“በብርሃን የማይጠፋ ጨለማ እንደሌለ ሁሉ በእውቀትም የማይገኝ የችግር መፍትሔ አይኖርም፡፡ ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ /// "Just as there is no darkness that cannot be extinguished by light There is no solution to a problem that cannot be found in knowledge. Prime Minister Dr. Abiy Ahmed

 



“በብርሃን የማይጠፋ ጨለማ እንደሌለ ሁሉ

በእውቀትም የማይገኝ የችግር መፍትሔ አይኖርም፡፡                                                     ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ

 

     ጨለማ የኖረበት ዋናው ምክንያት ብርሃን ስለሌለ ነው፡፡ ጥዋት በብርሃን የተጀመረው ብሩህ ቀን ድምቅ ብሎ ይውልና ማታ ላይ በጨለማ ይከበባል፡ ለምን? ያልን እንደሆነ ብርሃን የምትሰጠን ፀሐይ ከእኛ ዘወር በማለቷ ይሆናል፡፡እኛም ይሁን ብለን እንሸኛታለን፡፡ ምክንያቱም ግብፆች አባይን እኛ ብቻ ነን መጠቀም ያለብን ብለው እንደሚከራከሩት አይደለንምና፡፡ ሌሎቹም የፀሐይን ብርሃን የሚፈልጉ ስላሉ ደስ ብሎን እንሸኛታለን፡፡ ደስ ብሎን ስንሸኛት ግን በእኛ ላይ ድቅድቅ ጨለማ እንደሚመጣ ሳንዘነጋ ነው፡፡

ጨለማ የሚመጣው ወዲያው ፀሀይ እንደጠለቀች ነው፡፡ ይህም ጨለማ የሚመጣው ብርሃን ባለመኖሩ ምክንያት እንደሆነ ሀቅ ነው ማለት ነው፡፡ ጨለማ ከባድ ነው፡፡ ጨለማ ጭንቀትን የሚፈጥር ሰላምን የሚነሳ ነው፡፡ ማንም ሰው ጨለማን የሚያፈቅር የለም፡፡ በዚህም የተነሳ ሰዎች ጨለማን ለማሸሽ የተለያዬ አማራጭ ይጠቀሙ ነበር፡፡

   የተለያዩ ፈጠራዎችንም ለመፍጠር ብዙ ይደክሙ ነበር፡፡ ለምሳሌም፤ በመጀመሪያ እሳትን በመፍጠር አሳዩ፡፡ በመቀጠልም በእጅ በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ ብርሃን የሚሰጡአንድ አንድ ነገሮችን ፈበረኩ፡፡ ሌሎችንም ብዙ ጨለማን የሚቀንሱ መፍትሔዎችን ለመስራት ደከሙ፡፡ ተሳካላቸውም፡፡ በዚህም አሉ በዚያ ለጨለማው ችግር የሰጡት መፍትሔ ማብራት ቦግ ማድረግ ነበር፡፡

   ጨለማ የአለማወቅ፣ የድንቁርና፣ የመሃይምነት፣ የችግር ምሳሌ ነው፡፡ ብርሃን ደግሞ የእውቀት፣ የትምህርት፣ የስልጣኔ፣ የመፍትሔ ምሳሌ ነው፡፡ አለማወቅን ለማጥፋት የሚያውቅን መጠየቅና ማንበብ ፣ መሐይምነትን ለማጥፋት ደግሞ መማር እስፈላጊ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከልጅነቱ ጀምሮ ነገሮችን ሁሉ ወደ አዕምሮው እያስገባ አቅሙ የፈቀደውን ያህል እየተረዳ እውቀትን እያገኘ ይሄዳል፡፡ 

   የሰው ልጅ ሲማርና ሲያውቅ ደግሞ ባለው ላይ አዲስ ነገር እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ወደ ትምህርት ቤት በመግባት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አዳዲስ እውቀቶችን እየሸመተ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ በመዝለቅ በራሱ ላይ እና በወገኑ ላይ ለውጥ እንዲያመጣ ተደርጎ ይወጣል፡፡ 

