መክሊት
“ከፍጥረታት መካከል በብዙ ስጦታ የተንበሸበሸ የሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡” ይላሉ ሊቃውንት፡፡ ማድረግ እንዳይሳነው ተደርጎ የተሰራ ክቡር ፍጡር ነው፡፡ ብንመረምር የማንደርስበት፣ ብንፈላሰፍ እውነታው የሚረቅብን ብንጽፍ ቀለምና ወረቀት የሚያንስብን፤ ብንናገር ሰዓት የሚገድበን ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ተፈጥሮውና ስጦታው ነው፡፡ ሌላው የበለጠ የሚያስደንቀን ጉዳይ ደግሞ ሁላችንም አንድ ዓይነት ያልሆነ ስጦታ የታደልን መሆናችን ነው፡፡ እንደየመልካችንም ስጦታችንም ልዩ ልዩ ነው፡፡ ለእኔ የተሰጠውን ስጦታ ለተወሰነ እንጅ ለሁሉም አልተሰጠውም፡፡ እኔ ፀሀፊ ነኝ፡፡ እንደ እኔ የሚፅፉ ውስን የሆኑ እንጅ ሁሉም የሰው ልጅ አይደለም፡፡ ልፃፍ ብሎ ቢነሳ ስጦታው አይደለምና ያበላሸዋል፡፡ ውበት ሰጥቶ የሚማርክና ሲያነቡት ልብን የሚያስደስት ለአዕምሮ ምግብ መሆን የሚችል ሀሳብ ማመንጨት ከቶ አይችልምና፡፡ ስጦታውን ለይቶ ወደ ተሰጠበት ካልተመለሰ ሲደክም ይኖራል እንጅ ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡
የሰው ልጅ ውጤት ሊያመጣ የሚችለው ስጦታውን ለይቶ በዚያ መንገድ ሲሰማራ ብቻ ነው፡፡ አንድ ነጋዴ በንግድ ውስጥ የመስራት ፍላጎት ስላለው ብቻ ነግዶ ማትረፍ አይችልም፡፡ ምን ዓልባትም የእርሱ ስጦታ ጀግና ገበሬ ወይም ጎበዝ ወታደር ይሆናል፡፡ አንድ ፖለቲከኛ በፖለቲካው ዓለም የብጥብጥና የንትርክ መንስዔ ከሆነ ስጦታው እርሱ አይደለም ማለት ነው፡፡ ምን አልባትም በህክምናው ወይም በምህንድስናው መስክ ቢሰማራ ስኬታማ ሊሆን ይችላል፡፡ ስጦታው ይሄ ሊሆን ስለሚችል ማለት ነው፡፡ በአስተዳደር ቦታ ላይ ተቀምጠው ለህዝብ እንግልት መነሻ የሚሆኑ ሰዎች ማስተዳደር የእነእርሱ ስጦታ ስላልሆነ ነው፡፡ መምራት ወይም ማስተዳደር በትምህርት የሚመጣ ብቻ አይደለም፡፡ ጥበብ እና ክህሎት ያለው በመሆኑ በእኛ ውስጥ መኖሩንና አለመኖሩን መመርመር አለብን፡፡ ምክንያም አልቻሉም፡፡ ያልቻሉት ደግሞ ማስተዳደር ስጦታቸው ስላልሆነ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የሆነው ያለቦታው የተገጠመ ክዳን የማፍሰስ እድል እንዳለው ሁሉ ያለስጦታቸው የሚደክሙ ሰዎችም ወደኋላ የመመለስ እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
በእረኛዬ ድራማ ውስጥ ስጦታቸውን አውቀው ከሚደክሙት ሰዎች መካከል እረኛዋ እናና አንዷ ናት፡፡ እርሷ የመማርም ትልቅ ደረጃ የመድረስም እድል ነበራት፡፡ ነገር ግን የእርሷ ስጦታ እንስሳትን መንከባከብ ነው፡፡ ምግባቸውን እንዲያገኙ ማድረግ፣ ሲታመሙ በቶሎ ህክምና መስጠት፣ ባጠቃላይ ለእንስሳት ፍቅር መስጠት ለእናና የተሰጠ ሙያ ነው፡፡ እናም እናና ስጦታዋን ለይታ እየደከመች ነው፡፡ ውጤታማም እንደሆነች ተመልክተናል፡፡ ይህንንም አባባ ሳህሉ መስክረውላታል፡፡ እንዲህ ብለዋል “ሰው ታዲያ አንዱን ሞያ ከአንዱ አስበልጦ የሚበልጠውንም ወይ ሳያውቅበት ወይ ሳይደሰትበት ለሰውም ለራሱም ሳይጠቅም ዝም ብሎ አንከርፍፎ ቢይዘው ምን ያደርግለታል? ዋናው የተሰጠውን ማወቅ ነው፡፡”
እኛም እንደ እናና የተሰጠንን ስጦታ ለይተን መስራት አለብን፡፡ ያለተስጧችን የምንደክም ከሆነ በሚጠበቅብን ልክ ውጤት ልናመጣ አንችልም፡፡ እንቀየር እንለወጥ ስንል ሁላችንም የተሰጠንን ለይተን በዚያ ሙያ ላይ እንሰማራ ማለታችን ነው፡፡ ግንበኛው “ይሄ ሞያ የተሰጠው ለእኔ ነው” ብሎ ካልደከመ፤ ሀኪሙ “እኔ የተፈጠርኩት ህዝቤን ለማከም ነው” ብሎ ካላመነ፤ ቀጥቃጩም “እኔ የታደልኩት ለዚህ ነው” ብሎ ካልሰራ ለውጥ አይመጣም፡፡ ለውጥ ማምጣት የተሳነንም ከዚህ በተቃራኒው ሆነን ስለተገኘን ነው፡፡
እርግጥ ባህላችን አንዱን ሙያ ከፍ ሌላውን ዝቅ እንደሚያደርግ እናውቃለን፡፡ አሁን አሁን የተወሰነ መሻሻል ቢታይበትም፡፡ ይህንን ሰብሮ የራስን የውስጥ ፍላጎትና ልዩ ተስጦን ይዞ መጓዝ ፅናትን ሊፈልግ ይችላል፡፡ አንድ ነገር ማወቅ ያለብን ግን ውጤት የምናመጣውም ለስኬትም የምንበቃው የራሳችንን ስጦታ ለይተን ስንሰራ ብቻ ነው፡፡ እኛም ደግሞ ከመተቸትና የማይሆን አስተያየትና ሀሳብ ከመስጠት መቆጠብ ይገባናል፡፡ ይልቁንም እያበረታን የበለጠ ተስጧቸውን ይዘው እንዲተጉ ማድረግ ትልቅ የሰውነት ተግባር ነው፡፡
ተስጦ ሰው መርጦ የሚሰጠን፤ ሁኑ ብሎ የሚገፋን መሆን የለበትም፡፡ ውስጣችን ነው ለይቶ እንድንሆን የሚያደርገን፡፡ ከሰው የሚጠበቀው እንቅስቃሴያችንን በማስታወል ወደዚያው እንድንጠጋ መግፋት ነው፡፡ በተለይ ወላጆች ብዙ ነገር ይጠበቀባቸዋል፡፡ ልጆቻቸውን ተከታትለው ተስጧቸውንም ለይተው እንዲያድጉ ማድረግ ትልቅ የወላጆች ሃላፊነት ነው፡፡ ምንም ይሁኑ ምንም በመረጡት ላይ መጠንከር አለባቸው፡፡ “አንተ መሆን ያብህ ዶክተር ነው አንቺ መሆን ያለብሽ የህግ አዋቂ ነው” ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኛ የህግ አዋቂ እንዲሆን የተመኘንለት ልጅ ተስጦው መሃንዲስነት ሊሆን ይችላልና፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ የሰውን ተስጦ መለየት ከዚያም በዚያ መንገድ እንዲሄድ መገዝ አስፈላጊ ነው፡፡
ባምላኩ አበባው፣ ጅማ
.............................................................................................................................
Talent
"Among creatures, only man is spoiled by many gifts." say the experts. He is a noble creature made to fail. What we cannot reach if we analyze, if we philosophize, the truth will come to us; if we write, what ink and paper will draw us; If we speak, the only thing that limits us is human nature and its gifts. Another thing that amazes us is that we are all gifted differently. Our gifts are different according to our appearance. The gift that was given to me was not given to some but to all. I am a secretary. Not everyone is human except those who write like me. If he tries to write, he will ruin it because it is not his gift. Because he can never generate an idea that can be a food for the mind that gives beauty and charms and delights the heart when you read it. If the gift is not returned to the place where it was given, it will be tired and will not produce results.
