር ይችላል? 

    አዎ። የውሃ ፍጆታ መጠን እና የከባቢ አየር ሙቀት  በአንድ ሰው ሰውነት ውስጥ የሽንት መጠን የሚወስኑ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። የውሃ ፍጆታ ዝቅተኛ ከሆነ ሽንት መጠኑ ይቀንሳል፡፡ (500 ሚሊ ሊትር ያህል ያነሰ ሊሆን ይሆናል)፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ሲጠጣ, ብዙ ሽንት ይፈጠራል፡፡ በበጋው ወራት, በከፍተኛ የአካባቢ ሙቀት ምክንያት በሚፈጠር ላብ ምክንያት የሽንት መጠኑ ይቀንሳል፡፡ በዚህ ምክንያት የሽንት መጠኑ ካነሰ እስከ 500 ሚሊ ሊትር ወይም ከበዛ እስከ 3000 ሚሊ ሊትር በላይ ከፍ ሊል ይችላል፡፡ ይህ ጉዳይ ኩላሊቶቹ የበለጠ ትኩረት እና ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልጋቸው ሊያመለክት ይችላል፡፡

ዋ.ነ   በጣም ትንሽ ወይም በጣም ብዙ የሆነ የሽንት መፈጠር፤ ኩላሊት ትኩረት እና ምርመራን እንደምትፈልግ አመልካች ነው፡፡


ምላኩ አበባው. ጅማ 

..................................................................................................................................


How is blood purified?
             How is urine produced?
     Kidneys have a great function and role in the process of blood purification. They contain all the essential ingredients. They check. It selectively removes excess fluid, electrolytes and impurities.
      Let's better understand this complex and fascinating process of urine formation. Every minute, up to 1200 milliliters of blood must be pumped into the kidneys. This is about 20 percent of the total output from the heart. So, it means that 1700 liters of blood is cleaned in one day. Read it again and you will understand how amazing and wonderful it is.
       This refining process takes place in small filtration chambers. These are called "nephrons". Each kidney has about one million nephrons, and each nephron is made up of substances inside the kidney called glomeruli and tubules. The glomeruli have very small pores and perform filtration. Water and small amounts of substances pass through easily. But larger size like red blood cells, white blood cells, platelets, protein etc. cannot pass through these pores. Therefore, such cells are not normally seen in the urine of healthy people. They don't even have to be seen.

The big point is; The main function of the kidneys is to remove waste and harmful waste products and excess water in the form of urine.
The first step in urine formation occurs in the glomeruli. 125 ml of urine is filtered per minute. It is amazing that 180 liters of urine is produced in 24 hours. It contains not only wastes, electrolytes and toxins, but also glucose and other important nutrients.
  In this clever and precise process, all the essential ingredients and 178 liters of liquid are recombined in the pipes. But 1-2 liters of liquid, dirt and other harmful substances come out. Urine produced by the kidneys flows into the ureters. And it passes through the bladder and finally comes out as urine in the urethra.

Can urine volume fluctuate in a person with healthy kidneys?
     yes. Water consumption and ambient temperature are the main factors that determine the amount of urine in a person's body. If water intake is low, urine volume will decrease. (May  be less than 500 ml). But when drinking large amounts of water, more urine is produced. During the summer months, the amount of urine decreases due to sweating caused by high ambient temperatures. As a result, the urine output can be as low as 500 mL or as high as 3000 mL. This may indicate that the kidneys need more attention and further testing.
Main point. Production of too little or too much urine; Kidney is an indicator that you need attention and investigation.


Bamlaku abebaw, jimma from abajifar vilage
key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post