ነርሶችና የጤና መረጃ ሥርዓት .// Nurses and health information system

                                                                ነርሶችና የጤና መረጃ ሥርዓት

በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለው የህክምና ስርዓት የመረጃ ፍሰቱ እና እንቅስቃሴው ለህክምና ስርዓቱ መሻሻል ጉልህ ሚና አለው፡፡ ዛሬ ላይ የዘመነ የህክምና አሰጣጥ የመጣው በየደረጃው በየህክምና ተቋማት በተሰበሰበው መረጃ ነው፡፡ እናም ዛሬ ላይ ያለው የመረጃ አያያዛችንም ሆነ አሰባሰባችን ነገ ለምንሰጠው ወይም ለምንደርስበት የህክምና ስርዓት ወሳኝ ነው፡፡
የጤና መረጃ ሥርዓቶች (health information systems (HIS) ስንል የግለሰቦችን ጤና ወይም በጤናው ዘርፍ ውስጥ የሚሰሩ ድርጅቶችን አጠቃላይ የመረጃ እንቅስቃሴ የሚይዝ፣ የሚያስተዳድር ወይም የሚያስተላልፍ ማንኛውንም ሥርዓት ያመለክታል። ይህ ትርጉም በጣም ሰፊና ጥልቅ ነው፡፡ የህክምና አሰጣጡ ሁኔታ፣ የበሽታው እና የበሽተኛው የክትትል ሥርዓት፣ የላብራቶሪ መረጃ፣ የሆስፒታል ታካሚ አስተዳደር ሥርዓቶችን (PAS) እና የሰው ኃይል አስተዳደር መረጃ ሥርዓቶችን (HRMIS) ያጠቃልላል። ኤች.አይ.ኤስ የጤና መረጃን ለመሰብሰብ፣ ለማስኬድ፣ ሪፖርት ለማድረግ እና ለመጠቀም የተቀናጀ ጥረት ነው፡፡ ፖሊሲ ለማሻሻልና እና የተለያዩ ውሳኔዎችን ለመስጠት፣ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ለመቅረፅ በየደረጃው የምንሰበስበው መረጃ ወሳኝ ነው፡፡
ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ትክክለኛና ተዓማኒ የሆኑ መረጃዎች አስፈላጊ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ጠንካራ የጤና መረጃ ስርዓት ወይም አያያዝ (ኤች.አይ.ኤስ) የጠንካራ የጤና ስርዓቶች የጀርባ አጥንት ነው የሚባለው፡፡ ትክክለኛውን መረጃ በትክክለኛው ጊዜ ለትክክለኛው ሰው ማቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ (right information into the right hands at the right time) ይህም ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለአስተዳዳሪዎች እና ለግል አገልግሎት ሰጪዎች ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከአንድ ታካሚ ሕክምና አሰጣጥ እስከ ብሄራዊ እስከሆነው አገልግሎት ድረስ የሚሰራው በተሰበሰበው መረጃ ላይ ተመስርተው ነው፡፡
ከላይ የሚወጣው ፖሊሲ ከታች የተሰበሰበውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ነው፡፡ ፕሮግራም ሲቀረፅ፣ ህግ ሲሻሻል፣ መግለጫ ሲሰጥ፣ በጤናው በኩል ያሉት የትምህርት ስርዓት ሲቀረፅ፣….ወዘተ ከታች ነርሶች ከትላልቅ ሆስፒታሎች እስከ ታች ጤና ኬላዎች ድረስ በሚሰበስቡት መረጃ መሰረት ነው፡፡
ጠንካራ የሆነ የጤና መረጃ ስርዓቶች የመረጃ ተደራሽነትን በማሳደግ የበለጠ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን መኖር አለበት፡፡ የጤና እንክብካቤን በብቃት ለማሻሻል አንዱ መንገድ የጤና መረጃ አያያዝን ማሳደግ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂን በየደረጃው መጠቀም ነው። አላስፈላጊ ወጪዎችንና እና ስህተቶችን በከፍተኛ ሁኔታ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል፣
 የኤችአይኤስ (Health information systems) ዋና ጥቅሞች-
o የመረጃው ማእከላዊነት፡ ምንም እንኳን መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ቢኖረውም ሁሉንም መረጃዎች የተማከለ እንዲሆን ያግዛል። የታካሚ ፋይል በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ ሊደረስበት ይችላል።
o ውጤታማነቱ ይጨምራል፤ በመረጃው ማእከላዊነት ምክንያት ብዙ ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት መቆጠብ ይቻላል፡፡
o ደህንነቱ እና ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል፡ ሁሉም የታካሚ መዛግብት ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መቀመጥ አለበት፡፡ እና እነዚህን ሰነዶች ለማግኘት አንዳንድ ማረጋገጫ ያስፈልጋል ስለዚህ ሰነዶቹ ለአደጋ የተጋለጡ አይሆኑም፡፡ በእርግጥ የሳይበር ጥቃት ስጋት አለ።
በየትኛውም የህክምና መስጫ ማዕከል ውስጥ የሚሰበሰበው አብዛኛው መረጃ በዋናነት በነርስ ባለሞያዎች ነው፡፡ ህመምተኛው ገና ወደ ተቋሙ ሲገባ የሚሰጠው መረጃ የሚመዘገበው በነርስ ባለሞያዎች ነው፡፡ ሲወጣም እንዲሁ የሚመዘገበው በነርሶች ነው፡፡ ይሄ ማለት እስከአሁን ላለው የህክምና አሰጣጥ ፖሊሲ ነርሶች ከፍተኛ የሆነ ሚና ተጫውተዋል፡፡ አሁንም እየተሰበሰበ ያለው መረጃ ነገ ላይ ለሚመጣው አዲስ አሰራር መንስዔ መሆናቸውን ነው፡፡ ስለዚህ እየሰጠን ያለነው ህመምተኛውን ማዕከል ያደረገ የህክምና አሰጣጣች የበለጠ እንዲዳብር ነርሶች የሚሰበስቡትን መረጃ ማስተዋል አለባቸው፡፡ በሃላፊነትም ስሜት መሆን አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ፌደራል መንግስቱም ሆነ የክልል መንግስቱ ትኩረት መስጠት አለበት የሚል መልዕክት አለኝ፡፡
ክብር ለነርሶች ይሁን
ባምላኩ አበባው (ነርስ)፣ ከጅማ ህክምና ማዕከል
...................................................................................................
Nurses and health information system
