የጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ የአደባባይ ንግግሮች / Prime Minister Dr. Abiy Ahmed Public speaking// “አትጠራጠሩ እናሸንፋለን፡፡”

                            ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ

  

 




                       ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ በሄዱበት ሁሉ ንግግር ሲያደርጉ በዙ ጊዜ የሚደጋግሙት አንድ ቃል አለ፡፡ ይህ ቃል ከአንደበታቸው ሲወጣ እንደማንኛውም ዓይነት ቃል እንዳልሆነ የሚረዳው አስተዋይ የሆነ ሰው ነው፡፡ በማስተዋል ሆኖ ልብ ላለው ግን ይህ ቃል ምን ያህል ጉልበተኛ እንደሆነ ይረዳል፡፡ ይህም ቃል “አትጠራጠሩ እናሸንፋለን፡፡” የሚል ነው፡፡ የዚህን ቃል ታላቅነት ለመረዳት ሁለቱንም ቃላት በተናጠል ብንመለከተው የተሻለ ነው፡፡

“አትጠራጠሩ” የሚለውን ለብቻው እንመልከት፡፡ ብዙ ትርጉምና አንደምታ ቢኖረውም አትጠራጠሩ የሚለው ቃል እምነተ ጎደሎ አትሁኑ  የሚል ጠቅለል ያለ ትርጉም ሊሰጠን ይችላል፡፡ እምነተ ጎደሎ ማለት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ያላመነ እንደማለት ነው፡፡ ይህንንም በአማርኛ መዝገበ ቃላት ላይ መመልከት እንችላለን፡፡

ሰዎች በእምነት ውስጥ ተዓምር የሆነውን ሁሉ ማድረግ ይችላሉ፡፡ እምነት ከምናስበው በላይ ታላቅ ሀይል አለው፡፡ የሁሉ ፈጣሪ የሆነውን አምላክ ሰዎች በእምነት መነፅር መመልከት ይችላሉ፡፡ ችለዋልም፡፡ ያመነ ሁሉ ይችላል፡፡ እምነት የማይታየውን ለማየት፣ የማይዳሰሰውን ለመዳሰስ፣ የማይታለፍ የሚመስለውን ለማለፍ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው ባለመጠራጠር ሲሆን ብቻ ነው፡፡

እምነተ ጎደሎ የሆነ ማንም እንኳን ተዓምር ሊሰራ ቀርቶ፤ በሚበላው ምግብ መጥገብ አይችልም፡፡ በማንኛውም ነገር እርካታ ለማግኘት እምነት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

  የእምነት ትልቅነት በቅዱሳን መፃህፍት በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ በክርስትና ቅዱስ መፃህፍትን ያለውን ብናይ እንዲህ እናገኛለን፡፡ ይህም በማቲዎስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቁጥር 20 ጀምረን መመልከት እንችላለን፡፡ እየሱስ ክርስቶስ በባህሩ ላይ ሲረማመድ ደቀመዛሙርቱ ተመለከቱት፡፡ እነእርሱ ምትሀት መስሏቸው እጅግ በጣም ፈርተው ነበር፡፡ ከዚያም “አይዟችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ጌታ ሆይ አንተስ ከሆንክ በውሃው ላይ ወዳንተ እንድንመጣ እዘዘኝ አለው፡፡ እርሱም ና አለው፡፡ ጴጥሮስም ከታንኳዩቱ ወርዶ ወደ እየሱስ ሊደርስ በውሃው ላይ ሄደ፡፡ ነገር ግን የንፋሱን ሀይል አይቶ ፈራ፡፡ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ “ጌታ ሆይ አድነኝ” ብሎ ጮኸ፡፡  ጌታም “አንተ እምነት የጎደለህ ስለምን ተጠራጠርክ” አለው፡፡ የጴጥሮስ በባህሩ ላይ እንደፈለገ እንዳይራመድ እና ወደሚፈልገው ቦታ አለመድረስ ትልቁ እንቅፋቱ መጠራጠሩ ነበር፡፡ ጎደሎ እምነት ስላለው የሚፈልገውን ሳይሆን ቀረ፡፡ የእምነት ትልቅነት ይህን ያህል እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡
  “እናሸንፋለን” የሚለው ቃልም በራሱ ሀያል  የሆነ ቃል ነው፡፡ የዚህን ቃል ሀያልነት እስከምን ድረስ እንደሆነ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ ቢያብራራው በወደድኩ ነበር፡፡ ምክንያቱም “ይቻላል” የሚለውን ቃል ተጠቅሞ ችሎ ስላሳየን፡፡ ቢሆንም ግን “አሸንፋለው” የሚለው ቃል ሁልጊዜ የሚጠቀም ሰው የአዕምሮውን እምቅ አቅም መጠቀም ይችላል፡፡ እችላለሁ፣ አደርጋለሁ፣ አሸንፋለሁ፣…..ወዘተ የሚሉ ቃላት ለስኬታማነታችን በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡የውስጣችን ብርታት ማሳያዎች ናቸው፡፡