 ሰው በዚህ ሁሉ መስመር እንዲያልፍ ሲደረግ ጨለማ ሆኖ መንገድ ለሚከለክል ችግር ሁሉ መልስ መስጠት ይችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ብርሃን በመለኮስ መፍትሄ እንደሚሰጥና መንገዱን ብሩህ እንደሚያደርግ ይገመታል፡፡ ማንኛውም ችግር የራሱ የሆነ መፍትሄ አለው፡፡ መፍትሔውን ለማግኘት ግን እውቀትን በያዘ መነፅር መፈለግና ማየት ያስገልጋል፡፡ የሰው ልጅ ከኮሌጅ ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ በዲግሪና በማስተርስ ተመርቆ ሲወጣ ለችግሮች መፍትሔ ያገኛል ተብሎ ስለሚጠበቅ ሰው ሁሉ ከዛሬ ነገ እንዲህ አደረገልን እያለ መጓጓት ይጀምራል፡፡ ተምሮ መጥቶ ካልተማሩት ጋር እኩል በችግር የሚቸገር ከሆነ ዳ/ን ዳንኤል ክብረት እንዳለው ዲግሪው የአውራ ዶሮ ዲግሪ ነው ብለው የቡና መጠጫ ያደርጉታል፡፡ የወሬ ማድመቂያ ያደርጉታል፡፡ በእኛ ሀገር ያሉ እናቶች ልጃቸው ዩኒቨርስቲ ሲገባ በደስታ ጮቤ ይረግጣሉ፡፡ ተመርቆ ሲመጣ ደግሞ ያለ የሌለ አቅማቸውን ተጠቅመው ይደግሳሉ፡፡

ጉጉታቸው ደግሞ ከዛሬ ነገ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ምክንያቱም ተምሮ ስለመጣ ብዙ አንገብጋቢ ችግሮችን ማቅለል ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰብ በበኩሉ ተመርቆ መጣ ከተባለው ተማሪ ብዙ ይጠብቃሉ፡፡  መጠበቃቸው ልክ ናቸው፡፡ በእነእርሱ ባልተማሩትና በተማረው ሰውዬ መካከል የሚኖረው ልዩነት የመማርና አለመማር ብቻ ሳይሆን ለችግር መፍትሔ መስጠትና ያለመስጠትም ጭምር ነው፡፡ በቤተሰብ ውስጥ ካለው ትንሽ ችግር አንስቶ እንደ ሀገር ከገጠመን ውስብስብ ችግር ድረስ መፍትሔ የሚጠብቁት ከተማረው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ የተማረው ሀይል ከፍተኛ አደራ አለበት፡፡

 ኢትዮጵያ ሀገራችን እስከ አሁን ድረስ በጣም ብዙ ሊፈቱና ሊታለፉ የማይችሉ የሚመስሉ ችግሮችን አልፋና ፈታ እዚህ ደርሳለች፡፡ እንዴት? ከተባለ ችግሮች በሙሉ መፍትሄ ስላለው ያንን መፍትሄ መመልከትና መተግበር የሚችሉ አዋቂዎች ስለነበሯት ነው፡፡ ሌላ ምንም ሚስጥር የለውም፡፡ አሁንም ይቺ ሀገር በጣም ውስብስብና አስቸጋሪ ችግሮች ገጥመዋታል፡፡ ይህንን መፍታት የሚቻለው እውቀትን በመጠቀም ይሆናል፡፡ ሁላችንም መረዳት ያለብን ችግር ካለ መፍትሔ መኖሩን ነው፡፡ 

ዶ/ር አብይ አህመድ በብርሃን የማይጠፋ ጨለማ እንደሌለ ሁሉ በእውቀት የማይገኝ የችግር መፍትሔ እንደሌለ መናገሩ እውነታው የሚያጠራጥር እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይህንን የተናገረው ስልጣን በያዘ አመት ሳይሞላው ከመምህራን ጋር ባደረገው ስብሰባ ላይ ነው፡፡ መምህራን እውቀትን ከማስተማር ባለፈ ሰዎች እንደዚህ ያለ ስለልቦና እንዲያዳብሩ ማድረግ ያስፈላጋል፡፡  የሰው ልጅ “እችላለው” የሚል አመለካከት ካዳበረ እንደሚችል ሁሉ “ለችግርም ሁሉ መፍትሄ አለው” የሚል አመለካከት ያለው ሁሉ በቀላሉ ችግር ውስጥ ገብቶ አይቸገርም፡፡

