የጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ የአደባባይ ንግግሮች//Prime Minister Dr. Abiy Ahmed public speeches

 


ከላይኛው የቀጠለ …..

እነዚህ ያየናቸው ጥቅሶች በሆነ ወቅት የሀገር ወይም የድርጅት መሪ የነበሩ ሰዎች የተናገሯቸው ነው፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲ በወረቀት ታትመው የሚሸጡና በፖስተር ታትመውም በየመንገዱ የሚለጠፉት፡፡ አንድ እውነት አለ፡፡ እርሱም ቃላት ብቻቸውን የሰውን አመለካከት መቀየር አቅም አላቸው፡፡ ዐረፍተ ነገር ሲመሰርቱ ደግሞ የበለጠ አቅም ይኖራቸዋል፡፡ 

 ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ የሚናገሯቸው ንግግሮች ብቻቸውን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ በንግግራቸው መካከል ጣል የሚያደርጓቸው ጥቅሶች ጊዜ ወስዶ ለሚመረምራቸው ህይወትን የሚቀይሩ ናቸው፡፡ ማርቲን ሉተር ከተናገረው የሚበልጥ እንጅ የማያንስ፣ ባራክ ኦባማ ከተናገረው የሚስተካከል፣ አብርሃም ሊንከን ከጠቀሰው ጥቅስ ጋር እኩል ሊነገር የሚችል ጥቅስ ተናግረዋል፡፡ እርሳቸው የሌላ ሀገር መሪ ቢሆኑ ኖሮ እስከ አሁን ድረስ የተናገሩት ንግግር፣ የጠቀሱት ጥቅስ፣ የተረቱት ተረት፣  የተቀኙት ቅኔ እየተለቀመ በስልጠና ቦታ እና በየስብሰባው ማስጀመሪያ በየተቋሙ ደግሞ መነጋገሪያ ቋንቋ ያደርጉት ነበር፡፡ 

   ምክንያቱም የእርሳቸው ንግግር ዘመንን መዋጀት የሚችል፣ ፍቅርን መዝራት የሚችል ነው፡፡ የብርሃን ወጋገን የሚለቅ፣ በተስፋ የሚሞላ፣ ለውስጥ ደስታን የሚሰጥ፣ ወደ ነገ በክብር የሚያሻግር፣ በጎነትን የሚዘራ፣ ሰላምን የሚሰብክ፣ ጥላቻን የሚያርቅ፣ አንድነትን የሚሰብክ፣ መተባበርን የሚያፀና፣ የጠላትን ቅስም የሚሰብር ለብልፅግና መሰረት የሚሆን ነው፡፡ ይህንን ንግግራቸውን በማስተዋል የሚሰማ የሚያረጋግጠው እውነት ነው፡፡

 እርሳቸው ከተናገሩት ብዙ ንግግር መካከል አንዱ የስልጣንን ምንነት በደንብ ላልተገነዘቡ ሰዎች የተናገሩት ነው፡፡ ለምሳሌ፤ “ሀገራችንን ከወደድን ስልጣን ሀላፊነት እንጅ ገዥነት አይሁን፤ ሹመት ማገልገያ እንጅ መገልገያ አይሁን፡፡” ብለው በአንድ ወቅት አስረድተዋቸዋል፡፡  ይሄ ንግግራቸው በየትኛውም የስልጣን እርከን ላይ የተቀመጠ ሰው ከእርሳቸው ፎቶ ጋር ሰቅሎ ሲወጣ ሲገባ ሊመለከተው የሚገባ ድንቅ ጥቅስ ነው፡፡ ይህ የእርሳቸው ንግግር ብቻውን አመለካከትን የሚቀይር ነው፡፡ 

  “እኛ ለጉርሻ ስንጣላ ሞሰብ እንዳይሰረቅብን እንጠንቀቅ፡፡”  ብለው ሁሉንም ሰው ቆም ብሎ እንዲያስብ አድርገው እንደነበር አሁንም አንዘነጋም፡፡ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳቸው ለትናንሽ ጉዳይ ተጣልተው ትልቁን ሀብታቸውን እንዳይነጠቁ ያሳሰቡበት ንግግራቸው ነው፡፡ ይሄ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ አልፎም ደግሞ ለዓለም መሪዎች ጭምር የሚሰራ ጥቅስ ነው፡፡ የሃያላን ሀገራት መሪዎች ከፊትለፊታቸው ይህንን ንግግር ሰቅለው ጥዋትና ማታ ቢመለከቱት አመለካከታቸውን የሚቀይር እንደሚሆን ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም የሚያባላን ሁሉ ትንሽ የጉርሻ ጉዳይ እንጅ የሞሰቡ ጉዳይ አይደለም፡፡ 

   ልብ ብለው ካደመጡና ከደጋገሙት የእርሳቸው ንግግር የቀየራቸው ሰዎች ብዙ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም፡፡ ምክንያቱም ፈልገው ባይለወጡም ሳይፈልጉ በቃላቸው ጉልበት የሚቀየሩ ብዙ ናቸው፡፡ መልካም ንግግር ብቻውን የሰውን አዕምሮ እንደሚለውጥ ማመን አለብን፡፡ አሁንም መልካም ተናጋሪን ያብዛልን ማለት ይኖርብናል፡፡

   


Continued from above…..


These verses we have seen were spoken by people who were leaders of countries or organizations at some point. These are the ones that are printed and sold on paper and printed on posters and posted on the streets. There is one truth. And words alone have the power to change a person's attitude. They also have more power when forming sentences. Prime Minister Dr. Abiy Ahmed's speeches are self-evident. The quotes he drops in between his talks are life-changing for those who take the time to study them. He said a quote no less than what Martin Luther said, no less than what Barack Obama said, no less relatable than what Abraham Lincoln said. If he were the leader of another country, the speeches he made, the quotes he quoted, the stories he told, the poetry he wrote would be selected and used in the training place and at the beginning of every meeting in every institution. Because his speech is capable of redeeming the era and sowing love. It emits light, fills with hope, gives inner happiness, crosses to tomorrow with glory, sows goodness, preaches peace, dispels hatred, preaches unity, strengthens cooperation, breaks the enemy's bow, and is the foundation for prosperity. This is the truth that can be confirmed by those who understand their speech. One of the many speeches he made was to people who did not fully understand the nature of power. for example; "If we love our country, power should not be a responsibility but a rulership; Appointment should not be a utility but a utility.” They once explained to them. This is a wonderful quote that anyone sitting at any level of power should look at when they go out with their picture hanging. This speech of his alone is an attitude changer. "Let's be careful that Mosseb doesn't steal us while we fight for bonuses." We still can't forget that they made everyone stop and think. It is his speech in which he reminded Ethiopians not to fight each other over small issues and take away their biggest wealth. This is a quote that applies not only to Ethiopians, but also to African and world leaders. It is reasonable to think that if the leaders of powerful countries hang this speech in front of them and watch it morning and night, it will change their attitude. Because all that bothers us is not a matter of money but a small bonus. I have no doubt that there will be many people who will be changed by his speech if they listen carefully and repeat it. Because there are many who are changed by the power of their words, even if they don't want to change. We must believe that good speech alone can change people's minds. We still need to increase the number of good speakers.

key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post