አሸንፋለው ብሎ የተነሳ በምንም ሂሳብ አይሸነፍም፡፡ ቃሉ ጉልበት ያለው ስለሆነ በእኛ ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም እንዲወጣ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ እሸነፋለው ብሎ ቀድሞ ያሰበ ግን ምንም ጉልበተኛና ጥበበኛ ቢሆንም መሸነፉ አይቀርም፡፡

በተቃራኒው እሸነፋለው የሚለው ቃል በራሱ በሰው አዕምሮ ውስጥ አለመቻልን ስለሚሰብክ ሰውዬው ያለው ጉልበትና ጥበብ ወጥተው ስራ መስራት አይችሉም፡፡ ሰዎች ስኬታማ እንዲሆኑና እንዳይሆኑ የእነዚህ ቃላት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ስኬታማ ያለሆኑ ሰዎች እሸነፋለው የሚለውን ስለሚያስቡ ሲሆን ስኬታማ የሆኑት ደግሞ አሸንፋለው የሚለውን አብዝተው ስለሚያስቡ ነው፡፡ እንደሚያሸንፉ ያምናሉ፡፡ ሀሳባቸውንም በተግባር ለማሳየት ይጥራሉ፡፡ ይሳካላቸዋል፡፡

 ታዲያ የኢትዮጲያ ጠ/ሚ/ዶ/ር አብይ አህመድ እነዚህን ሁለት የተለያዩ ጉልበተኛ ቃላት በአንድ ላይ ደምረው ዘወትር መናገራቸው ሚስጢሩ ምን ይሆን? የመናገር ሱስ ስላለባቸው ይመስላችኋል? ሁለቱም ጉልበት ያላቸው ቃላት ናቸው፡፡ ለየብቻ ቢነገሩም ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ ጠ/ሚንስትሩ ሁለቱንም በአንድ መናገራቸው የሚሰጠን ትርጉም ምንድን ነው?  አትጠራጠሩ እናሸንፋለን፡፡ በደንብ እንድታስቡት እፈልጋለው፡፡

   ልብ ልንል የሚገባው ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጲያ ውስጥ ያለ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ናቸው፡፡ ይህንን ቃል ሲናገሩ ምን አልባት በፖለቲካው መድረክ ሰፊ የሆነ ድጋፉ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ነው ይህን ያሉት ብሎ መገመት ተገቢ አይመስለኝም፡፡ አዎ እውነት ነው እርሳቸው ብልፅግና የሚባል የፖለቲካ ድርጅት መሪ ናቸው፡፡ እርሳቸው ይህንን ድርጅት ይዘው  ህዝባቸውን ወደ ብልፅግና ማማ ለማውጣት የሚደክሙ ናቸው፡፡ በኢትዮጲያችን ውስጥ ደግሞ ብልፅግና ሊረጋገጥ የሚችላው ብልፅግና የሚባል ፓርቲ ስተለቋቋመ ሳይሆን ሁሉም ሰው የመስራትና የመፍጠር እምቅ አቅሙን እንዲጠቀም በማስቻል ነው፡፡ እናም አትጠራጠሩ እናሸንፋለን ብለው ሲናገሩ ዋና ማጠቃለያ ሀሳባቸው በኢትዮጲያ አልፎም  በአፍሪካ ውስጥ ድህነትን እናሸንፋለን ብልፅግናን እናመጣለን የሚል ይሆናል፡፡ ይህንን ደግሞ ለማድረግ እንችላለን፡፡

አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ነው፡፡ አንድ ጉልበተኛ ቃል ከሌላ ጉልበተኛ ቃል ጋር በአንድ ሲጠሩ ሌላ የተሻለ ጉልበተኛ ቃል ይፈጠራል፡፡ ይህ የተፈጠረው ጉልበተኛ ቃል ለተጠቀመበት የበለጠ እቅምና ጉልበት ይሆናል፡፡

እርሳቸው ይህን ያደረጉበት ምክንያት በሁሉም ነገር ላይ ትልቅ የአሸናፊነትን ስለልቦና እንዲኖረንና የበለጠ ስኬታማ እንድንሆን አብዝተው ከመጓጓታቸው የተነሳ ነው፡፡ ይህንን ቃል ፖለቲካዊ ትርጉም ብቻ ባንሰጠው እመርጣለው፡፡ ለእያንዳንዳችን ህይወት መሰረት ሊሆን የሚችል ጉልበተኛ ቃል ነው፡፡ ይህ ቃል ለኢትዮጲያና ለኢትዮጲያውያን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

 የምንም ነገር መጀመሪያ ቃል ነው፡፡ የዓለም መፈጠር መጀመሪያው ቃል ነው፡፡ የዓለም መጥፊያም መጀመሪያው ቃል ነው፡፡ ይህንን ቅዱሳን መፃህፍት ነግረውናል፡፡ በቃል ደረጃ የነበረው ነው ወደ ተግባር የሚቀየረው፡፡ የመዳንም የመሞትም፣ የመደህየትም የመበልፀግም፣ የማትረፍም የመክሰርም መነሻውም መጀመሪያውም ቃል ነው፡፡

  ይቀጥላል፡፡

   ባምላኩ አበባው (ጅማ፣ ከአባ ጅፋር መንደር) 

 .