በእኛ ሀገር እጅግ ብዙ መፍትሔ የሚሹ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች መፍትሄ ሳይኖራቸው ቀርቶ ሳይሆን አስከአሁን ችግር ሆነው ያሉት በሁለት ምክንያት ነው፡፡ 

አንደኛው ለተፈጠረው ችግር ትክክለኛውን መፍትሄ ባለመስጠት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ችግሩ ከአስቸጋሪነቱ እንዲጠፋ ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ነው፡፡ የትም ቦታ ያሉ ችግሮች በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች መቀረፍ ያልተቻሉ ናቸው፡፡ ይሄ ደግሞ በቀጥታ የሚነግረን በቦታው ላይ ያሉና ጉዳዩ በቀጥታየሚመለከታቸው ሰዎች እውቀት እንደሌላቸው አሊያም ደግሞ ለችግሩ መፍትሄ የመስጠት ፍላጎት እንደሌላቸው ነው፡፡ እውቀት ያለው ሰው የችግርን መፍትሄ መመልከት የሚችል ነው፡፡ 

 በአንድ ሀገር ውስጥ የተማረው የሰው ሀይል እየጨመረ ሲሄድ በተቃራኒው ችግሩ እየቀነሰ መሄድ ይኖርበታል፡፡ ይህንን እንደ አለም ብንመለከተው ብዙ ነገር እናስተውላለን፡፡ ድሮ የነበሩት ችግሮች አሁን የሉም፡፡ ሌላ ዓይነት መፍትሄ የሚፈለጉ ናቸው አሁን ያሉት፡፡ ለምሳሌ ሀገራት በቀላሉ ተገናኝተው እቃ እየተለዋወጡ ነው፡፡ ይህ ማለት በመካከል እንዳይገናኙ አጥር የሆናቸውን አስወግደዋል፡፡ ይሄ መፍትሄ ነው፡፡

አሁን ደግሞ በመቀራረባቸው የተፈጠረ ችግር አለ፡፡ እርሱንም እውቀታቸውን ተጠቅመው እንደሚፈቱት እርግጠኛ ነኝ፡፡

 ወደ ሀገራችን ስንመለስ ደግሞ ፍፁም የተቃረነ ነገር እናስተውላለን፡፡ እድገታችን ቁልቁል እየሆነ ነው፡፡ ስልጣኔያችን ወደ ኋላ እየተመለሰ ነው፡፡ በህብረት መቆም ሲገባን መለያየትን እየመረጥን ነው፡፡ ይሄ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የተማረ ሀይል እጅግ ሊያስወቅስ የሚችል ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ ሀገር ውስጥ የተማረው የሰው ሀይል እየበዛ ሲሄድ ተራርቆ የሚኖረው ህዝብ የበለጠ አንድ እየሆነ ነው የሚሄደው፡፡ መለያየት ችግር ነው፡፡ መቀራረብ ደግሞ የችግሩ መፍትሄ ነው፡፡

በየጊዜው የመማሪያ ተቋማት ቁጥራቸው እየበዛ እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ ችግሮች ግን ሲቀንሱ አይታይም፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ የሚወጣው በየጊዜው ቁጥሩ ከፍ እያለ ነው፡፡ በዛው ልክ ደግሞ በችግር የሚሞተው ሰውም እየጨመረ ነው፡፡ በበሽታ የሚሰቃየው ኢትዮጲያዊ ቁጥሩ ትንሽ የሚባል አይደለም፡፡ የተመጣጠነ ምግብ የሚመገበውኢትዮጲያዊ ብዙ አይደለም፡፡ እነዚህ ችግሮች በእውቀት የሚመረቀው ሰው ሲበዛ መቀነስ ነበረባቸው፡፡ ግን አሁንም ባሉበት አሉ፡፡ ይሄ የተማረውን የሰው ሀይል የሚያስተቹ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በብርሃን የማይሸሽ ጨለማ እንደሌለ ሁሉ በእውቀትም የማይገኝ የችግር መፍትሄ የለምና፡፡

 ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት መፍለቂያዎች ናቸው፡፡ እውቀቶች ደግሞ የችግር ሁሉ መዶሻዎች ናቸው፡፡ ችግር እንዳልነበር የሚሆነው እውቀት ስራውን በአግባቡ መስራት ሲጀምር ነው፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የኢትዮጲያን ችግር በመፍታት እረገድ ሰፊ ድርሻ አላቸው፡፡ እንደውም የመፍትሄ ምንጭ ናቸው፡፡ ከአርባ አምስት በላይ ዩኒቨርሲቲዎች በኢትዮጲያ ውስጥ አሉ፡፡ ሁሉም በአካባቢያቸው ያለውን ችግር ለይተው መፍትሄ ቢሰጡ ትክክለኛ ስራቸውን እንደሰሩ ይቆጠራል፡፡ በአካባቢ ያለውን የንፅህና ችግር ቢቀርፉ፣ በህዝቡ መካከል የሚፈጠርን አለመስማማት በቶሎ ዘላቂ መፍትሄ ቢሰጡ፣ የአካባቢያቸውን ስራ አጥ ወጣቶች አሰልጥነው ወደ ስራ እንዲሰማሩ እድል ቢያመቻቹ፣…..ወዘተ ይሄን ሁሉ ቢያደርጉ ምስጋና ይቸራቸው ነበር፡፡

 የፍትህ መጓደል ሲኖርና ህዝብ ሲቆጣ በመካከል ገብተው የማስታረቅ ስራ ቢሰሩና መፍትሄ መሆን ቢችሉ መልካም ነው፡፡ የህዝብ አገልጋዮች በታማኝነት መስራት ሲሳናቸው የጥናት ውጤት ለበላይ አካል በማድረስ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር መቀነስ መቻል እራሱ አንድ የመፍትሄ አካል መሆን ነው፡፡ሌሎችንም ተግባሮች በማድረግ ለችግር ሁሉ መፍትሄ የመስጠት ልምድ በማዳበር ሀገርን ማዳን እውቀት ስለሆነ ዩኒቨርሲቲዎች ድርሻችሁን ለይታችሁ መስራት አለባችሁ፡፡

 እዚህ ላይ አንድ ነገር መጨመር ፈለኩ፡፡ ይህም ችግር ሲያስቸግረን ችግሩን የምናይበት እይታ ለምንሰጠው ምላሽ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የምንሰጠውን ትክክለኛ መፍትሔ የሚወስነው እይታችን ነው፡፡አግዝፈን ችግሩን ካየነው መፍትሄውን በቀላሉ ማግኘት አንችልም፡፡ ችግሩን አቅልለን ካየነው ደግሞ በቀላሉ መፍትሄውን ማግኘት እንችላለን፡፡ለችግር ሁሉ መፍትሔ እንዳለ ከተስማማን በየአካባቢያችን ላሉት ቀላልና አነስተኛ እስከ ውስብስብ ለሚመስሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እንነሳ፡፡ 



 ባምላኩ አበባው፣ ጅማ ከአባጅፋር መንደር

.......................................................................................................


"Just as there is no darkness that cannot be extinguished by light

There is no solution to a problem that cannot be found in knowledge. 

Prime Minister Dr. Abiy Ahmed

 

      The main reason there is darkness is because there is no light. The bright day that started with light in the morning is bright and surrounded by darkness at night. Why? The sun that gives us light will be because it turns away from us. Because we are not like the Egyptians arguing that we are the only ones who should use the Nile. The others are looking for sunlight, so we gladly accompany her. When we happily accompany her, we do not forget that darkness will come upon us.

Darkness comes as soon as the sun goes down. This means that it is a fact that darkness comes from the absence of light. Darkness is hard. Darkness creates anxiety and brings peace. No one loves darkness. As a result, people used different options to avoid darkness.

    They worked hard to create different inventions. For example: First demonstrate by creating a fire. Next, I created light objects that could easily be moved by hand. Others labored to devise solutions that would reduce the darkness. And they succeeded. They said that the solution to the problem of darkness was to turn on the lights.

    Darkness is a symbol of ignorance, ignorance, illiteracy, trouble. And light is an example of knowledge, education, civilization, solution. To destroy ignorance, it is necessary to ask and read what is known, and to destroy ignorance, it is necessary to learn. Since childhood, human beings take everything into their minds and gain knowledge as much as they can.

    When man learns and knows, new things are added to what is already there. In addition to this, by entering school, starting from the first grade, acquiring new knowledge and jumping to university, he is expected to make a difference to himself and his community.

