“ከከፍታችሁ እንዳትወርዱ፡፡”
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ
ከሁሉም ፍጥረታት በተሻለ ከፍታ ላይ ሆኖ የተፈጠረ የሰው ልጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ የተፈጠረው በመጨረሻው ቀን እንደሆነ ቅዱሳን መፃህፍት ነግረውናል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት “የሰው ልጅ የሁሉ ገዥ እንዲሆንና እንዲጠብቅ ታስቦ ነው፡፡” ይላሉ፡፡ የሰው ልጅ ከፍታው በዚህ ልክ ነው፡፡ ምድርን እንደፈለገ ማድረግ ይችላል፡፡ ሰማይን መቆጣጠር ይችላል፡፡ ተፈጥሮን ማዘዝ ይችላል፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን አምላኩን መስሎ የተፈጠረ መሆኑ ደግሞ ምን ያህል ከፍ ያለ ፍጥረት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የሰው ልጅ ከፍታው በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ የማሰብና የመመራመር፣ የማወቅ፣ የመፍጠር ከፍተኛ ብቃት እንዲኖረው ተደርጎ የተፈጠረ ክቡር ፍጥረት ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጅ ከፍ ያለ ፍጡር ነው፡፡
መሬት አይናገርም አያስብም፡፡ ሰማይ አያወራም፡፡ አይንቀሳቀስም፡፡ ዕፅዋት አያስቡም አይፈጥሩም፡፡ ድንጋይ፣ አፈር፣ ሌሎችም እንዲሁ ምንም ሊደረግባቸው ይችላል እንጀ ምንም ማድረግ በራሳቸው አይችሉም፡፡
እንስሳትን ብንመለከትም እንዲሁ ከሰው ልጅ በብዙ መንገድ እንደሚያንሱ መረዳት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም በሰው ልጅ ልክ ማሰብ አይችሉም፡፡ በሰው ልጅ ልክ ዓለምን መረዳት አይችሉም፡፡ በሰው ልጅ ልክ ማድረግም መሆንም አይችሉም፡፡ አዎ የሰው ልጅ ከሁሉም ፍጥረት በተሻለ ከፍ ብሎ የተፈጠረ ፍጡር ነው፡፡
አንድ ነገር ከፍታው የሚታወቀው በሚሰጠውና በሚያደርገው ጥቅም ልክ ነው፡፡ ከፍታ ብቻውን ዝቅታ ሊሆን ይችላል፡፡ ከፍ ብሎ መፈጠር ጥቅም ከሌለው ዝቅ ብሎ መኖር ይሻላል፡፡ ከፍታ ሁሉንም የሚቆጣጠር ነው፡፡ ከፍታ ሁሉንም የሚመራ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከፍ ብሎ የተፈጠረ የከፍታ ባለቤት ነው ማለት ዝቅታውን ሁሉ ይቆጣጠራል ማለታችን ነው፡፡ ዝቅታው ደግሞ በዓለም ያለ ሁሉም ነገር ነው፡፡ ዓለም እንደተፈጠረች አይደለችም፡፡ ብዙ ነገር ተጨምሮባታል፡፡ ምንም ያልነበረባት አሁን ግን ብዙ ነገር አላት፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው የሰው ልጅ ከፍታውን መጠቀም ስለቻለ ነው፡፡
የሰው ልጅ ከፍታው በማሰቡና በመፍጠሩ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ በመኖሩም ጭምር የሚለካ ነው፡፡ በአብሮነትና በፍቅር የሚኖር ማህበረሰብ ከፍ ያለ ማህበረሰብ ነው፡፡ የሰው ልጅ መኖር ያለበት እንደ ሰው ሆኖ ነው፡፡ እንደ ሰው መኖር ማለት ደግሞ በህብረት በፍቅር ያለ ምንም ተቃርኖና ያለ ምንም መቃቃር መኖር ማለት ነው፡፡ እንደ ሰው መኖር ማለት ከትላንት እየተማሩ ነገን በተሻለ መንገድ ለመምራት መዘጋጀት ነው፡፡ የሰው ልጅ የሚሞት ፍጡር ነው፡፡ ማንም እንደሚሞት አውቆ የማይሞት ስራ ሰርቶ ለማለፍ መሞከር የከፍታ ልክ ነው፡፡
ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ በአንድ ወቅት የተናገሩት ነገር ነበር፡፡ ይህን የተናገሩት በሚሊኒየም አዳራሽ የመልካም ወጣት የመዝጊያ ዝግጅት ላይ ተገኝተው በነበረበት ወቅት ነው፡፡ እርሳቸው ለወጣቶች ካስተላለፉት መልዕክት መካከል “ከከፍታችሁ እንዳትወርዱ፡፡” ብለው አደራ የሰጡበት ንግግር አይዘነጋም፡፡ ይህ ንግግር ድንቅ ንግግር ነው፡፡ ብዙ ሊያስብል የሚችል ሀሳብ የያዘ ነው፡፡ ከከፍታ እንዳትወርዱ ብለው የተናገሩበት ዋናው ምክንያት ከከፍታ መውረድ መዋረድ ስለሆነና ተገቢ ባለመሆኑ ነው፡፡ እርሳቸው በወቅቱ በመልካም ወጣት ስም ለተሰበሰቡት ቢሆንም ቃሉን የተናገሩት በመልካም ጎዳና ላይ ላሉት ሁሉ ይጠቅማል፡፡