                                          "Don't doubt, we will win."

                                                                              Prime Minister Dr. Abiy Ahmed


 


     There is one word that Prime Minister Dr. Abiy Ahmed often repeats whenever he makes a speech wherever he goes. It is a wise person who understands that this word is not like any other word when it comes out of their mouth. But those with a discerning heart will understand how aggressive this word is. That word is "Do not doubt, we will win." is that To understand the greatness of this word, it is better to look at both words separately.

Let's look at "do not doubt" separately. Although it has many meanings and connotations, the word "do not doubt" can give us a general meaning of "don't be unfaithful". Unbelief means not believing at all. We can see this in Amharic dictionary.

People can do miraculous things in faith. Faith is more powerful than we think. People can look at God, the creator of all, through the lens of faith. And they did. Whoever believes is able. Faith is needed to see the unseen, to touch the untouchable, to overcome the seemingly insurmountable. This can only happen if there is no doubt.

Even a person who lacks faith can perform a miracle. He cannot be satisfied with the food he eats. Faith is very important to be satisfied with anything.

   The greatness of faith is widely mentioned in the holy books. If we look at what the Christian scriptures say, we will find this. We can see this starting from Matthew chapter 14 verse 20. The disciples saw Jesus Christ walking on the sea. They were very afraid, thinking it was magic. Then he said to them, "Take courage, it is I, do not be afraid." Saint Peter said to him, Lord, if it is you, command me to come to you on the water. And he said come. Peter got out of the boat and walked on the water to reach Jesus. But he saw the power of the wind and was afraid. When he was about to drown, he cried out, "Lord, save me." And the Lord said, "Why did you doubt, you who lack faith?" Peter's biggest obstacle to walking on the sea and getting to where he wanted was his doubt. Because he lacked faith, he did not get what he wanted. We need to understand that this is the greatness of faith.

   The word "we shall overcome" is a powerful word in itself. I would have liked if athlete Haile G/Salase explained the extent of the power of this word. Because he used the word "possible" to show us. However, a person who always uses the word "overcome" can use the potential of his mind. Words like I can, I will, I will win, etc. are very important for our success. They are the indicators of our inner strength.

He won't be defeated by any account. Because the word is energetic, it plays a major role in unleashing the potential within us. He who thinks that he will win, but no matter how energetic and wise he is, he is bound to lose.

On the contrary, the word "I will overcome" preaches impotence in the human mind, so the energy and wisdom of the person cannot go out and do the work. The role of these words is high for people to be successful or not. Successful people are because they think they will win, and successful people are because they think they will win too much. They believe they will win. They try to show their ideas in practice. They will succeed.

  So what is the secret of Ethiopia's Prime Minister Dr. Abiy Ahmed always saying these two different bully words together? Do you think they are addicted to talking? Both are energetic words. Even when spoken separately, they make sense. What is the meaning of the Prime Minister saying both together? Do not doubt, we will win. I want you to think about it.

    It should be noted that Dr. Abiy Ahmed is the leader of a political organization in Ethiopia. I don't think it is fair to assume that when they say this word, they say it only with the intention of getting a wide support in the political arena. Yes, it is true that he is the leader of a political organization called Baltseghana. He is the one who takes this organization and works hard to bring his people to prosperity. Prosperity can be ensured in our Ethiopia not by establishing a party called Prosperity, but by enabling everyone to use their potential to work and create. And don't doubt when they say that we will win, their main conclusion will be that we will overcome poverty and bring prosperity in Ethiopia and even in Africa. We can do this too.

One plus one is two. When one bully word is combined with another bully word, another better bully word is formed. This creates more power and energy for the bully to use the word.

The reason they did this was because they wanted us to have a winning mindset in everything and be more successful. I prefer not to give this word only a political meaning. It is a powerful word that can be the foundation of each of our lives. This word is very important for Ethiopia and Ethiopians.

  It is the first word of anything. The creation of the world is the first word. The end of the world is the first word. The holy books have told us this. It is what was in words that turns into action. It is the beginning and the beginning of salvation and death, prosperity and wealth, profit and bankruptcy.

                   

                                         to be continued.

    Bamlaku Abebaw (Jimma, from Aba Jifar village)

key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post