ክፍል 2
አጥር
በአንድ ሀገር ውስጥ ትልቁ ሀብት የማህበረሰብ አንድነት ነው፡፡ አንድነቱን ጠብቆ የሚኖር አካባቢ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ ህብረቱን የተነጠቀ አካባቢ የጠላት መግቢያ መውጫ በር፣ መደበቂያ ዋሻ ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሰላም የሌለበት፣ መሰረተ ልማት የማይስፋፋበት፣ አዳዲስ ነገር የማይታይበት፣ የትምህርትና ጤና ተደራሽነትም እንዲሁ ፈተና ውስጥ የሚገቡበት እድል ሰፊ ይሆናል፡፡ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች የማይገነቡበት ነው የሚሆነው፡፡
አካባቢውን ለማልማት ፍላጎት ያለው ሰው መጀመሪያ ማድረግ ያለበት የአካባቢውን ነዋሪ ህብረት ማጠናከር ነው፡፡ አንድነትን ማጠናከር ደግሞ የቅን ሰዎች ተግባር ነው፡፡ ልዩነትን ለማስፋት ጥረት ማድረግ ደግሞ የደካሞች ስራ ነው፡፡
ቸል ብለን እና ንቀን የተውናቸው ግን ውለው አድረው ትልቅ ዋጋ እንድንከፍል የሚያደርጉ ጉዳዮች አሉ፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ጎልተው ያልወጡ ችግሮች ቀስ በቀስ እየተዛመቱ መተሳሰብን ሊያጠፉ፣ ፍቅርን ሊያቀዘቅዙ፣ ህብረትን ሊበትኑ ይችላሉና በፍጥነት መታከም እና መቆም አለባቸው። የማህበረሰብን አንድነት ለመጠበቅም ሆነ ለማስቀጠል ሶስት ጉዳዮች ላይ ቸል ማለjት የለብንም፡፡
የመጀመሪያው በግለሰቦች መካከል ያለውን ግንኙነት አዎንታዊ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ሰዎች ከሰዎች ጋር ተቀራርበው ተሳስበውና ተዋደው እንዲኖሩ ማድረግ የማህበረሰቡን አንድነት የምንጠብቅበት መልካም ዘዴ ነው፡፡ ባል ከሚስቱ ጋር፣ ወንድም ከወንድሙ ጋር፣ አባት ከልጁ ጋር፣ ወንድም ከእህቱ ጋር፣ በሁለት በጓደኛሞች መካከል ያለው ግንኙነት መተዋወቅ ያለበት፣ መተሳሰብ የሰፈነበት፣ ፍቅር የዳበረበት፣ ትብብር የጎላበት፣ አንድነት የጠነከረበት፣….ወዘተ ከሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለው አንድነት የተጠበቀ ነው የሚሆነው፡፡
እርግጥ ሁላችንም የተለያዬ አመለካት፣ አተያይ፣ ዝንባሌ፣ እውቀት፣ ፍላጎት፣…ወዘተ እንዳለን መዘንጋት የለብንም፡፡ ይሄ የተለያዬ ነገራችን የተለያዬ አቅጣጫ እንድንይዝ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ይሄ ወደ አለመስማማት ሊወስደን፤ አለመስማማታችን ደግሞ እንዳንተባበር ሊያደርገን ይችላል፡፡ ይሄንን አወንታዊ አስተሳሰብ ካለ ማስተካከል ቀላል ነው፡፡ የተለያዬን መሆናችን እድል እንደሆነ ሁሉም ሰው ማወቅ አለበት፡፡
ከዚህ አለፍ ብሎ አለመስማማቱ ከቀጠለ ደግሞ በቅርብ ያሉ የተሻሉ ሰዎች እንዲፈቱት እድል መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ይህንን ስናደርግ ግን በጊዜ መሆን አለበት፡፡ ሚስትም ልጅም ሳያውቁ፤ ጎረቤት ቤተዘመድ ሳይሰማ የተከሰተው አለመስማማት ወደ መስማማት መቀየር ችግሩ እንዳይሰፋ ለማድረግ መልካም መንገድ ነው፡፡
