Roles of a Nurse (part two)
የነርሶች ሚና
ነርሶች ማህበረሰባቸውን በህክምና ተቋም ብቻ ሳይሆን ከህክምና ተቋም ውጭ ባላቸው ህይወት በተለያዩ መንገዶች ያገለግላሉ፡፡ ይሳተፋሉ፡፡ በተለይ በጤና እንክብካቤ ስርዓት ውስጥ ለየት ያሉና አስፈላጊ የሆኑ ሚናዎች አሏቸው። የተወሰኑትን እንጥቀስ ብንል እንኳን ነርሶች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎችን ያበረታታሉ፣ ለታካሚዎች ወግነው ይሟገታሉ፣ የጤና ትምህርት ይሰጣሉ፣ ለብዙ ታካሚዎች ያለመሰልቸት ይንከባከባሉ፣…..ወዘተ ብዙ ማለት ይቻላ፡፡. የነርሶች ተግባራት ባለፉት ዓመታት ውስጥ በተወሰነ ደረጃ እድገት አሳይቷል፡፡ በተለይ በእኛ ሀገር የተነበራቸው ቦታ፣ ባለሞያዎቹ ነርሶች እራሳቸው ለራሳቸው የሚሰጡት የተዛባ እይታ፣ ህሙማን እራሳቸው ለነርሶች ያላቸው የተዛባ አመለካከት፣ መንግሰት ለሙያው የሰጠው ያነሰ ትኩረት ስለነበረ ሙያው በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ አድርጎት ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ነርሶች በጤና እንክብካቤ ውስጥ ያላቸው ጠቀሜታ ግልጽ የሆነና እጅግ አስፈላጊ ስለመሆኑ የሚጠራጠር የለም፡፡
ዘመናዊ ህክምና ከመጣ ጀምሮ የነርሶች ሚና ከማጽናናት፣ መድሐኒት ብቻ ከመስጠት፣ አልጋ ከማንጠፍ፣…ወዘተ ወደ ዘመናዊ የሆነ የጤና አጠባበቅ እና እንክብካቤ ወደመስጠት አድጓል፡፡ የነርስ ባለሙያዎች በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ህክምና እና የጤንነት ትምህርት በሄዱበት እየሰጡ ነው፡፡ በአሁን ሰዓት ነርሶች እንደ ሁለንተናዊ ተንከባካቢዎች፣ የታካሚ ጠበቃዎች፣ ስፔሻሊስቶች እና ተመራማሪዎች ሁለገብ ሚና አላቸው።
የታካሚ ተንከባካቢ ናቸው ስንል ምን ለማለት ነው?
የነርስ ዋና ተግባር ህመምተኛውን በትክክል ፍላጎቱን መለየት፣ በፍላጎቱ ልክ ማስተናገድ ከዚህ በተጨማሪም በሽታን በመከላከል እና የጤና ሁኔታዎችን በመለየትና በማከም ለታካሚዎች እውነተኛና ሃቀኛ ተንከባካቢ መሆን ነው። ይህንን ለማድረግ ነርሶች በሽተኛውን መከታተል እና በሕክምና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ለማገዝ ማንኛውንም አስፈላጊ መረጃ መመዝገብ አለባቸው ።
ነርሶች የትኛውንም ዓይነት ጉዳቶችን ይንከባከባሉ፣ አስፈላጊውን መድሃኒት ይሰጣሉ፣ ተደጋጋሚ የሕክምና ምርመራዎችን ያካሂዳሉ፣ ዝርዝር የሕክምና ታሪክን ይመዘግባሉ፣ የልብ ምትን እና የደም ግፊትን ይቆጣጠራሉ፣ ለየት ያሉ ምርመራዎችን ማዘዝ ይችላሉ፣ የሕክምና መሣሪያዎችን ይሠራሉ ይጠግናሉ፡፡ በተጨማሪም ነርሶች የታካሚዎችን ምቾት ያረጋግጣሉ፣ ፋሻ ይለውጣሉ፣ በታካሚው ሁኔታ ላይ ያሉ ማናቸውንም ለውጦች ለሌሎች ነርሶች ወይም ዶክተሮች ያሳውቃሉ፣ የታካሚ እንቅስቃሴዎችን ይመዘግቡ እና ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ይወስዳሉ። ይሄ ሁሉ ለህመምተኛው እንክብካቤ ሲባል የሚደረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተግባር የእንክብካቤ አካል የህክምናው አንድ ክፍል ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ አንዱ ቢጎድል ህመምተኛው ምቾት አይሰማውም፡፡ ትክክለኛ ህክምና አገኘ ሊባልም አይችልም፡፡