At any level of the medical system, the information flow and activity has a significant role in the improvement of the medical system. Today's updated medical delivery comes from the data collected at every level of medical facilities. And our data handling and collection today is crucial for the medical system we provide or access tomorrow. Health information systems (HIS) refers to any system that captures, manages, or transmits information about the health of individuals or organizations working in the health sector. This definition is very broad and deep. It includes medical care, disease and patient monitoring systems, laboratory data, hospital patient management systems (PAS), and human resource management information systems (HRMIS). HIS is a coordinated effort to collect, process, report, and use health information. The information we collect at every level is critical to making decisions and formulating various programs. Accurate and reliable data are essential to building a strong health system. This is why a strong health information system or management (HIS) is said to be the backbone of strong health systems. It is important to get the right information to the right person at the right time. (right information into the right hands at the right time) which policy makers, managers and private service providers need. From individual patient care delivery to national services, it operates based on the data collected. The above policy is based on the information collected below. When a program is designed, a law is amended, a statement is made, the education system on the health side is designed, etc., it is based on the information collected by the nurses from the big hospitals to the health centers. Stronger health information systems should increase access to information and increase transparency and accountability. One way to effectively improve health care is to improve health information management. For this, it is necessary to use the technology produced by the age at every level. It has the potential to significantly reduce unnecessary costs and errors;  Main advantages of HIS (Health information systems)- o Centralization of data: It helps to centralize all data despite its geographical location. A patient file can be accessed anytime anywhere. o Increases efficiency; A lot of time, money and energy can be saved due to the centralization of data. o Maintain security and confidentiality: All patient records must be kept secure. And some authentication is required to access these documents so the documents are not compromised. Of course there is the threat of cyber attacks. Most of the information collected in any medical center is primarily done by nurse practitioners. When the patient enters the facility, the information is recorded by the nursing staff. It is also recorded by the nurses when it comes out. This means that nurses have played a significant role in the current medical delivery policy. The information that is still being collected is that they are the reason for the new system that will be introduced tomorrow. Therefore, in order to further develop the patient-centered care we are providing, nurses must understand the data they collect. It should also be a sense of responsibility. I have a message that both the federal government and the state government should pay attention to this.

Glory be to the nurses Bamlaku abebaw (nurse), from Jimma Medical Center
key for prosperous/የብልፅግና ቁልፍ

ስለበጎ ነገር እንነጋገር፡፡ ለኢትዮጲያ እና ኢትዮጲያውያን ለውጥ ብልፅግና በጋራ እንድከም፡፡ ስለዚህ የሚያስተምር ከልቡ ያስተምር፣ የሚመራ ከልቡ በማስተዋል ይምራ፣ ……..ወዘተ፡፡

Post a Comment

Previous Post Next Post