ሁለተኛው መንገድ ደግሞ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን መልካም እሴቶች መጠበቅ ነው፡፡ በየትኛውም አካባቢ ብንሄድ ያለልዩነት ደስታ ሲገኝ በጋራ የሚደምቁበት ሀዘን ሲከሰት በጋራ ሆነው የሚፅናኑበት ባህል አላችው፡፡ ችግር ሲመጣ በጋራ የሚጋፈጡበት ልማት ሲኖር በጋራ የሚሳተፉበት ድንቅ እሴት አላቸው፡፡ ይሄ ለአንድነታቸው ሲባል መጠበቅ አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ይህንን መሰል ባህል በብዛት ጎልተው ከሚታዩባቸው ሀገራት መካከል ናት፡፡
አንድነትን፣ ህብረትን፣ መተጋገዝን፣ መረዳዳትን፣….ወዘተ አጉልተው ከሚያሳዩን ተግባራት መካከል እድር፣ አቁብ፣ እዝን፣ እሩብ፣ ፅዋ ማህበር፣ ክርስትና፣ …..ወዘተ የሚባሉ አሉ፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ የቡና አጠጣጥ ስርዓታችን፣ ሰርግ ላይ ያለን ተሳትፎ፣ ሀዘን ሲከሰት የምናሳየው በጎ ትብብር፣ በልማት ወደ ኋላ የቀረን ወዳጅ የምናበረታታበት መንገድ፣ የተቸገረን የምናግዝበት ዘዴ፣ የወለደችን ሴት የምንጠይቅበት መንገድ…..ወዘተ ለአንድነታችን መሰረት ነው፡፡
የተጣላን ሰው የምናስታርቅበት፣ ያጠፋን ሰው የምንቀጣበት ባህል መጠበቅ ያለበት እሴት ነው፡፡ ይህንን የበለጠ የሚያበረታታ ነገር መስራት አለብን፡፡ ለዚህ ሲባል መሰረተ ልማት መገንባት አለበት፡፡ መሰረት ልማት ስንል መንገድ፣ መብራት፣ ስልክ፣ …ወዘተ ማለታችን ነው፡፡ ይችንን ላማከናወን አቅም የሌለው ሰው ከመንግስት ብድር የሚያገኝበት ስርዓት መዘርጋት አለበት፡፡ ለዚህ ሲባል የመንግስትም ሆነ የግል ሚዲያዎች ወጥ የሆነ ሽፋን መስጠት አለባቸው፡፡ ለዚህ ተብሎ የተሰየመ እና ይህንን የሚያበረታታ ሚኒስተር መስሪያ ቤት መቋቋም አለበት፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ አንድነት መሰረት ነውና፡፡
የእነዚህ ጉዳዮች መላላት የኢትዮጵያ አንድነት መላላት ነው፡፡ የሁሉም ነገር ምንጭ እንዳለው ሁሉ የአንድነታችን መቀዛቀዝም ምንጩ እሴቶቻችን ላይ እንደሆነ መታወቅ ይኖርታል፡፡ ቡና አብሮ ሲጠጣ የነበረ ሰው ባልታወቀ ምክንያት ቢያቆም ይሄ ለሀገር አንድነት መሸርሸር እንደምክንያት መቆጠር አለበት፡፡ እንዚህ ቸል ሊባሉ የማይገቡ ችግሮች ናቸው፡፡
ሶስተኛው ጉዳይ ደግሞ የአንድ ወገን ብቻ የሆኑትን ጎዳዮች የጋራ ማድረግ ነው፡፡ ቋንቋችን የተለያዬ ሊሆን ይችላል፡፡ በግል ያዳበርነው እሴት ሊኖረን ይችላል፡፡ የአንድ ወገን ብቻ ሆነው የቆዩ ባህሎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን በተቻለ መጠን የሁሉም እንዲሆኑ ማድረግ አንድነታችን የበለጠ እንዲዳብር ይረዳል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያን ለመሰሉ ሀገራት ይህን መሰል ተግባር በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
የአማራውን አማራዎች ብቻ ሳይሆኑ ኦሮሞ የሆኑ ሁሉ የ”እኔ” ብለው መቀበል አለባቸው፡፡ የትግሬዎችን ባህል፣ እሴት፣ ቋንቋ፣….ወዘተ ሌሎች እህት ወንድሞች የ”እኛ” ነው ብለው መለማመድ፣ መተግበር፣ መናገር፣ መጠበቅና ማስቀጠል አለባቸው፡፡ በጋራ ሀገር የአንድ ወገን ብቻ የሚሆን ጉዳይ መኖር የለበትም፡፡ ይህ እንዲሆን ግን አጥር ትልቁን ሚና መጫወት ይችላል፡፡ የቃልም ሆነ የእንጨት አጥር ሰውን ከሰው፣ ማህበረሰብን ከማህበረሰብ ከዚያም ሀገርን ከሀገር መለያየት ይችላል፡፡