እናም ነርሶች ብዙውን ጊዜ የታካሚውን ህክምና አሰጣጥ እና ለእያንዳንዱ ተግባር እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ ለእያንዳንዱ ዝርዝር ሁኔታ ትኩረት በመስጠት ይከታተላሉ። አንድ ችግር ከታወቀ ቀድመው ነርሶች ናቸው ብዙውን ጊዜ በመጀመሪያ የሚያስተውሉት፡፡ ይሄንን ብቻ እንደቀላል ነገር መመልከት ችግር አለው፡፡ ስለዚህ ችግሩን በተለይም ድንገተኛ ሁኔታ ሲያጋጥም ለሀኪም በፍጥነት በማሳወቅ ሳይባባስ ለህክምና ቡድኑ በማሳወቅ ህክምናው እንዲቀጥል ማድረግ ህይወትን ማዳን ይችላሉ፡፡
በሕክምናው ሂደት ውስጥ ነርሷ የታካሚውን ለውጥ በመከተል፣ የታካሚውን ጥቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ነርሶች የሚሰሩት ስራ ወይም የሚሰጡት እንክብካቤ መድሃኒቶችን እና ሌሎች የሕክምና ዘዴዎችን ከማድረግ በላይ ነው፡፡ ነርሶች ብዙውን ጊዜ ለታካሚዎች ሁለንተናዊ እንክብካቤ ሃላፊነት አለባቸው፣ ይህም የግለሰቡን ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ፍላጎቶች ሊያጠቃልል ይችላል።
ለታካሚዎች ድጋፍ ይሰጣሉ ሲባል ምን ማለት ነው?
እንደ ሀኪም ከሚጫወቱት ሚና በተጨማሪ ነርሶች ብዙውን ጊዜ ለታካሚዎቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ስሜታዊ ድጋፍ ይሰጣሉ። ይህም በሽተኛው ለሚሰጡት ህክምና መረዳቱን እና ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ታካሚዎችን ማዳመጥ እና አካላዊ፣ ስሜታዊ፣ አእምሯዊ እና መንፈሳዊ ፍላጎቶቻቸውን መገምገምን ይጨምራል፡፡ መረዳት ማለት እስከዚህ የጠለቀ እና የሰፋ ነው፡፡
ነርሶች ብዙውን ጊዜ ታካሚዎችን እና የሚወዷቸውን ሰዎች በህመማቸው ላይ ስሜታቸውን እና ብስጭታቸውን እንዲያካሂዱ ይረዷቸዋል፡፡ በምክር እና በትዕግስት፣ ትምህርት በመስጠት፣ ነርሶች ለታካሚዎች እና ለቤተሰባቸው አባላት የህክምና አማራጮችን በማብራራት እንዲሁም ለታካሚዎቻቸው ጤና እና ደህንነት በመደገፍ ሊረዱ ይችላሉ። እያደረጉትም ነው፡፡
ነርስ ብዙውን ጊዜ የታካሚን የህክምና፣ የህግ እና የሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ እንደ ታካሚ ጠበቃ ሆና ታገለግላለች። ብዙ የታመሙ ሕመምተኞች የሕክምና ሁኔታዎችን ሊረዱ እና ተገቢውን እርምጃ ሊወስዱ ስለማይችሉ, በሽተኛውን መደገፍ ብዙውን ጊዜ የነርሷ ሚና ነው፡፡ ትልቁ ችግር ይሄ አስገራሚ ሚናቸው በህክምና ተቋም ውስጥ ስለሆነ በዚህ ልክ መሆናቸውን የሚያውቅ ውስጥ የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ የሚመለከተው ደግሞ አቅልሎ ይመለከተዋል እንጅ ለታመመው እፎይታ የሚሰጥ ሰው ትልቅ ተግባር ነው፡፡
ይህ በተለይ የሕክምና ውሳኔ በሚደረግበት ጊዜ ታካሚውን ወክለው የሚቀበሉ ነርሶች ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ ነርሶች ለታካሚዎች ጥያቄዎች ሲኖራቸው ወይም ስለ ሕክምናዎች ማብራራት ሲኖርባቸው፣ ሂደቶች ወይም ማናቸውም የእንክብካቤ አይነቶችን ሲፈሩ ብዙ ጊዜ ያሳውቃሉም ይደግፋሉ።
የእንክብካቤ እቅድ ማውጣት ማለት ምንድነው?