  When a person is made to pass through all these lines, it is thought that he can answer all the problems that block the way as darkness. It is believed that by shining light, it will provide solutions and brighten the way. Every problem has its own solution. But in order to find the solution, it is necessary to search and see through the lens of knowledge. From college to university, when a human being graduates with a degree or a master's degree, it is expected that he will find solutions to problems. If he comes to study and has the same problems as the uneducated, they will make him drink coffee, saying that his degree is a cock's degree. They make it a gossip highlight. Mothers in our country jump with joy when their child enters university. When he graduated, they used their non-existent abilities to repay.

And their enthusiasm will increase from today to tomorrow. Because they think that because they are educated, they can alleviate many pressing problems. Not only the family but also the society expects a lot from the student who has just graduated. They are right to expect. The difference between the uneducated and the educated person is not only learning and not learning, but also the solution to the problem and not. From a small problem in the family to a complex problem that we face as a nation, they expect a solution from an educated person. Therefore, the learned power is highly trusted.

  Our country, Ethiopia, has gone through so many problems that seem to be impossible to solve and have reached here. why? It is because she had adults who could look at and implement that solution because there is a solution to all problems. There is no other secret. This country is still facing very complex and difficult problems. This can be solved using knowledge. We all need to understand that if there is a problem, there is a solution.

It should be noted that Dr. Abi Ahmed said that there is no darkness that cannot be dispelled by light, and that there is no solution to a problem that cannot be found through knowledge. He said this in a meeting with teachers less than a year after assuming office. Teachers should not only teach knowledge, but also make people develop such a mindset. If a human being develops the attitude of "I can do it", anyone who has the attitude of "every problem has a solution" will not easily get into trouble.

There are many problems that need to be solved in our country. These problems have not yet been resolved, but remain problematic for two reasons.

One is due to not providing the right solution to the problem and the second is due to lack of determination to make the problem disappear from its difficulty. Problems everywhere are intractable due to these two factors. This directly tells us that the people on the spot who are directly affected by the issue do not have the knowledge or they do not have the desire to solve the problem. A person with knowledge is able to see the solution to a problem.

  As the educated manpower in a country increases, the problem should decrease. If we look at this as a world, we will notice many things. The problems of the past are no more. Other solutions are needed. For example, countries are easily connected and exchanging goods. This means that they have removed the fences so that they do not meet in the middle. This is the solution.

And now there is a problem with their proximity. I am sure they will use their knowledge to solve it.

  When we return to our country, we notice the complete opposite. Our growth is going downhill. Our civilization is going backwards. We are choosing to stand apart when we should be standing together. This is something that can be very critical of the educated forces in the country. Because when the number of educated human resources in a country increases, the people who live apart are becoming more united. Separation is a problem. Closeness is the solution to the problem.

Every now and then we notice that the number of learning institutions is increasing. But problems do not appear to be diminishing. The number of people who graduate from university is constantly increasing. At the same time, the number of people dying due to the problem is also increasing. The number of Ethiopians suffering from the disease is not small. Not many Ethiopians eat nutritious food. These problems should have decreased as the number of people graduating with knowledge increased. But they are still there. These are the critics of the educated manpower. Because just as there is no darkness that cannot be overcome by light, there is no solution to a problem that cannot be found through knowledge.

  Universities are generators of knowledge. Knowledge is the hammer of all problems. It is not a problem when knowledge starts doing its job properly. Universities in Ethiopia have a large share in solving Ethiopia's problems. In fact, they are the source of the solution. There are more than forty five universities in Ethiopia. If everyone identifies the problem in their area and solves it, it is considered that they have done their proper work. If they solve the problem of sanitation in the area, if they provide a permanent solution to the disagreements between the people, if they train the unemployed youth of the area and provide them with the opportunity to work, etc., they would be grateful if they did all this.

When there is injustice and when people are angry, it is good if they intervene and work to reconcile and be the solution. When public servants fail to work honestly, being able to reduce the problems that may arise by delivering research results to a higher body is itself a part of the solution. Since it is the knowledge to save the country by doing other tasks, universities should do their part.

  I wanted to add something here. When we face a problem, the way we see it is very important to our response. It is our perspective that determines the right solution. If we look at the problem lightly, we can find the solution easily.

Bamlaku Abebaw, jimma from the abajifar village



key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post