የቃል አጥር በቀላሉ የሚዛመትና መድሐኒት የማይገኝለት የአንድነት ነቀርሳ ነው፡፡ የመተባበር በሽታ ነው፡፡ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በባህል፣….ወዘተ ያለው ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ግን አንድነቱን ጠብቆ በሚኖር ማህበረሰብ ውስጥ ስለምንተርከው ታሪክ፣ ስለምንናገረው ንግግርና ስለምናስበው ሃሳብ በጣም መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ አጥር ሰርተን ማህበረሰቡን ልናቃቅረው እንችላለንና፡፡
ትላንትን አስታውሰን ስንነጋገር ጠቃሚ ለሆነ ዓላማ መሆን አለበት፡፡ አንድነታችንን የሚሸረሽር፣ ህብረታችንን የሚበትን፣ ፍቅራችንን የሚቀዘቅዝ ከሆነ መልካም አይደለምና አጉልተን መነጋገር ሊኖርብን አይገባም፡፡ ትላንትን ስናስብና ስንነጋገር ዛሬ እና ነገን ዘንግተን መሆን የለበትም፡፡ ስለትናንት የምንናገረው ቃል ለብዙ ዘመናት አብሮ በኖረው ህዝብ መካከል አጥር ሊሆን አይገባም፡፡
ለኢትዮጵያ ትልቅ ፈተና የሆነው የቃል አጥር ነው፡፡ ጎረቤትን ከጎረቤቱ፣ አንድን ብሄር ከሌላኛው ብሔር፣ አንድን አካባቢ ከሌላው አካባቢ፣ ክርስቲያን ከሙስሊሙ፣….ወዘተ ልብ ለልብ እንዳይገናኝ የከለከለው በቃል የታጠረ አጥር ስላለ ነው፡፡ ይህንን አጥር አልፈው የተገናኙም የሚገናኙም እንዳሉም እንደሚኖሩም ይታወቃል፡፡ ግን አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በዚህ አጥር ምክንያት ተለያይቶ እየኖረ ነው፡፡
እንቀጥላለን፡፡
ባምላኩ አበባባ፣ ከአባ ጅፋር መንደር፣ ጅማ
.............................................................................................................................................................
Section 2
Fence
The greatest asset in a country is community unity. It is known that an environment that maintains its unity will benefit in many ways. An area that has been deprived of the alliance becomes an entrance and exit door for the enemy, a hiding place. As a result, there is no peace, infrastructure is not expanded, new things are not seen, access to education and health will also be challenged. It happens when other important matters do not develop.
The first thing anyone who wants to develop the area should do is to strengthen the local resident union. Strengthening unity is the task of honest people. Efforts to widen diversity are the work of the weak.
