የጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ የአደባባይ ንግግሮች / Prime Minister Dr. Abiy Ahmed Public speaking

 

   


በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ወደ አመራርነት የስልጣን እርከን የሚገፋ አጋጣሚ ይከሰታል፡፡ የግል ህይወትን ከመምራት ጀምሮ የአንድ ተቋም መሪ እስከመሆን ልንታደል እንችላለን፡፡ አንድ ሰው የግል ህይወቱን በስኬት ከመራ፣ ተቋምንም በብቃት መምራት ይችላል፡፡ ቤተሰቡን በቅንነት ካገለገለ ሀገሩንም በቅንነት ማገልገል ይችላል፡፡

  እርግጥ ነው፣ በድንገት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ወይም ፕሬዚደንት መሆንን ልንፈልግ እንችላለን፡፡ ወይም በሚኒስትርነት ለመምራት ፈላጎት ሊያድርብን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ከባድ ነገር አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ግን እራስን በስኬት ጎዳና ላይ መምራት መቻል ነው፡፡ አንድ ሰው በህይወቱ ውስጥ የሚያጋጥመውን ፈተና ተቋቁሞ በሁሉም መስክ ማለትም በግል ህይወቱም በትዳሩም በስራውም ለስኬት ከበቃ እርሱ የሀገር መሪ ነው፡፡  አንድ ሰው ህይወቱን በትክክል መምራት ሳይችል ሀገር ለመምራት ቢያስብ ግን ተሳስቷል፡፡

  በታሪክ ውስጥ፣ የሀገር ወይም የድርጅት መሪ ሆነው ያለፉ ሰዎች በብዛት ታሪካቸው አስተማሪ ሆኖ ተመልክተናል፡፡ የእነእርሱ ስም ሲጠራ አብሮ ተያይዞ የሚወሳ ንግግር አላቸው፡፡ ሀገራቸውን ወይም ድርጅታቸውን ለስኬት ያበቁበት ሚስጥር ለሌላ መሪ አርዓያም ሆኖት መልካም ትምህርት ይሆነዋል፡፡ ለዚህ የታደሉ ብዙ አሉ፡፡   የእነዚህ የአመራር ሰዎች ንግግራቸው፣ ጥቅሶቻቸው፣ ተረታቸው፣ ግጥማቸው፣ ብዙ ሰዎች ህይወታቸውን እና ሌሎች በዙሪያቸው ያሉትን ቀይረዋል።

  እንደ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ካሉ ኃያላን የለውጥ መሪዎች አንደበት የወጣው ንግግር ዛሬም ድረስ እየተነገረ ለውጥ እየተፈጠረበት ነው፡፡ ከአሜሪካን የእነ አብርሃም ሊንከን ከአፍሪካ ደግሞ የእነ ኔልሰን ማንዴላ ንግግር አሁን ድረስ ታሪክ እየሰራ ይገኛል፡፡ ግለሰብን ብቻ ሳይሆን  ሀገርን እየሰራ ነው፡፡  መሪዎቹ የተናገሩትን ንግግር በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሰቅለው ዘወትር እንደቅዱሳን ምስል የሚሳለሙ ሰዎች አሉ፡፡ “ለእኔ ስኬት ይሄ የእገሌ ንግግር ነው፡፡” የሚሉ ሰዎችም ጭምር አሉ፡፡

ለምሳሌ የተወሰኑትን ብቻ ብንመለከት እንኳን፤

·         "መጪው ጊዜ በህልማቸው ብሩህነት ለሚያምኑት ነው፡፡" ኤሌኖር ሩዝቬልት

·         "ሁሉም ህልሞቻችን እውን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነሱን የምንከታተልበት ድፍረትም ብቃትም ካለን፡፡"  ዋልት ዲስ