ምን ማለት ነው ከከፍታ መውረድ ማለት? ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም፡፡ ከከፍታ ላይ የሚቆም ሰው የትኛውንም ዝቅታ መመልከት ይችላል፡፡ በዝቅታ ውስጥ ያለ ግን የሚያየው ዝቅታውን ብቻ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከፍታው የሚለካው በአስተሳሰቡ ነው፡፡ መልካም አስቦ መልካም የሚያደርግ ሰው ከፍታ ላይ እንዳለ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ መልካም ማሰብ እየቻሉ ማሰብና ማድረግ ያልቻሉ ግን በዝቅታ ውስጥ እንዳሉ መታወቅ አለበት፡፡ የምንም ነገር መነሻ ሀሳብ ነው፡፡ ሀሳቡ መልካም ከሆነ ድርጊቱም መልካም ይሆናል፡፡ ሀሳብ መልካም ካልሆነ ደግሞ ድርጊቱም መልካም አይሆንም፡ የአንድ ሰው ከፍታውና ዝቅታው መነሻው ሀሳብ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ “ከከፍታችሁ እንዳትወርዱ” ብለው ያሳሰቡበት ዋናው ምክንያት ሰዎች ከመልካም አስተሳሰባቸው እንዳይሸሹ ለማሳሰብ ነው፡፡ የሰው ልጅ መልካም ሲያስብና መልካም ሲያደርግ ከከፍታ ጫፍ መድረስ ይችላል፡፡ በተቃራኒ መስመር ላይ ከሆነ ግን ዝቅ እንዳለ ይቀራል፡፡ በክርስትና አስተህምሮ ውስጥ ለዚህ ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ ታሪኮች አሉ፡፡ ለምሳሌ አቤልንና አይሁዳውያንን መመልከት እንችላለን፡፡ አቤል ቃዔልን ለማንገላታትና ለመግደል ሲያስብ አቤል በዝቅታ ውስጥ ስለነበር ነው፡፡ አይሁዳውያን ክርስቶስን ሲሰቅሉትና ሲወግሩት እነእርሱ በዝቅታ ውስጥ ስለነበሩ ነው፡፡ በዝቅታ ውስጥ ያለ ማንም ቢሆን የዘቀጠና የማይጠቅም ተግባር የሚፈፅም ነው፡፡ ለዚህ ነው አቤልም ይሁን ክርስቶስን የሰቀሉ አይሁዳውያን አሁን ድረስ በክፉ የምናነሳቸው፡፡ በከፍታ ውስጥ ሆኖ የሚኖር ሰው የሚሰራው ሁሉ ዘመን ተሻጋሪ ስለሆነ ትውልድ ሲያመሰግነው ይኖራል፡፡ ከከፍታችሁ አትውረዱ ማለት በዘመን ተወቃሽ እንዳትሆኑ መልካም አስባችሁ መልካም ስሩ ማለት፡፡ ከከፍታችሁ አትውረዱ ማለት ሰው ናችሁና እንደ ሰው ኑሩ ማለት ነው፡፡
አዳምና ሄዋን በገነት ሲኖሩ በከፍታ ነበር፡፡ ከፍታቸውን ያጡት የአምላካቸውን ትዕዛዝ ባለማክበራቸው ነው፡፡ የአዳምና የሄዋን ታሪክ የሚነግረን የፈጣሪን ትዕዛዝ የማያከብር ማንም ከከፍታው ወርዶ በዝቅታ ውስጥ እንደሚኖር ነው፡፡ አንተም አንችም ሁላችንም በከፍታ እንድንኖር የተፈጠርን ነን፡፡ በዝቅታ እንድንኖር አልተፈቀደልንም፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኑም ሙስሊሙም በቅዱስ መፅሐፉ ይመራ፡፡ ስለዚህ ከከፍታችሁ አትውረዱ ማለት በእምነታችሁ የፀናችሁ ሁኑ እንጅ አስመሳይ አትሁን ማለት ነው፡፡ አስመሳይ ሰው በዝቅታ ያሚኖር ነውና፡፡
ሀገር የምትበለፅገው በከፍታ ውስጥ ባሉ ዜጎቿ ነው፡፡ በመግደል የማያምኑ፣ በማቀፍና በመተባበር የሚሰሩ እነእርሱ የከፍታ ሰዎች ናቸው፡፡ ትላንትን ትምህርት ቤት አድርገው ነገን ለመስራት የሚደክሙ እነእርሱ በእውነት በከፍታ ላይ ናቸው፡፡