There are issues that we ignore and ignore but eventually make us pay a big price. Unexplained problems in the community can slowly spread and destroy empathy, slow down love, and destroy unity, so they must be treated and stopped quickly. In order to maintain and maintain the unity of society, we must not neglect three issues.
The first is to make interpersonal relationships positive. Making people live close to each other and love each other is a good way to maintain the unity of the community. A husband with his wife, a brother with his brother, a father with his son, a brother with his sister, if the relationship between two friends should be familiar, where there is mutual respect, where love is developed, where cooperation is strong, unity is strong, etc., then the unity in the society will be protected.
Of course, we must not forget that we all have different views, perspectives, attitudes, knowledge, interests, etc. This difference can lead us to take different directions. This leads us to disagreement; Disagreement can also keep us from cooperating. It is easy to fix this positive thinking. Everyone should know that it is a privilege that we are apart.
If the disagreement continues beyond this, it is appropriate to give a chance to better people nearby to solve it. But when we do this, it must be in time. Unbeknownst to the wife and child. Disagreement that occurred without listening to the neighbors is a good way to prevent the problem from spreading.
The second way is to protect the good values in the society. No matter where we go, there is a culture where happiness is found without distinction, and when sadness happens, they are comforted together. When there is a problem, they face together and there is development, they have a great value to participate in together. This must be maintained for their unity. Ethiopia is one of the countries where this kind of culture is prominent.
Among the activities that highlight unity, union, support, help, etc., there are Edr, Akub, Ezun, Erub, Tswa association, Christianity, etc. Beyond this, our coffee drinking system, our participation in weddings, the good cooperation we show when grief occurs, the way we encourage our friends who are behind in development, the way we help those in need, the way we ask for the woman we gave birth to... etc. are the basis of our unity.
A culture in which we reconcile a quarrelsome person and punish a person who has destroyed us is a value that must be preserved. We need to do something to encourage this more. For this, infrastructure needs to be built. When we say basic development, we mean roads, electricity, telephone, etc. In order to do this, a system should be established where people who cannot afford to get loans from the government. For this, both government and private media should provide consistent coverage. A ministry designated for this and promoting this should be established. Because it is the foundation of Ethiopian unity.
The failure of these issues is the failure of Ethiopian unity. Just as everything has its source, the decline of our unity must be recognized as having its source in our values. If a person who was drinking coffee with him stops for unknown reasons, this should be considered as a reason for the erosion of national unity. These are problems that should not be ignored.
The third issue is to make the one-sided streets common. Our language may be different. We may have values that we have personally developed. Cultures can exist that are only one sided. Making these as inclusive as possible helps our unity grow. This kind of activity is very important especially for countries like Ethiopia.
Not only the Amhara, but all Oromos must be accepted as belonging to "me". The culture, values, language, etc. of the Tigries must be practiced, spoken, protected and maintained by other siblings as "ours". There should not be a one-sided issue in a common country. For this to happen, fencing can play a major role. Verbal or wooden fences can separate people from people, communities from communities and countries from countries.
Verbal barriers are an infectious and incurable cancer of unity. It's a collaborative disease. In spite of the differences in language, religion, race, culture, etc., we must be very careful about the stories we tell, the speech we speak and the thoughts we think in a society that maintains unity. We can build a fence and destroy the community.
Remembering yesterday when we talked, it must be for a worthwhile purpose. If it destroys our unity, destroys our union, and cools our love, it is not good, so we should not talk about it. When we think and talk about yesterday, we should not forget about today and tomorrow. The words we talk about yesterday should not be a barrier between people who have lived together for many centuries.
The biggest challenge for Ethiopia is the verbal fence. Neighbor from neighbor, one nation from another nation, one area from another area, Christian from Muslim, etc., because there is a fence that prevents heart to heart. It is known that there are those who have crossed this fence and are still meeting. But most Ethiopians are living separated because of this fence.
........ here we go.
Bamlaku Ababaw, from Aba Jifar Village, Jimma