·         "ብዙዎቹ የህይወት ውድቀቶች ከተስፋ መቁረጥ የሚመነጩ ናቸው፡፡” ቶማስ ኤዲሰን

·         "አንተ ህዝቡን አትከተል፤ ህዝቡ ግን ይከተልህ።" ማርጋሬት ታቼ

·          "አንድን ነገር በምትሰሩበት ጊዜ ዓለም ሁሉ እንደሚመለከተው አስቡት።" - ቶማስ ጄፈርሰን

·          "በዓለም ላይ ምልክት ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ቀላል ቢሆን ኖሮ ሁሉም ያደርጉት ነበር። ግን አልሆነም፡፡ ትዕግስት ይጠይቃል፣ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል፡፡ እናም በመንገዱ ላይ ብዙ መውደቅ መነሳት  ይኖረዋል። - ባራክ ኦባማ

·         “ደግ ሁን፤ በህይወትህ የምታገኛቸው ሰዎች ሁሉ ከባድ ጦርነቶች ናቸው” - ፕላቶ

·         "ሁሉም ሰዎች መከራን ሊቋቋሙት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የሰውን ባህሪ ለመፈተሽ ከፈለጋችሁ ስልጣን ወይም ሃላፊነት ስጡት." - አብርሃም ሊንከን

·         "መሪዎችን አትጠብቅ፤ ብቻህን አድርግ፡፡ ከሰው ለሰው። - እናት ቴሬዛ

·         "እውነተኛ መሪ መግባባትን የሚፈልግ ሳይሆን የጋራ ስምምነትን የሚቀርጽ ነው" ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር

·         “መሪ እንደ እረኛ ነው። ከመንጋው ኋላ ይሆናል፣ በጣም ልባሞች ወደ ፊት እንዲወጡ ይፈቅድላቸዋል፣ ከዚያም ሌሎቹ በሙሉ ከኋላ እየተመሩ መሆናቸውን ሳያውቅ ይከተላሉ። - ኔልሰን ማንዴል

·         …. ወዘተ፡፡

English version

    In every person's life there is an opportunity that pushes them to a higher level of leadership. From leading a private life to being the leader of an institution, we can be blessed. If a person leads his personal life successfully, he can also lead an institution effectively. If he serves his family with sincerity, he can also serve his country with sincerity.

   Of course, we may suddenly want to be the Prime Minister or President of Ethiopia. Or we may want to lead as a minister. But this is not a serious matter. But the main thing is to be able to lead yourself on the path of success. If a person can face the challenges in his life and achieve success in all fields, whether in his personal life, in his marriage or in his career, then he is a leader of the country. If a person thinks of leading a country without being able to lead his life properly, he is mistaken.

   Throughout history, we have seen many people who have become leaders of nations or organizations have their stories instructive. When their name is called, they have an accompanying speech. The secret of success of their country or company will be a good example for other leaders. There are many who are blessed with this. The speeches, quotes, stories, poems of these leaders have changed many people's lives and others around them.

   Speeches from powerful change leaders such as Martin Luther King Jr. are still being spoken and changed today. Abraham Lincoln's speech from America and Nelson Mandela's speech from Africa are still making history. He is working not only for the individual but also for the country. There are people who hang the speeches of the leaders in their homes and worship them as saints. "This is my personal speech for my success." There are also people who say

For example, even if we only look at some;

• "The future belongs to those who believe in the brilliance of their dreams." Eleanor Roosevelt

• "All our dreams can come true if we have the courage and ability to pursue them." Walt Dis

• "Many of life's failures stem from despair." Thomas Edison

• "Don't follow the people, but let the people follow you." Margaret Thatcher

• "Imagine that the whole world is watching when you do something." - Thomas Jefferson

• "Making your mark on the world is hard. If it were easy, everyone would be doing it. But it's not. It takes patience, it takes determination. And there will be many falls and rises along the way." - Barack Obama

• “Be kind; All the people you meet in life are hard battles” - Plato

• "All men can handle adversity. But if you want to test a man's character, give him power or responsibility." - Abraham Lincoln

• "Don't wait for leaders. Do it alone. From person to person. - Mother Teresa

• "A true leader is not one who seeks compromise but one who creates consensus" Martin Luther King Jr.

• “A leader is like a shepherd. He would be at the back of the herd, allowing the bravest to come forward, and then all the others would follow, unaware that they were being led from behind. - Nelson Mandel

 .................

                       we will continue


key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post