በህብረት ተደምረው በፍቅር ተሳስረው በይቅርታ የሚኖሩ እነእርሱ ከከፍታ ጫፍ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ አምላካቸውን ፈርተው በእውነተኛ ስሜት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን የሚያገለግሉ እነእርሱ ከፍ ያሉ ናቸው፡፡ ክቡር ጠ/ሚኒስተር ከከፍታችሁ እንዳትወርዱ ብለው ያሳሰቡት እንደዚህ ላሉት ከፍ ላሉት ሰዎች ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ብልፅግና እንዲመጣ የምንሻ ከሆነ ሁላችን ተመልሰን ወደ ከፍታው መውጣት አለብን፡፡ ይህን ያልኩበት ዋናው ምክንያት ቀደምት ኢትዮጵያውያን የከፍታው ጫፍ ላይ ስለነበሩ ነው፡፡ ይህን የሚያረጋግጥልን ደግሞ የመጀመሪያው የሰው ዘር መጀመሪያ መሆናችን ሲሆን ሁለተኛው ከዓለም ሀገራት በተሻለ በስልጣኔ ጎዳና ላይ ስለነበርን ነው፡፡ በአንድ ሀገር ላይ ስልጣኔ አለ ማለት አብዛኛው ሰው በከፍታ ላይ ነው ማለት ነው፡፡ ታሪካችን የሚነግረን አምላኩን የሚፈራ ትውልድ እንደነበር፣ የሀገሩን ልጅ ወንድሙን ብቻ ሳይሆን ስደተኛውን የማያውቀውንም ጭምር የሚያቅፍ ባሕል እንደነበር፣ የሚመራመርና የሚፈጥር አዕምሮ ባለቤት የሆኑ ጀግና ትውልድ እንደነበር ነው፡፡
ታዲያ ከዚህ በላይ ከፍታ የታል? ከዚህ አንፃር አሁን ላይ ያለን ኢትዮጲያውያን ትንሽም ቢሆን ዝቅ ያልን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም መገዳደል በዛ፡፡ ፍቅር እራቀን፡፡ እርስ በእርሳችን ከመተቃቀፍ ይልቅ መገፈታተር አበዛን፡፡ የሚሰሩ እጆች አንሰው የጥፋት እጆች ግን በዙ፡፡ የሚፈጥሩ የሚመራመሩ አዕምሮዎች መነመኑ፡፡ ሀገሩን የሚወድ ጠፋ፡፡ የሌላ ሀገር የሚናፍቀው ግን በረከተ፡፡ በባህሉ የሚኮራ ጠፍቶ በተውሶ ባህል የሚደምቅና የሚኮራ በዛ፡፡ ይህ ሁሉ ከከፍታችን ምን ያህል እንደወረድን የሚያሳይ ነው፡፡
የሰው ልጅ በዝቅታ ውስጥ በመኖሩ ማንንም ተጠያቂ ሊያደርግ አይገባም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ ትክክለኛውን የመለየትና ልክ ያለሆነውንም የሚጥል ትልቅ አዕምሮ ስላላው ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ከዝቅታ ውስጥ ያለው ወደ ከፍታው መውጣት ይኖርበታል፡፡ በከፍታ ውስጥ ያለው ደግሞ ከከፍታው እንዳይወርድ መጠንቀቅ ይኖርበታል፡፡
ሁላችንም በአንድ እንቁም፡፡ በፍቅር ዓይን እንተያይ፡፡ ትላንትን በይቅርታ ዘግተን ነገን እንደ አዲስ እንገንባ፡፡ ይህን ስናደርግ ወደ ከፍታችን እንመለሳለን፡፡
ባ ባምላኩ አበባው (ጅማ፣ ከአባ ጅፋር መንደር)
.........................................................................................................................................
"Do not come down from your high."
Prime Minister Dr. Abiy Ahmed
Human beings are created to be the highest of all creatures. The holy books tell us that mankind was created on the last day. This is because "man was designed to be the ruler and preserver of all." They say. This is the height of humanity. He can do whatever he wants with the earth. He can control the sky. He can command nature. From all of this, it is possible to understand how high a creation he is that he was created in the image of God. Human height is not limited to this. It is a noble creation created to have a high ability to think and research, to know, to create. Therefore, the human being is a higher being.