አንድ ነርስ በሽተኞችን በማከም የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ በቀጥታ ይሳተፋል፡፡ ስለሆነም ነርሶች የታካሚ ምልክቶችን በሚገመግሙበት ጊዜ በትኩረት እንዲያስቡ እና ተገቢ ምክሮችን ለመስጠት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለይተው ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ነርሶች በታካሚ የህክምና አሰጣጥ ዕቅዶች ውስጥ ወሳኝ ሚና አላቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት ነርሶች ምልክቶቻቸውን በቅርበት እና በተከታታይ ስለሚከታተሉ ከታካሚው ግለሰብ ጋር በደንብ ስለሚያውቁ ነው። ስለዚህ ነርሶች ጥሩ የታካሚ የጤና ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ከሌሎች የህክምና ቡድን አባላት ጋር መተባበር አለባቸው።
የታካሚ ትምህርት እና ድጋፍ አሰጣጥ እንዴት ያለ ነው?
ነርሶችም ታማሚዎች ጤንነታቸውን፣ ህመማቸውን፣ መድሃኒቶቻቸውን እና ህክምናዎቻቸውን በተቻለ መጠን እንዲረዱ የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው። ይህ በተለይ ህመምተኞች ከሆስፒታል ሲወጡ እና በቤት ውስጥ ህክምናቸውን በትክክል እንዲቀጥሉ ለማድረግ ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ከህክምና ተቋሙ ሲወጡ በአብዛኛው የሚያገኟቸው ነርሶችን ስለሆነ ማለት ነው፡፡
ነርስ ለታካሚው እና ለቤተሰባቸው ወይም ለተንከባካቢው ከሆስፒታል ወይም ከህክምና ክሊኒክ ሲወጡ ምን ማድረግ እና መጠበቅ እንዳለባቸው ለማስረዳት ጊዜ ወስዶ ማስረዳት አለባቸው። ነርሶች በሽተኛው ድጋፍ እንደሚሰማው እና አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ የት እንደሚፈልግ እንደሚያውቅ ማረጋገጥ አለባቸው።
በሁሉም የጤና እንክብካቤ ዘርፍ፣ ነርሶች ትምህርት ይሰጣሉ፣ ጤናማ ልምዶችን ያስተዋውቃሉ፣ እውቀታቸውን ያካፍላሉ እና ታካሚዎች እንዲፈውሱ ይረዷቸዋል። ታካሚዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን በመምራት፣ ነርሶች ለታካሚዎች ለሌሎች አገልግሎቶች፣ ግብዓቶች እና ክፍሎች ተገቢውን ሪፈራል ሊሰጡ ይችላሉ።
ይህን ሁሉ ማድረግ እንዲችሉና የተሰጣቸውን ሚና በትክክል እንዲወጡ ደግሞ ከመንግስት ሆነ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ብዙ ይጠበቃል፡፡ በየተቋሙ ያሉ የህክምና ባለሞያዎችን መረዳትና መርዳት ማለት ህመምተኛውን መርዳትና መረዳት ስለሆነ ባለሞያች ለየት ያለ ትኩረት ይፈልጋሉ፡፡
በችግር ውስጥ ያለ ባለሞያ በችግሩ ምክንያት ሚናውን በትክክል ላይወጣ ይችላል፡፡ ይሄ እውነት ነው፡፡ ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ከተወሰኑት በስተቀር አብዛኞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ማህበረሰብን ማገልገል እውነት “ጀግና” ያስብላል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደሌለበት ግና መስማማት አለብን ብዬ አምናለው፡፡
መልካም ጊዜ ተመኘውላችሁ
ክብር ለነርሶች ይሁን
ባምላኩ አበባው (ነርስ)፣ ጅማ ህክምና ማዕከል
..................................................................................................................................................
The role of nurses
Nurses serve their communities in many ways, not only in the medical institution, but in their lives outside of the medical institution. They participate. They have unique and important roles in the health care system. To name a few, nurses promote healthy lifestyles, advocate for patients, provide health education, tirelessly care for many patients, etc. The duties of nurses have evolved somewhat over the years. Especially in our country, the professional nurses themselves have a distorted view of themselves, the patients themselves have a distorted view of nurses, the government paid less attention to the profession, so it has kept the profession from growing as it should. However, there is no doubt that the role of nurses in health care is clear and vital.