Humans can only achieve results when they recognize their gifts and use them in that way. A trader cannot profit from trading just because he is interested in doing business. Perhaps his gift will be a brave farmer or a brave soldier. If a politician is the cause of violence and controversy in the political world, then the gift is not his. He may be successful in the field of medicine or engineering. The gift is because this can happen. People who sit in administrative positions and are the source of public abuse is because it is not their gift to manage. Leadership does not just come from education. It is wisdom and skill that we must examine whether it is present in us or not. Because they couldn't. And they failed because it was not their gift to manage. And this is just as a misplaced lid is likely to leak, so those who labor without their gifts are more likely to backslide.
Inanna, the shepherdess, is one of the people who know their gifts and work hard in the drama. She had the opportunity to learn and reach great heights. But her gift is caring for animals. Making them get their food, giving them quick treatment when they are sick, giving love to animals in general is a profession given to Inana. And Inana. is struggling to identify her gifts. We have seen that it is effective. Sahlu witnessed this to her. He said, "If a person chooses one profession over the other and does not know or enjoy it, what will it do for him if he just ignores it without benefiting the person or himself? The key is to know what is given.”
As mothers, we must take care of the gifts we have been given. If we work hard without motivation, we will not be able to produce the results we expect. When we say let's change, we mean that we all identify what we have been given and engage in that profession. If the builder doesn't get tired of saying, "This job was given to me"; If the doctor does not believe that "I was created to heal my people"; And if the person doesn't say, "This is why I am blessed," there will be no change. We failed to bring about change because we were found to be the opposite.
Of course, we know that our culture elevates one profession and lowers another. Although there has been some progress now. Breaking through this and traveling with one's inner passions and unique gifts can take perseverance. One thing we need to know is that we will achieve results and be successful only when we identify our own gifts. We should also refrain from criticizing and giving inappropriate opinions and ideas. Rather, it is a great body function to encourage them to work harder.
The one who chooses and gives to us. It shouldn't be pushing us to be. It's what makes us unique. What is expected of man is to remember our movement and push us closer to it. A lot is expected of parents in particular. It is the responsibility of parents to monitor their children and make them grow up. Whatever they are, they should be careful about what they choose. It is not appropriate to say, "You should be a doctor, you should be a lawyer." Because the child we wish to become a legal expert may become an engineer. Therefore, it is important to first identify a person's desire and then guide him to go that way.
Bamlaku abebaw , jimma
bnmnhnv
ReplyDelete