Land does not speak or think. Heaven does not speak. It doesn't move. Plants do not think or create. Stone, soil, etc. can be done to them, but they cannot do anything by themselves.
Even if we look at animals, we can understand that they are inferior to humans in many ways. Because they cannot think like human beings. Human beings cannot understand the world. You can't do or be like human beings. Yes, the human being is a creature created higher than all other creatures.
A thing's height is known by the value it gives and what it does. Highs alone can be lows. It is better to live low than to be made high. Altitude controls everything. Elevation rules all. To say that the human being is the master of the higher created means that he controls all the lower. And the lowest is everything in the world. The world is not as it was. A lot has been added to her. She had nothing but now she has a lot. This is possible because humans have been able to use the height.
Human height is not only defined by thinking and creating, but also measured by living in the right way. A society that lives in harmony and love is a higher society. Human beings must live as human beings. To live as a human being means to live together in love without any conflict or strife. To live like a human is to learn from yesterday and prepare to lead tomorrow in a better way. Man is a mortal being. Knowing that one is going to die, doing an immortal job and trying to get through it is the height.
It was something that Prime Minister Dr. Abiy Ahmed once said. He said this when he was present at the closing event of Good Youth at the Millennium Hall. Among the messages he conveyed to the youth was, "Don't come down from your hight" The speech they entrusted will not be forgotten. This speech is a wonderful speech. It contains many thought-provoking ideas. The main reason why they said not to descend from a height is because it is inappropriate to descend from a height. Although he spoke the word to those who gathered in the name of a good young man at that time, it will benefit all those who are on the good path.
What does it mean to descend from a height? He who asks will not disappear. A person standing on a high place can look down on anything. But he who is in the low sees only the low. A man's height is measured by his thoughts. It is important to understand that a person who thinks good and does good is at the top. It should be known that those who are able to think well but are unable to think and act are in a state of misery. The starting point of anything is an idea. If the thought is good, the action will be good. If the thought is not good, then the action will not be good.
The main reason why the prime minister said "don't come down from your high" is to remind people not to run away from their good thoughts. When a human being thinks good and does good, he can reach the top. If it is on the opposite line, it will remain low. There are stories in Christian teaching that can be a demonstration of this. For example, we can look at Abel and the Jews. When Abel thought to torture and kill Cael, it was because Abel was in the dark. When the Jews crucified and stoned Christ, it was because they were in shame. Anyone who is in a state of indolence is one who commits evil and useless actions. This is why we still hate the Jews who crucified Abel or Christ. A person who lives in height will be praised by generations because everything he does is timeless. Don't come down from your high position. It means think well and do good so that you will not be blamed in time. Don't come down from your height, it means that you are human and live like a human.
When Adam and Eve lived in Paradise, it was high. They lost their dignity because they disobeyed the commands of their God. The story of Adam and Eve tells us that anyone who disobeys the command of the Creator will come down from the heights and live in the low. You and I are all meant to live high. We are not allowed to live quietly. Therefore, the Christian and the Muslim should be guided by the Holy Book. Therefore, do not come down from your height, it means to be firm in your faith, but do not be a hypocrite. For a hypocrite is one who lives quietly.
A nation thrives on its citizens who excel. They are people of height who do not believe in killing, embrace and cooperate. Those who spend yesterday in school and work hard for tomorrow are truly at the top.
They are the ones who live together in love and live in forgiveness. Those who fear their God and serve their country and people with true feelings are exalted. Honorable Prime Minister has warned such high people not to come down.
If we want prosperity to come in Ethiopia, we all have to go back to the top. The main reason I say this is because the early Ethiopians were at the top of the mountain. This is confirmed by the fact that we are the first human race and the second is because we were on the path of civilization better than the countries of the world. Civilization in a country means that most of the people are on top. Our history tells us that it was a God-fearing generation, a culture that embraces not only the countryman's brother, but also the stranger, and that it was a heroic generation with researching and creative minds.
So where is the height above this? From this point of view, I think we Ethiopians are a little low. Because that's killing. Love away from us. Instead of hugging each other, we loosened up more. The hands of work are lifted up, but the hands of destruction are many. Creative and researching minds wither. He who loves his country is lost. But he who yearns for another country is blessed. There is one who is proud of his culture, who shines and is proud of his lost culture. All this shows how far we have fallen from our heights.
Human beings should not blame anyone for their existence in poverty. This is because human beings have a great mind to distinguish between what is right and what is wrong. From this point of view, the one who is in the low should rise to the high. He who is in a height should be careful not to come down from the height.
Let us all stand together. Let us see each other with loving eyes. Let's close yesterday with forgiveness and build a new tomorrow. When we do this, we return to our heights.
Thank u.
Bamlaku Abebaw, From abajifar village jimma