Since the advent of modern medicine, the role of nurses has grown from comforting, giving only medicine, making beds, etc. to providing modern health care and care. Nurse practitioners are providing evidence-based medicine and wellness education on the go. Nurses today have a multifaceted role as holistic caregivers, patient advocates, specialists, and researchers.
What do we mean when we say they are patient caregivers?
The main task of a nurse is to accurately identify the patient's needs, to treat them according to their needs, and to be a true and honest caregiver to patients by preventing disease and identifying and treating health conditions. To do this, nurses must observe the patient and record any necessary information to assist in the medical decision-making process.
Nurses care for any injuries, administer necessary medications, perform routine medical examinations, record detailed medical histories, monitor heart rate and blood pressure, order special tests, operate and repair medical equipment. Nurses also ensure patient comfort, change bandages, notify other nurses or doctors of any changes in the patient's condition, record patient movements, and perform other related duties. All this is done for the sake of patient care. Each care component is a part of the treatment. If any one of these is missing, the patient will not feel comfortable. It cannot be said that he received proper treatment.
And nurses often monitor the patient's treatment delivery and how they respond to each task, paying attention to every detail. Nurses are often the first to notice a problem. Taking this for granted is problematic. Therefore, you can save lives by notifying the doctor quickly about the problem, especially in an emergency, and notifying the medical team before it gets worse.
In the process of treatment, the nurse follows the patient's changes, taking into account the patient's interests, the work that nurses do or the care they provide is more than just administering drugs and other treatment methods. Nurses are often responsible for the holistic care of patients, which may include the individual's psychological, social, and spiritual needs.
What does it mean to provide patient support?
In addition to their role as physicians, nurses often provide emotional support to their patients and their families. This includes making sure the patient understands and is ready for the treatment, listening to patients, and assessing their physical, emotional, mental, and spiritual needs. Understanding is so deep and wide.
Nurses often help patients and their loved ones process their feelings and frustrations about their illness. Through counseling and patience, providing education, nurses can help patients and their family members by explaining treatment options and advocating for their patients' health and well-being. And they are doing it.
A nurse often serves as a patient advocate to protect a patient's medical, legal, and human rights. Because many sick patients cannot understand medical conditions and take appropriate action, it is often the nurse's role to support the patient. The biggest problem is that this is a part of society that knows they are valid because of their amazing role in the medical establishment. And the one who looks at it takes it lightly, but it is a great task for a person who gives relief to the sick.
This is especially true of nurses who act on behalf of the patient when making medical decisions. In addition, nurses often inform and support patients when they have questions or need clarification about treatments, procedures, or fears of any type of care.
What is care planning?
A nurse is directly involved in the decision-making process of treating patients. Therefore, it is important for nurses to think carefully when assessing patient symptoms and identify potential complications in order to make appropriate recommendations.
Nurses play a vital role in patient care planning. This is because nurses are familiar with the individual patient as they monitor their symptoms closely and consistently. Therefore, nurses must collaborate with other members of the medical team to promote optimal patient health outcomes.
How is patient education and support provided?
Nurses are also responsible for ensuring that patients understand their health, illness, medications, and treatments as best as possible. This is particularly important when patients are discharged from hospital and are responsible for ensuring that they continue their treatment properly at home. This is because they are mostly nurses when they leave the medical facility.
A nurse should take the time to explain to the patient and their family or caregiver what to do and expect when they leave the hospital or medical clinic. Nurses must ensure that the patient feels supported and knows where to seek additional information if necessary.
In all areas of health care, nurses provide education, promote healthy habits, share knowledge, and help patients heal. By guiding patients and their families, nurses can provide patients with appropriate referrals to other services, resources, and departments.
A lot is expected from the government and relevant stakeholders to be able to do all this and fulfill their assigned roles properly. Because understanding and helping the medical professionals in each institution means helping and understanding the patient, professionals need special attention.
A professional in crisis may not perform the role properly because of the crisis. This is true. It is known that most of the health professionals in Ethiopia are in a difficult situation, except for a few. Serving the community in this situation is considered a true "hero". But I believe that we should agree that this situation should not continue.
I wish you a good time
Glory be to the nurses
Bamlaku abebaw (Nurse), Jimma Medical Center